>

በዚህ አያያዙዋ ሃገሬ መቼም አትናፍቀኝም...

ሰሞኑን ሙሉቀን መለሰ ሃገሬ አትናፍቀኝም! አለ ተብሎ የብዙሃን መነጋገሪያ እና መዘባበቻ ሲሆን ባየው ይህን ልል ተገደድኩ:: በእውነት…. ስለ እውነት እንነጋገርና…. እነዚህ ሙሉቀንን ሲያብጠለጥሉ የነበሩት ሰዎች ከሃገራቸው ውጪ ያሉና እነሱ በሃገራቸው ናፍቆት የነደዱ ሆነው ነው? ወይስ ውድና ተናፋቂ የሆነች ሃገሪቸው ላይ እየኖሩ ይቺ ሃገር ያልተናፈቀች ምን ይናፈቃል? እያሉን ነው?: እኔ በበኩሌ የሙሉቀንን አለመናፈቅ በሚያጠናክር ሁኔታ በአፅንኦት እናገራለሁ!!! ሃገሬ አትናፍቀኝም እላለሁ….. አሁን ባለችበት ሁኔታ ሃገሬ አትናፍቀኝም! በዚህ አያያዙዋ ሃገሬ መቼም አትናፍቀኝም…. ልጄን በጆሮው የምነግረው እንጂ በአይኑ የማሳየው ሃገር በዚህ ሰአት የለኝም!!!

ጂኒየስ የሆኑ ዜጎችዋን …. ሌላው ሃገር እንደ እንቁ እየሳሳ የሚጠቀምባት ምሁራኖችዋን ማኖር ያልቻለች ሃገሬ አትናፍቀኝም:: እነ አንዳርጋቸው ፅጌን.. እማዋይሽ አለሙን…እስክንድር ነጋን… አንዱአለም አራጌን.. ውብሸት ታዬን… ተመስገን ደሳለኝን…በቀለ ገርባን በእስር ቤት ቶርቸር የሚሰቃዩባት ሃገሬ አትናፍቀኝም! መረራ ጉዲናን የሚያህል ምሁር ባይሆን ትልቅ አባት ልጆቹ በሚሆኑ ውርጋጦች እጃቸውን የፊጥኝ ታስረው የሚነዱባት ሃገሬ በእውነት አትናፍቀኝም! ወጣት ልጆችዋ … እነ ኤልያስ ገብሩ.. ዳንኤል ሽበሺ.. የጉብዝናቸውን እድሜ ያለምንም ጥፋታቸው 9 ወር ሽንት ቤት አጠገብ ተኝተው …. በሽታ አትርፈው ለወጡበት ለዚህ ሰርቢስ 50,000 ብር ከፍለው ለሚወጡባት ለዛች ሃገር ምንም ናፍቆት የለኝም!

ልጆችዋ ሸሽተዋት በየአረብ ሃገር ጉዞዋቸው ሞታቸው መንገድ ላይ የሆነባትን ሃገር አልናፍቅም! በስደት በየ ጢሻው ከመውደቃቸው ይብስ በባእድ ሃገር የመፃተኛ ዋጋቸው አንሶ ተዋርደው…. ተርበው… ተጠምተው ለመኖር ጥለዋት የሸሹትን ሃገር እንዴት ነው የምናፍቃት?? እነ ሃብታሙ አያሌው በእስር እና በህመም የተሰቃዩባትን ሃገር መናፈቅ …. ለኔ ጥፋት ነው:: ቤተ ክርስቲያን እንደ ጠጅ ንግድ አዋጭና አትራፊ የሆነችባትን ኢንቨስተር ቄስ አቅፋ የምትይዝ ሃገር ስለምን ሲባል ትናፍቀኛለች?? እልፍ አእላፍ ልጆችዋ ጎዳና ተዳዳሪ የሆኑባት… ደካማ እና ጧሪ አልባ ሽማግሌዎች ለማኝ የሆኑባት …. ህፃናት ወላጅ እና ጥግ አልባ ርሃብተኛ የሆኑባት ሃገር እንዴት ትናፈቃለች?? ለስኳር… ለዳቦ.. ለዘይት… ለጨው… ለታክሲ በመሰለፍ በየቀኑ የእድሜያችን ግማሽ የሚባክንባትን ሃገር መናፈቅ ቅንጦት ነውና አልቀናጣም- አልናፍቅም! ዝዋይ ቤቴ ሳድር የእስረኛ ግርፋትና የጣር ለቅሶ የምሰማበት…. ጠላ ቤት ገብቼ የምፈልገውን ሙዚቃ የማልሰማበት…በፈለግሁበት ሰአት ያሻኝ ቦታ በኢትዮጵያዊነቴ የማልገኝባት…. ሃገር መቼውንም አይናፍቀኝም!! ባይሆን እነዚህ ሁሉ ጎዶሎዎቿና ስብራቷ ተጠግነውላት ድሮሮሮሮሮሮ የማውቃት እንግዳ ተቀባይ የነበረች ሃገሬን…. የህዝቦች እኩልነት የሃገር ሉአላዊነት የዜጎች ነፃነት የሚከበርባት ሃገሬን ካለሁበት ሆኜ ይህን ትውፊቷን ያጠፉባትን ጠላቶቿን እታገልላታለሁ!! ለዚህም የማከፈለውን መስዋእትነት ልከፍልላት በልጄ ምዬ ቃል ገብቼላታለሁ!! የቀድሞ ማንነቷ ሲመለስ …. ሃገሬ እሄዳለሁ!! ያኔኔኔ ትቻት ብመለስ ናፍቆቱን አልችለውምና እዚያው እቀራለሁ!!
… ኢትዮጵያያያያ ሃገሬሬ
ባንቺ አይደል ወይ ክብሬሬሬሬሬሬ!!
እልላታለሁ!!! በዚያ ደስታ ይኖራል! በዚያ ወገን ቤተሰብ ጏደኛ ጎረቤት ዘመድ አዝማድ አውዳመት ልዪ ስሜት ይፈጥራል! ይሄን ማየት እናፍቃለሁ!!!! ይህቺን ሃገሬን ለማየት እናፍቃለሁ:: ልጄ በየቀኑ ኢትዬጵያን እንዳሳየው ይለምነኛል… ይቺ ናት ሃገሬ የምላት ሃገር ስለሌለችኝ ጥያቄው ያሳምመኛል…. ልጄ እጅግ ያሳዝነኛል::

ከሶሻል ሚዲያ(ፌስ ቡክ)

Filed in: Amharic