>

“የተኛውን ትልቅ አውሬ የቀሰቀስነው በገዛ እጃችን ነው” ጃፓናዊያን (በቅዱስ መሃሉ)

አንስታይን፣አሜሪካ እና ጃፓን:-የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ!
እኤአ ሴፕቴምበር 2 ቀን 1945ዓ/ም -የዛሬ 72መት በዛሬው ቀን ይህ ሆነ!

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አውድማን በሰሜን አፍሪካ፣ምዕራብ አውሮፓ እና አውስትራሊያን ከጃፓን ወረራ ለመታደግ በተደረገው ትንቅንቅ ውስጥ አሃዱ ብላ የተቀላቀለችው አሜሪካ ጀርመን እንጅ ጃፓን ያን ያህል ታስቸግራለች ብላ የገመተች አትመስልም። ይህንኑ የጀርመን ፍራቻ በተለይም አልበርት አይንስታይን “ናዚ የአቶም ቦምብ ሊሰራ ይችላል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ አሜሪካንም ቢሆን ከናዚ የሚታደጋት አታገኝም።” በማለት ፕሬዝዳንት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልትን በማሳመናቸው የማንሃተን ፕሮጀክት እንዲጀመር ተደረገ። ከሁለት ዓመት በኋላ የፕሮጀክቱን ሂደት እና ስኬታማነት እርግጠኛ እየሆኑ ሲመጡ አልበርት አይንስታይን እና ሊዮ ዚላርድ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት “አቶሚክ ቦምቡ የአሜሪካን ጠላቶች በጦር ሜዳ ላይ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ እጅ እንዲሰጡ ማድረጊያ ለማስፈራሪያ ብቻ የሚውል ነው።” በማለት ዕቅዳቸውን ተናገሩ። ይሄውም የሚደረገው ሰው በማይኖርበት ቦታ ላይ በመጣል “እንደዚህ ከምናረጋችሁ እጅ ስጡ!” በማለት ሊሆን እንደሚችል ዝርዝር ሃሳብ አቀረቡ። ይህን ዝርዝር ሃሳብ በቅጡ ማንበብ እንኳ ሳይችሉ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ሞት ቀደማቸው። ፕሬዝዳንት ሃሪ ትሩማን ስልጣኑን ተረከቡ።

ጃፓን ለአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በኤዥያ ተረጋግተው ተቀምጠው ለነበሩ አውሮፓዊያን ቅኝ ገዥዎች ራስ ምታት መሆኗን ቀጥላለች። በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጀርመን ሽንፈት ሲቋጭ ከማንሃተን ፕሮጀት ተሳታፊ ሳይንቲስቶች ውስጥ ኤድዋርድ ቴለር የአቶም ቦምብ መስራት የሚያስችለውን ቀመር ከአንስታይን E=MC2 ውስጥ ለይቶ ማግኘት ቻለ። በዚሁም መሰረት የተቀመረው የአቶም ቦምብ በኒው ሜክሲኮ ስኬታማ ሙከራውን አደረገ። የጀርመንን ሽንፈት ተከትሎ ከራሽያ፣ከቻይና፣ከፈረንሳይ እና ከእንግሊዝ መሪዎች ጋር በበርሊን የሚገኙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ስለ አቶም ቦምቡ ስኬታማ ሙከራ በስልክ ተነገራቸው። በዜናው በጣም የተደሰቱት ሃሪ ትሩማን አብረዋቸው ለነበሩት መሪዎች “ጃፓንን ከዚህ በፊት እናንተም ሆነ ዓለም ዓይቶት በማያውቀው መሳሪያ ልንቀጣት ነው?ምን ትላላችሁ?” ሁሉም በአንድ ድምጽ በተለይም በተለያየ ጊዜ በጃፓን ሽንፈት እና ውርደትን የተከናነቡት ቻይና እና ሩሲያ “ዛሬውኑ አድርጉት!ትመታ!” ሲሉ ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጡ።

“የአቶም ቦምቡ ሰዎች በማይኖርበት ቦታ በመጣል ጃፓንን እጅ እንድትሰጥ መጠየቅ ይሻላል” የሚለውን የአልበርት አይንስታይን እና የጓደኞቹን ሃሳብ ፕሬዝዳንት ሃሪ ትሩማን አልተቀበሉትም። ፕሬዝዳንቱ እና የጦር አዛዦቹ የአሜሪካን ሃያልነት ለዓለም ለማሳየት እና ጠላቶቿን ለማሸማቀቅ የተሻለ አማራጭ ባሉት እና ቦምቡን በቀጥታ ጃፓናዊያን ላይ መጣል በሚለው ሃሳብ ተስማሙ። እኤአ ነሃሴ 6 ቀን 1945 ዓ/ም በጃፓን ሄሮሽማ ውስጥ የመጀመሪያውን የአቶሚክ ቦምብ ጣለች። ጃፓኖች ብቻ ሳይሆኑ የተቀረው ዓለም ሁሉ ደነገጠ። በአንድ ጊዜ ከመቶ ሽህ በላይ ሰዎች አለቁ። ጃፓናዊያን “የተኛውን ትልቅ አውሬ የቀሰቀስነው በገዛ እጃችን ነው።” አሉ። ጃፓን በይፋ በጦርነቱ መሸነፏን አምና እጅ እንድትሰጥ አሜሪካ ጠየቀች። ጃፓን ግን አሻፈረኝ አለች። እኤአ ነሃሴ 9 ቀን 1945 ዓ/ም ማለትም የመጀመሪያው አቶሚክ ቦምብ ከተጣለ ከሶስት ቀናት በኋላ ናጋሳኪ ተደገመች። ይህኛው የአቶም ቦምብ የመቶ ሽህ ህዝብ ህይዎት ቀጠፈ። ከስድስት ቀናት በኋላ ኦገስት 15 ቀን ጃፓን እጅ እንደምትሰጥ በማስታወቅ ልክ የዛሬ 72ዓመት በዛሬው ቀን ማለትም ሴፕቴምቤር 2 ቀን 1945ዓ/ም ይህንኑ ሽንፈቷን በኦፊሴል በፊርማዋ አረጋገጠች።ቻይና፣ኮሪያ፣ራሽያ እና የደቡብ ምስራቅ ኤዥያ ሃገራት በጃፓን የተነጠቁትን ሉዓላዊ ግዛታቸውን መልሰው ማግኘት ቻሉ። የሆኖ ሆኖ አሜሪካንን ከፕሮፖጋንዳ ባለፈ ፊትለፊት ጦርነት ገጥማ አቅሟን የተፈታተነች የምድራችን ብቸኛ ሃገር ጃፓን ናት። በዚህም ምክንያት የኑክሌር ጦር መሳሪያ አረር የነደደባት ብቸኛ ሃገርም መሆን ችላለች። የጃፓንን እና የጃፓናዊያንን ያህል የኑክሌር ጦር መሳሪያን አደገኛነት በተግባር የሚያውቅ የለም። ዶናልድ ትራምፕን በምርጫ ውድድር ወቅት አድናቂዎቹ እና ደጋፊዎቹ “የሃሪ ትሩማንን ወኔ የታጠቀ ጀግና” እያሉ ሲያቀማጥሉት ነበር። የሃሪ ትሩማን ወኔ የአቶም ቦምብን በንጹሃን ላይ የማዝነብ ድፍረት ነው። ትራምፕ ይህ ድፍረት ካለው በማን ላይ እና በምን ምክንያት ሊጠቀመው እንደሚችል ለጊዜው ከብዥታ የጠራ መልስ የለም። የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ሜርክል ግን ከቀናት በፊት ስለ ትራምፕ እና አሜሪካ እንዲህ ብላለች •••ሙሉ ጽሁፉን በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ!
http://teaminitiatives.org/…/%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%88%b5%e…/

Filed in: Amharic