>
5:13 pm - Wednesday April 19, 8367

ለእቴጌይቱ ሀውልት

“አዲስ አበባ የሴት ሀውልት የላትም
አዲስ አበባ ለመሥራቿ እቴጌ ጣይቱ ሀውልት ልታቆም ይገባል!”

LTV እንሂድ ከመቲ ጋር
***
ታሪክ
empress-taytu-betul-in-le-petit-journal-of-march-1896አዲስ ፡ አበባ ፡ ተብላ ፡ የተሠየመችው ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ ኅዳር ፲፬ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፸፱ (1879) ፡ ዓ/ም ፡ ፍልውሃ ፡ ፊል-ፊል ፡ ወደሚልበት ፡ መስክ ፡ ወርደው ፡ ሳሉ ፡ ከዚህ ፡ በፊት ፡ አይተዋት ፡ የማያውቋት ፡ አንዲት ፡ ልዩ ፡ አበባ ፡ አይተው ፡ ስለማረከቻቸው ፡ ቦታውን ፡ ‹‹አዲስ ፡ አበባ!›› ፡ አሉ ፡ ይባላል። አዲስ ፡ አበባ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ዋና ፡ ከተማ ፡ ስትሆን ፡ በተጨማሪ ፡ የአፍሪካ ፡ ሕብረት ፡ መቀመጫ ፡ እንዲሁም ፡ የብዙ ፡ የተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ድርጅት ፡ ቅርንጫፎችና ፡ ሌሎችም ፡ የዓለም ፡ የዲፕሎማቲክ ፡ ልዑካን ፡ መሰብሰቢያ ፡ ከተማ ፡ ናት። ራስ-ገዝ ፡ አስተዳደር ፡ ስላላት ፡ የከተማና ፡ የክልል ፡ ማዕረግ ፡ ይዛ ፡ ትገኛለች። አብዛኞቹን ፡ የሀገሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ የሚናገሩ ፡ ክርስቲያኖች ፡ እና ፡ ሙስሊሞች ፡ የሚኖሩባት ፡ ከተማ ፡ ናት። ከባሕር ፡ ጠለል ፡ በ2500 ፡ ሜትር ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ የምትገኘው ፡ ከተማ ፡ በግምት ፡ 2,757,729 ፡ ሕዝብ ፡ የሚኖርባት ፡ በመሆኗ ፡ የሀገሪቱ ፡ አንደኛ ፡ ትልቅ ፡ ከተማ ፡ ናት።

ከተማዋ ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ በመረጡት ፡ ቦታ ፡ ማለትም ፡ በፍል ፡ ውሐ ፡ አካባቢ ፡ ላይ ፡ በባላቸው ፡ በዳግማዊ ፡ ምኒልክ ፡ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ፡ ተቆረቆረች። የሕዝቧ ፡ ብዛት ፡ በያመቱ ፡ 8% (ስምንት ፡ በመቶ) ፡ እየጨመረ ፡ አሁን ፡ አራት ፡ ሚሊዮን ፡ እንደሚደርስ ፡ ይገመታል።

ከእንጦጦ ፡ ጋራ ፡ ግርጌ ፡ ያለችው ፡ መዲና ፡ የአዲስ ፡ አበባ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ መገኛ ፡ ሆናለች። ይህም ፡ በመስራቹ ፡ የቀድሞው ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ ስም ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ ይባል ፡ ነበር።አዲስ ፡ አበባ ፡ ተብላ ፡ የተሠየመችው ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ ኅዳር ፲፬ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፸፱ (1879) ፡ ዓ/ም ፡ ፍልውሃ ፡ ፊል-ፊል ፡ ወደሚልበት ፡ መስክ ፡ ወርደው ፡ ሳሉ ፡ ከዚህ ፡ በፊት ፡ አይተዋት ፡ የማያውቋት ፡ አንዲት ፡ ልዩ ፡ አበባ ፡ አይተው ፡ ስለማረከቻቸው ፡ ቦታውን ፡ ‹‹አዲስ ፡ አበባ!›› ፡ አሉ ፡ ይባላል። አዲስ ፡ አበባ ፡ የኢትዮጵያ ፡ ዋና ፡ ከተማ ፡ ስትሆን ፡ በተጨማሪ ፡ የአፍሪካ ፡ ሕብረት ፡ መቀመጫ ፡ እንዲሁም ፡ የብዙ ፡ የተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ድርጅት ፡ ቅርንጫፎችና ፡ ሌሎችም ፡ የዓለም ፡ የዲፕሎማቲክ ፡ ልዑካን ፡ መሰብሰቢያ ፡ ከተማ ፡ ናት። ራስ-ገዝ ፡ አስተዳደር ፡ ስላላት ፡ የከተማና ፡ የክልል ፡ ማዕረግ ፡ ይዛ ፡ ትገኛለች። አብዛኞቹን ፡ የሀገሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ የሚናገሩ ፡ ክርስቲያኖች ፡ እና ፡ ሙስሊሞች ፡ የሚኖሩባት ፡ ከተማ ፡ ናት። ከባሕር ፡ ጠለል ፡ በ2500 ፡ ሜትር ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ የምትገኘው ፡ ከተማ ፡ በግምት ፡ 2,757,729 ፡ ሕዝብ ፡ የሚኖርባት ፡ በመሆኗ ፡ የሀገሪቱ ፡ አንደኛ ፡ ትልቅ ፡ ከተማ ፡ ናት።

ከተማዋ ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ በመረጡት ፡ ቦታ ፡ ማለትም ፡ በፍል ፡ ውሐ ፡ አካባቢ ፡ ላይ ፡ በባላቸው ፡ በዳግማዊ ፡ ምኒልክ ፡ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ፡ ተቆረቆረች። የሕዝቧ ፡ ብዛት ፡ በያመቱ ፡ 8% (ስምንት ፡ በመቶ) ፡ እየጨመረ ፡ አሁን ፡ አራት ፡ ሚሊዮን ፡ እንደሚደርስ ፡ ይገመታል።

ከእንጦጦ ፡ ጋራ ፡ ግርጌ ፡ ያለችው ፡ መዲና ፡ የአዲስ ፡ አበባ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ መገኛ ፡ ሆናለች። ይህም ፡ በመስራቹ ፡ የቀድሞው ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ ስም ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ ይባል ፡ ነበር።

Filed in: Amharic