>

የህወሓት ተንኮሎች እና 2010 (በዶ/ር ታደሰ ብሩ)

በአሁኑ ሰዓት ህወሓት እየሠራቸው ያሉት ሶስት ከፍተኛ አገራዊ አሻጥሮች (የተንኮል ሥራዎች) 2010ን የመናጥ ዓመት ያደርጉታል ብዬ አስባለሁ።
የሚከተሉት ሶስት ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንድናደርግ እጠይቃለሁ

(1) ህወሓት ብአዴን ላይ (በተለይም ገዱ አንዳርጋቸው ላይ) የሠራው አሻጥርና የአሻጥሩ ውጤት የሆነው “የድንበር መካከል ስምምነት”፤

(2) በሱማሌ ክልል ልዩ ኃይልና በኦሮሚያ ነዋሪዎች መካከል የተከፈተው ከግጭት ያለፈ ጦርነት፤ እና (3) የሀረሪ ክልል የገባበት ውጥንቅጥ። የሶስቱም የተንኮል ሥራዎች ግብ ብአዴንና ኦህዴድን ማዳከምና ህወሓት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሸረሸረበት ያለውን የበላይነትና ሙሉ ቁጥጥር በማያሻማ ሁኔታ ማረጋገጥ ነው። በአሁኑ ሰዓት ህወሓት ራሱ ችግር ውስጥ ያለ መሆኑ እየታወቀው በመሆኑ ከኃይለማርያሙ ደኢህዴን በተጨማሪ የሶማሊ ክልሉን ሶህዴፓና የሀረሪ ክልሉን ሀብሊ አሰልፎ በብአዴንና ኦህዴድ ላይ ስውር ጦርነት እያካሄደ ነው።
እነዚህን አሻጥሮች ማክሸፍ የሚችሉ ሀሳቦችን ማፍለቅና መተግበር የሚችሉ ሰዎች ብአዴንና ኦህዴድ ውስጥ ካሉ የህወሓት አሻጥሮች በቀላሉ ሊቀለበሱ የሚችሉ ናቸው።
ብአዴንና ኦህዴድ ሕዝባዊ ትግሉን በገሀድ ወይም በከፊል ገሀድ የሚደግፉበት ቀዳዳ ራሱ ህወሓት ፈጥሮላቸዋል፤ ከተጠቀሙበት የህወሓት አሻጥሮችን በመቀልበስ ህወሓትን ተነጥሎ እንዲጠፋ ማድረግ ይችላሉ። አለበሊዚያ ግን 2010 ለኢህአዴጎች ሁሉ መጥፎ ዓመት ነው የሚሆነው።

Filed in: Amharic