>

‹‹እምነት አይሸጥም!›› (ጎሳዬ ተስፋዬ) :- ይድረስ ለኢትዮጵያውያን

‹‹እምነት አይሸጥም!›› 

– ጎሳዬ ተስፋዬ

ይድረስ ለኢትዮጵያውያን

በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ የምትገኙ የስራዬ አድናቂዎች በሙሉ ይህን ግልፅ የሆነ መልእክቴን ከአክብሮት ጋር ወደናንተ ይደርስልኝ ዘንድ እወዳለሁ::

Artist Gosaye Tesfayeኢትዮጵያዊነት ማለት ከአባቶቻችን የወረስነው ጀግንነት; ጨዋነት; እርስ በእርስ መከባበርና መዋደድ ነውና ዛሬም ከዚህ ማንነት ተካፋይ በመሆኔ የሚሰማኝ ደስታ ወደር የለውም::

ዛሬ ዛሬ እራሳችን በምንፈጥራቸው የሀሳብ ልዩነቶችና ያለመግባባት ችግሮች ሲያጋጥሙን ተወያይተንና ተከባብረን ጉዳዩን በመፍታት ፈንታ ብዙሀኑ ህዝብ በሚጠቀምባቸው ድረገፆች ላይ የተዛባ መልእክቶችን ማስተላለፍ የተለመደ ሆኗል!!

እንደሚታወቀው በያዝነው አመት የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ላይ ሙዚቃዎቼን ለማቅረብና ከአድናቂዎቼ ጋር ለመገናኘት ዝግጅቴን አጠናቅቄ በስፍራው የተገኘሁ ቢሆንም በጥቂት ግለሰቦች ፍርደገምድል ውሳኔና ጫና እንዳሰብኩት ከአድናቂዎቼ ጋር ሳልገናኝ ቀርቻለሁ::

በዛ ሰአት በተፈጠረው የአድናቂዎቼ መጉላላት ከልብ ባዝንም በሶሻልሚዲያ ላይ ወጥቼ እሰጥ-አገባ መመላለሱ ስብእናዬና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አስተዳደጌ ስለማይፈቅድ ብዬ ዝምታን መርጬ የነበረ ቢሆንም , እየተላለፈ ያለው የተዛባ መልእክትና የእናንተ የአድናቂዎቼ ፍቅር ; አክብሮትና ; የማበረታታት መልእክቶቻችሁ ይህንን እንድፅፍ አስገድዶኛል!!

የዚህ አይነቱ የተሳሳተ የስም ማጥፋት ዘመቻ በኔ ላይ ሲፈፀም ኢሄ የመጀመሪያው አይደለም ከዚ በፊትም በሀይማኖት ጉዳይ የተሳሳተ ነገር ተነስቶብኝ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሄር ፈቃድና በእናንተ አድናቂዎቼ ድጋፍ እንደተወጣሁት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው!!

ዛሬም ከእውነት ጎን ቆማችሁ ፍቅራችሁንና ድጋፋችሁን በተለያዩ ድረገፆችና በግል ኢሜል በሜሴንጀር ከጎኔ ቆማችሁ ወገናዊነታችሁን ላደረሳችሁኝ አድናቂዎቼ እና ለእምነታችሁ ያደራችሁ ጋዜጠኞችና ጦማርያን ስለሁሉም ነገር ልባዊ ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ!!!

አሁንም ቢሆን እኔ አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬ ከምንም ነገር የፀዳሁ ; በኢትዮጵያዊነቴ የማልደራደር ; እግዚአብሄር በሰጠኝ ፀጋ በሙያዬ ህዝቤንና ሀገሬን እንደማገለግል ቃል እየገባሁ እሰናበታለሁ::
እምነት አይሸጥም!!!!

ጎሳዬ ተስፋዬ

***
ጎሣዬ የተናገረው በቂ ነው። ሁሉም ዘፋኝ ጃ- እንዲያስተሰርይለት ከጠበቅን ችግር ነው። ሁሉም እንደመክሊቱ ነው። ሁሉም ሰው እኔን ይሁን ማለት አልችልም።

ግማሹ ተቃውሞን እራሱ ዝና ማሟሟቂያ አርጎታል። እነ አስቴር፤ እነ ጎሣዬ የኮንሰርቱን ቦታ፤ ቀኑንና ክፍያውን ከ6 ወር በፊት ተነጋግረው ይጨርሱና የስፖንሰሩን ማንነት ፖስተር ሲወጣ ነው የሚያውቁት። በርግጥ ከአሁን በኋላ ውሉ ውስጥ የሚገባም ይመስለኛል።

ዋናው ነገር ግን… ለኔ… በአንድ ዘፋኝ መኖር የለብንም። አንዱን ለማስደሰት ሌላውን ማሳደድም ልክ አይደለም።

እኔ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅር የምንዘምርላትን ኢትዮጵያ ፍለጋ ላይ ነኝ። ያ ደግሞ የሚሆነው በማስተዋል ነው።

እኔ በሃገር ጉዳይ ላይ ያለኝን አመለካከት ሁሉም ያውቃል። ለነሱም ስከራከር ምክንያት ይዤ ነው። የሃይማኖት ድርጅቶች አባል ለማብዛት እንዴት እንደሚተጉና እንደሚደልሉ ታውቁ የለ?! ምነው የናንተው የተገላቢጦሽ ሆነ?!።

አብራሃም ወልዴ( ባላገሩ)

Filed in: Amharic