>
5:13 pm - Monday April 18, 1104

ማራኪ (ስዊድን)

ይድረስ ላንተ ለወገኔ..
ግማሽ አካሌ ጎኔ..
ይድረስህ መልክቴ ላንተ…
መቼም ዝም እትልም ሰምተ…

በጭካኔ ሲፈርዱብኝ…
ጨለማ ቤት ሲዘጉብኝ…
ስብእናዬን ሲገፉብኝ…
ምነው ዝም እልካቸውና ተውከኝ..

ጨርቄን ገፈው ቀደው…
ፀጉሬን ጎትተው ነጭተው…
ሲተፉብኝ ሲቀልዱ…
ሴትነቴን ሲያዎርዱ…
እኮ የታለ ወንድሜ ውዱ..
ደም መላሼ ወንዱ…

እርቃን ገላዬን አራቁተው…
ሲሳለቁ ተስብስበው…
ለምንድነው ዝም ያልከው…

ወጣትነት ሴትነቴን…
ተፀይፈው ማንነቴን…
ሲያጣጥሉ ክብሬን…
አላወቁት ደሜን..

አንገት ደፍቼ ሳለቅስ…
ስሜ ሲረክስ…
እስቲ ማንን ልውቀስ…

ፆታ ክብሬን ሲደፍሩ…
እኔን ንፁህ ኩሩ..
ምነው ዝም አለኝ አገሩ…

ስም አውጥተው ያለስሜ…
ሲሳለቁብኝ በቁሜ..
የታለህ ወንድሜ..

አበባዬን ሲቀጥፉ..
ውበት ቁንጅናዬን ሲያጠፉ..
እንዲ ሲበዛ ግፉ..
ምነው ጎበዛዝቱ ጠፉ..

ስሞታዬን ሰምታቹ..
አለን በሉኝ እባካቹ..

ጥሩልኝ የጋይንቱን ጀግና..
ከጎበዞቹ ቀጠና…
እንዴት ልግባ ልመና..

የአርማጭሆ ቆላ ዲባ ጎርጎራ…
ጥቃቴን ስማልኝ አዘዞና ቋራ…
ወንዶቹን ጥሩልኝ በተራ..
እንዴት ይድፈረኝ ኩታራ…

እኮ እንዴት…? እንዴት…?

Nigist Yirgaየ24 አመቷ ወጣት ንግስት ይርጋ በጎንደር በተደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ ተሳትፈሻል በሚል ሰበብ በ ሃምሌ ወር 2008 እስር ቤት ከተወረወረች በሃላ በሴትነቷ በደረሰባት መከራና ግፍ የደረሰባትን ጥቃት በማሰብ የድረሱልኝ ድምፆን እያሰማች ነውና መታሳቢያነቱ ለእህቴ ይሁንልኝ

Filed in: Amharic