>

ቡሄ እንዲህም አልፏል (ታምሩ ተመስገን)

buhe chiboቡሄ ሲመጣ ሁሌም ከአዕምሮየ ‘ማትጠፋ አንድ ጨዋታ አለች፡፡ ፀሀፈ ወጉን ማን እንደሆነ ዛሬ ላይ ሆኘ በውል አላስታውስም፡፡ ታሪኩን ግን በብዥታም ቢሆን ስለማስታውስ ቀጥየ የምፅፍ ይሆናል፡፡
.
…. ከቁጫጭ ከፍ ከፍ የሚሉ ህፃናት (ግነት ዘይቤ ሳልጠቀም አልቀርም) ሎል፡፡ ከቁጫጭ ከፍ ከፍ የሚሉ ህፃናት ቡሄ ሲጨፍሩ ቆይተው ማምሻውን ካንድ ካድሬ ቤት በደረሱ ጊዜ ከመጨፈራቸው በፊት በአካባቢው የነበረ ሰው ተመልክቷቸው ኖሮ አውራውን ፓርቲ እያሞጋገሳችሁ ብትጨፍሩለት በደስታ ትልልቅ ሙል ሙሎችን ይሰጣችኋል ብሎ መከራቸና እብስ አለ፡፡
ህፃናቱ የተባሉትን መተግበር ጀመሩ፡፡
“ሆያ ሆየ”
አንዱ ሲያቀነቅን ሌሎች ይቀበላሉ
“ሆ”
“እዛ ማዶ አንድ ዳኛ”
“ሆ”
“እዚህ ማዶ አንድ ዳኛ”
“ሆ”
አውሬው ፓርቲ አደገኛ!”
እዚህ ጋር አውራው ፓርቲ በማለት ፈንታ አውሬው ፓርቲ በማለት እንደገደፉ የተረዳው ካድሬ ሲከንፍ ከቤቱ ተፈትልኮ ወጣና በትምክተኛ አይኖቹ አፈጠጠባቸው፡፡ ህፃናቱ አፀፋውን እንባ ባዘሉ አይኖቻቸው እየተቁለጨለጩ ምስኪንነታቸውን ለማስመስከር ጣሩ፡፡ ካድሬው ግን ማፍጠጡን አላቆመም ነበር፡፡ እነሆ ህፃናቱ የተሳሳቱትን ለማረም ሌላ ገጠሙ
“ሆያ ሆየ”
“ሆ”
“እዛ ማዶ አንድ ዳኛ”
“ሆ”
“እዚህ ማዶ አንድ ዳኛ”
“ሆ”
አውሪው ፓርቲ አደገኛ!”
አሁንም አውራው ፓርቲ በማለት ፈንታ አውሪው ፓርቲ ሲሉ በድጋሚ ተሳሳቱ፡፡ ልጆቹ ክው ብለው ደነገጡ፡፡ አንዳች መርዶ እንደሰማ ሰው ባሉበት ፈዘው ቀሩ፡፡ ኋላ ካድሬው ሁለት ባልዲ ውሃ ደፍቶባቸው ሲያበቃ ነፍስ ዘሩ፡፡ወዲያው ህፃናቱን ከቆሙበት ውልፍት እንዳይሉ አስጠነቀቃቸውና የሬድዮ መገናኛውን አውጥቶ ተደዋወለ፡፡ 3 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት መኪና ፌደራል ፖሊሶች በ6 ታንክ ታጅበው መጡና ህፃናቱን አፍሰው ወሰዷቸው፡፡
.
…. በነጋታው በEBC እንዲህ ተብሎ ተዘገበ “ሰበር ዜና! ቁጥራቸው በርከት ያሉ ህፃናት ሆን ብለው ህገ-መንግስቱን በሀይል ለመናድ ጠላታችን የሻቢያ መንግስት ድረስ በመሄድና በመመሳጠር ገዥው ፓርቲን የሚያጥላላ የቡሄ ግጥም በመማር ሀገር ሲያሸብሩ በትናንትናው ማታ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ አሸባሪዎችን በማጋለጥ ህዳሴአችንን እናፋጥን፡፡”
.
እነሆ ከዚህ ቀን በኋላ ስለ ህፃናቱ ሰማንም አየንም የሚል አልተገኘም….

Filed in: Amharic