~ ችግሩ ሲፈጠር አንተ የት ነበርክ?
~ ከጓደኞቼ ጋር እየተጫወትኩ ነበር፣ ቆሼ ላያችን ላይ ወረደብን።
~ አንተን ማን አወጥህ ከዛ?
~ ራሴ እየሮጥኩ /በጣፋጭ የልጅ አንደበት/
(የኢዩኤል አስታማሚ አክስቱ ናት። በመሃል ገብታ እንደተናገረችው ለእሱ አልተነገረውም እንጂ ወላጅ እናቱና እህቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል)
====
ሌላዋ ተጎጂ ምልዕተ ደበበ ትባላለች። እዛው አለርት በህክምና ላይ ትገኛለች።
~ በወቅቱ አንቺ የት ነበርሽ?
~ ቤቴ፣ ከቤተሰቦቼ ጋር ••• አደጋው ሲፈጠር ህፃኗን ልጄን ይዤ ልወጣ ስል አፈሩ ተጫነኝ።
~ ማን አወጣሽ?
~ ሰዎች ናቸው ቆፍረው ያወጡኝ።
~ ቤተሰቦችሽስ?
~ የት እንዳሉ አላውቅም።
~ ባለቤትሽ ምን ነበር ስራው።
~ በየቤተክርስቲያኑ እየሄደ ጧፍ ነበር ሚሸጠው።
~ ልጆችሽ ስንት ናቸው? ዕድሜያቸውስ?
~ አንዷ 7 አመት ከ8 ወር አንዷ ደግሞ 1 አመት ከ7ወር
(ከምልእተ አጠገብ ያሉ ሰዎች ለጋዜጠኛዋ እንደነገሯት እሷ ከህመሟ ስላላገመች አልተነገራትም እንጂ ባለቤቷም፣ ሁለቱም ልጆቿም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። አስከሬናቸው ተገኝቶም ተቀብሯል)
•
አህ!••• ልብ ያደማል!!
በህይወት ያጣናቸውን ወገኖች ሁሉ ነፍስ ይማር!!
ቪኦኤ ከሰዓታት በፊት [በጋዜጠኛ ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን]
Filed in: Amharic