>

ማሳሰቢያ ለቪኦኤ! (ምንሊክ ሳልሳዊ)

tesfaye-gebreebab-on-voaየአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ተስፋዬ ገብረአብ የተባለውን ከፋፋይና ፀረ ኢትዮጵያ ስራ የሚሰራውን እርጉም የገንጣይ አስገንጣይ ሐዋርያ አምጥቶ መርዙን እንዲረጭ ቀጠሮ ይዞለታል ። እኛ የናፈቀን አንድነት ፣ ፍቅር ፣ መቻቻል የሚሰብክ ብሔራዊ እርቅ የሚያመጣ በሳል ሰው ነው የምንፈልገው ። አሜሪካ ሬዲዮ ውስጥ ያሉ የጃጁ ጋዜጠኞች ሐገርን ከማደፍረስ አይመለሱም ። እነሱ የአሜሪካ ዜግነት ስለወሰዱ ስለ ኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ደንታ ቢስ ናቸው ። ሲላቸው ቤተክርስቲያን የሚበጠብጡ ሲላቸው እስልምናን አሸባሪ ብለው የሚያጠለሹ ሚዲያዎች ከቆዳቸው ይልቅ እምሯቸው ተሸብሽቦ ሐገርን ለመበታተን የዘመቱ የሻእቢያ እና ወያኔ ተላላኪዎችን እንድናጫውትላቸው ይጋብዛሉ ። ተስፋዬ ገብረዓብ ማለት ሕዝብ ለሕዝብ ለማጋጨት የሚሰራ የኢትዮጵያን መከፋፈል የሚፈልግ በጸረ ኢትዮጵያውያን የሰለጠነ የሻእቢያ ጸረ ኢትዮጵያ ክፍል ዋና አስፈጻሚ የሆነ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያጠለሽ እጅግ አደገኛ የሆነ ኤርትራዊ ግለሰብ ነው። ይህን ግለሰብ እንግዳ ማድረግ እናንተም ሌላኛው የጸረ ኢትዮጵያ አካል መሆናችሁን ይጠቁማል። ይህቺን አገርና ሕዝቧን ገደል ለመክተት ከሚሯሯጡ ድኩማኖች መካከል መገኘታችሁን እያሳያቹ ነው።

Filed in: Amharic