>
5:13 pm - Monday April 19, 6771

እንግሊዝ ለሃገሩ ራሡን የሚሠዋና የማይራደረው የጀግናው እዳ አለባት (ተስፋሁን ተሾመ አለማየሁ)

“አፄ ቴወድሮስ” የዙፋን ስማቸው «ቴዎድሮስ»ን የወሰዱትከፍካሬ ኢየሱስ ከተገኘ ትንቢት ነበረ ማለታችን እናስታውሳለን። በዚያው ትንቢት በኩል በዓለም መጨረሻው ክፍለ ዘመን፣ ተወዳጁ፣ የጥንቱ ዘመን ንጉስ ቀዳማዊ ቴዎድሮስ እንደገና ተነስቶ አገሪቱ(ኢትዮጵያን ማለቱ ነው ለ40 ዓመታት ይገዛል የሚል ነበር ይላል ታሪክ። “ቴዎድሮስ” የሚለው ስም ከግሪክ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ጤዎስዶሮስ ‘የአምላክ ስጦታ’ ማለት ነው። ዓጼ ቴወድሮስ የቋራ አስተዳዳሪ የነበሩት ደጃዝማች ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ጊዮርጊስ (ባጭሩ ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ) ልጅ ናቸው። እናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ወንድበወሰን ሲባሉ አመጣጣቸውም ከ ጎንደር ከተማ ባላባቶች ነበር። የወይዘሮ አትጠገብ እናት ወይዘሮ ትሻል ስትባል የበጌምድር ክፍል መሳፍንት ዘር ነበረች፣ በአባቷ በኩል አያቷ ራስ ወዳጆ በዘመናቸው ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ባላባት ነበሩ። የወይዘሮ አትጠገብ ድህነት በታሪክ መጻህፍት በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ቢሆንም አመጣጡ እንዲህ ነበር፡ የህጻኑ ቴወድሮስ አባት ደጃች ሃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ከሱዳኖች ጋር በተነሳ ጦርነት በጀግንነት ሲወድቁ እናት ገና ሁለት አመት የሆነውን ልጇን ይዛ ከቋራ ወደ ጎንደር ከተማ ሄደች።
በዚህ መሰረት ቴዲ የጀግና ልጅ ጀገና ነበር ማለት ይቻላል። ወደ ጎንደር ልጇን ቴወድሮሥን ይዛ የገባች እናቱ ሁለተኛ ላታገባ በመቁረብ ልጇን ብቻዋን ማሳደግ ግድ አላት። አንዳንዶች በዚህ ምክንያት እራሷን ለማስተዳደር ኮሶ ትሸጥ ነበር ሲሉ ጸሃፊው ጳውሎስ ኞኞ ወይዘሮ አትጠገብ መቼውንም ኮሶ አትሸጥም ነበር ይላል (ኮሶ ትሸጥ ነበር የሚለው የቴዲ ጠላቶች ፈጠራ ወሬ ነበር በማለት ያስረዳል)። ያም ሆነ ይህ ህጻኑ ቴወድሮስ በድህነት እንዳላደገ ሁሉም የታሪክ ጸሃፊያን ይስማማ።
አንድ ለናቱ ቴወድሮስ በእናቱ በኩል እህትም ሆነ ወንድም አልነበረውም። የወደፊቱ አጼ ቴዎድሮስ ተዋበች አሊ የተባለችውን የዘመነ መሳፍንት ታላቅ ባላባት፣ የራስ አሊ
አሉላን ልጅ አገባ። ተዋበች በጊዜው የ15 ዓመት ወጣት የነበረች ሲሆን ቁንጅናዋና
አስተሳሰቧ በጊዜው በነበሩ ሰወች ዘንድ የተደነቀ ነበር። ሁለቱ በፍቅር በመውደቃቸው ቴወድሮስ በአባቷ ራስ አሊና በአያቷ እቴጌ መነን ላይ ሲያምጽ ባሏን ትደግፍ ነበር።አጼ ቴወድሮስ የሚስታቸውን መታመም ከዘመቻ መልስ ላይ ከሰሙ በኋላ እቴጌ
ተዋበች ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በኃዘኑ ወቅት እስቲ ጠይቁልኝ እርቃ ሳትሄድ
እትጌ ተዋበች ሚስት ናት ገረድ?
ብለው እንደተቀኙ በታሪክ መዛግብት ሰፍሮ ይገኛል። ከሁለት ዓመት ሀዘን በኋላ ዓፄ ቴዎድሮስ ከሁለተኛ ሚስታቸው ጋር ተገናኙ። በደራስጌ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተቀምጠው ሳለ አንድ ወታደራቸው ወደ ርሳቸው ቀረበና «ጌታየ አንዲት ሴት አገኘሁ ፊቷም እንደ ፀሐይ የሚያበራ ነው።» ካለ በዃላ ልጅቱም ወደ ቤተመንግሥት ቀረበች፣ ስሟም ጥሩነሽ ውቤ፣ የደጃዝማች ውቤ ኃይለማርያም ልጅ ነበረች። አፄ ቴወድሮሥም አይተዋት “እውነትም ወርቅ ናት” በማለት አገቧት። በዚህ ወቅት ንጉሠ ነገሥቱ አባቷን ራስ ውቤን አስረዋቸው ነበር። ራስ ውቤ የሰሜን አካባቢ እንደ ሰራየ፣ ሐማሴንና አንጎት አካባቢወች (ሰሜን ወሎ) አስተዳዳሪ ሲሆኑ ከዓፄ ፋሲለደስ የሚወለዱ ስለነበሩ ለንጉሥነት የሚገዳደሩ ነበሩ። የጥሩነሽ እናት ደግሞ ወይዘሮ ላቂያየ የተባሉ የትግራይ መሳፍንት ዘር ነበሩ። ከኒህ ሚስታቸው ደጃዝማች ዓለማየሁ ቴዎድሮስ የተባለውን ከሁሉ በላይ የሚወዱትን፣እርሳቸውን እንዲተካ ያጩትን ልጅ ወለዱ። ዓፄ ቴዎድሮስ በአጠቃላይ 4 ጊዜ ሲያገቡ 6 ወንድና 3 ሴት ልጆች እንደ ነበሯቸው ታሪክ ያወሣል የበሣል አዕምሮ ባለቤቱ አፄ ቴወድሮስ። የወጣት ጀግና!! እንግሊዝ ለሃገሩ ራሡን የሚሠዋና የማይራደረው የጀግናው እዳ አለባት እላለሁ።
Filed in: Amharic