>

ከኮሎኔል መንግሥቱ ውጭ ሁሉም ሌባ...... (ኤርሚያስ ቶኩማ)

Mengistu Hailemariam by Tamiru Gedaከሃይለስላሴ ጀምሮ እስከህወሃት ድረስ ባሉት 3 ስርአቶች ውስጥ በሙስና ያልተዘፈቀ መሪ ቢኖር ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ ነው።ኃይለሥላሴ የወሎ ህዝብ በረሃብ ሲማቅቅ እርሱ የህዝብ ገንዘብ ዘርፎ ስዊዝ ባንክ ያጠራቅም ነበረ፤ አሁን ላይ ኢትዮጵያን የወረሩት የህወሃት መሪዎች ደግሞ በመላ ኢትዮጵያ እንደተራበ ጅብ ተሰማርተው ኢትዮጵያን እንደፈለጉት እየዘረፉ ይገኛሉ። ሌብነታቸውን ለመደበቅ ሲሉ ግን የህወሃት አባል ያልሆኑ ተራ የቢሮ ሠራተኞችን በማሰር ህዝቡን ለማሞኘት ቢሞክሩም እውነታውን ሁሉም ያውቀዋል፤ ከ25 አመት በፊት በረባሶ አድርጋ ጫካ ውስጥ የነበረችው አዜብ መስፍን ዛሬ ላይ ቢሊየነር ስትሆን ከየት አመጣችው ያላለ ፍርድ ቤት፤ ከ25 አመት በፊት ጫካ የነበረው ኮሎኔል አወል ዛሬ ላይ ደደቢት የተባለ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት ሲሆን ገንዘቡን ከየት አመጣኸው ያላለው ፍርድ ቤት ዛሬ የህግ ጠበቃ ነኝ ሲል መስማት እውነትም ያስቃል። ህወሃቶች ሙስናን የመታገል አቅሙም ሆነ ፍላጐት የላቸውም ምክንያቱም ሁሉም ሌባ ሁሉም ሙሰኛ ናቸውና።
ከላይ እንደጠቀስኩት በቅርብ ከነበሩት የኢትዮጵያ መሪዎች ሁሉ በህወሃቶች አይነት ሌብነት ያልተሳተፈው ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ ነው። ኮሎኔል መንግሥቱ በራሱ አንደበት በገነት መጽሐፍ ላይ ስለሙስና ሲያወራ እንዲህ ይላል

<<ከኢትዮጵያ ስወጣ አደለም ገንዘብ ልይዝ ቀርቶ … ከፈለግሽ አሳይሻለሁ ይዤ የወጣሁትን:: በትረ መኮንኔንና የደንብ ልብስ ላይ የደረብኩትን የሚሊታሪ ጃኬት ብቻ ነው ይዤ የወጣሁት:: ከኢትዮጵያ ስወጣ ብቻዬን አይደለም የወጣሁት:: አብረውኝ የነበሩ ሰዎች ገንዘብ ጭኜ ወጥቼ እንደሆነ መመስከር ይችላሉ:: ራቁቴን ነው የወጣሁት:: የገንዘብ ሰው ብሆን ኖሮ ያንን በመሰለ ቀውጢ ጊዜ ሳይሆን 17 ዓመት በስልጣን ላይ በነበርኩበት ወቅት የፈለገኝን ማድረግ እችል ነበር:: ሀገሬን ለመልቀቅ ከመገደዴ ጥቂት ሳምንታት በፊት የኩዌት መንግስት በስሜ ለግሌ የላከውን 20 ሚሊዮን ዶላር ትቼ ነው የወጣሁት:: ከዚያ ጥቂት ዓመታት ቀደም ሲል የሊቢያው ኮሎኔል ጋዳፊ አሁንም በስሜ የላከውን 150 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አድርጌ ላገር ግንባታ ውሏል:: እኔ ለአገሬ ገንዘብ አምጪ እንጂ ገንዘብ ዘራፊ አይደለሁም:: የባዕዳን ፊት እንደ እሳት እየገረፈኝ ከውጪ እርዳታ እየለመንኩ እያመጣሁ ነው ለግብርና ለኢንዱስትሪ ለማዕድን ሲውል የነበረው:: ስምንት ቢሊዮን ሩብል አልከፈልንም:: ከብዙ ሶሻሊስት አገሮች የመጣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አልተከፈለም:: በነጻ ብር እያመጣሁ ላገር ልማት ያዋልኩኝ ነኝ ነን:: በዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስክር ነው አይጠረጥረኝም:: እኔም ሆንኩ በመንግሥት ሥልጣን ላይ የነበሩ ጓዶቼ በዘረፋ አንታማም:: ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ይመሰክርልናል:: ወያኔዎች እንደራሳቸው ስለሚመስላቸው የፈለጋቸውን ሊያወሩ ይችላሉ:: እነሱ በባዶ እግራቸው መጥተው ዛሬ ባለማርቸዲስ ናቸው:: በቁምጣ መጥተው ዛሬ ሚሊየነሮች ናቸው:: የነሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ታምራት ላይኔ የመንግስት ካዝና ውስጥ እጁን ከቶ ሳይርመጠመጥ ጥቂት አመታት እንኳ መቆየት አልቻለም:: ሌሎቹም ያው የምናያቸው ናቸው:: ዛሬ እኔ እነሱ በግራና በቀኝ ለሚወረውሩት የጠላ ቤት ክስና ጫጫታ ደንታም ጆሮም የለኝም:: ሕዝቡ አሳምሮ ያውቀናል::>>
የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የሞቶ መኖር መፅሀፍ ደራሲ ኮሎኔል ደበላ ዲንሳ ስለኮሎኔል መንግሥቱ ከሙስና ፅዱነት ሲገልፁ
<<መንግሥቱ ሊመሰገንባቸው ከሚገባው በርካታ ጐኖቹ  በኔ አስተያየት አንዱ በሙስና አለመዘፈቁ ነው:: አምስት ሳንቲም አይፈልግም ነበር:: የገንዘብን ትርጉም የሚያውቀውም አይመስለኝም:: ለራሱ ምቾትም ጨርሶ ደንታ የሌለው ሰው ነበር:: ሌላው ቀርቶ ቤተመንግሥት ውስጥ የርሱ መኖሪያ እንዲሆን ተብሎ የተሰራው ቤት እንኳ እሱ በስራ ጉዳይ ለረጅም ጉብኝት ወደ ውጭ በሄደ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ቶሎ ተሰርቶ ያለቀ ነበር እንጂ እሱ እያለ እንግዳ ሲመጣ እስከሚያሳፍር ድረስ ቤተመንግሥት ውስጥ በሚገኝ ባለ አንድ ክፍል ተራ ቤት ውስጥ ነበር የሚኖረው:: ከቤተመንግሥት ውጭ ቤተሰቡ ጋር ይኖርበት የነበረውም ያው የቀበሌ ቤት ውስጥ ነበር:: እስከማውቀው ድረስ ንብረቴ የሚለው አንድም ቁስ አልነበረውም>>

Filed in: Amharic