>

የሳምንቴ ትዝብትና ትንግርት! [አስፋ ጫቦ]

Corpus Chirsti ,Texas USA

Ato Assefa Chaboአሜሪካ ዛሬም በሁለንተናው ግምባር ቀደም ነኝ ስለምትል(“ያማ ያለፈ ወሬ ነው! የሚሉ ሞልተዋል) በፕሬዚዳንቱ፤ በዶናል ትራምፕ፤ ልጀመር።”የኔ ጠላት የአሜሪካን ህዝብ ጠላት ነው” “They are not my enemies but the enemy of the American people) ብሎ አረፈው።
የፈረንሳይ ንጉሥ የነበውን ልዊ 14ኛውን አስታወሰኝ።”ፈረንሳይማለትእኔነኝ!”አለ! L’Etat est Se Moi! ጠላቴ የሚለው የህዝብ መገናኛውን እንዳለ ነው።አንድ ሁለት በራሱ ቅጥረኛ የሚታተሙና አንድ የማይሆን ዜና አቀባይ የሆነ ቴሌቪዥን ጣቢያ፤Fox፤ ከዚህ ውስጥ አስወጥቷል። “አርብ ማታ ሲውዲን የደረሰው አደጋ !” አለ። ሲውዲኖቹ “እንዴት እኛ ሳናይ፣ ሳንስማ ትርምፕ ሰማ !”አሉና አሽሟጠጡትቱ። ይህንን ዜና ያገኘው ከFox ነበር።
ጣላቴ የሚለውን መገናኛ ብዙኅን ነበር::አሜሪካኖቹ አራተኛው የመንግስት ዘርፍ ይሏቸዋል።The Fourth Branch of Government! ሶስቱ ያው የታወቁት ህግ አመንጭ ፤ሕግ ተርጓሚና ህግ አስፈጻሚ የሚባለው ነው። ትራምፕ እንግዲህ እልቅናው ለዚህ ለፈጻሚው ክፍል ነው። ፈጽም ተብሎ የተሰጠውን!!
“አንድ እስላም ድርሽ አንዳይልብን!” ብሎ ያወጣውን ህግ አንድ የፌዴራል ዳኛ አቀበው። የትራምፕ ሰዎች ይግባኝ ብለው ወደሚቀጥለው ፍርድ ቤት ሲሔድ ይግባኝ ስሚው ፍርድ ቤት” ይግባኝ አላችህ እንጅ
Page 2 of 6

ለምን ይግባኝ ስለአላችህ ልታስረዱን አልቻለችሁም “ብለው ያንኑ የታችናውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አጸደቀ። ከዚያ ትርራምፕ ዳኞቹን “ዳኛ ተብዬ!” ብሎ ዘለፋቸው፣።
እንደልቡ ተነጋሪ ነው? ዘረጦ ነው ማለት ሳይሻል አይቀረም!የአሜሪካንን መንግስት ሥርአት ሀ ሁ ሳይውቅ እንዴት እንደተመረጠ አሁን መጠየቁ “ጅብ ከሔድ ውሻ ጮኸ!” እንደማለት ነው። ከሁለት ወር በፊት “በማግስቱ!” ብዬ በሳጻፍኩት በመጠኑ አንስቻለህ። ። የአሜሪካን መንግስት ሥርአት “ሀ ሁ” መንግስት በሶስት ቅርንጫፍ ይከፍላል የሚለውን ያለሰማ መሆኑ ነው። አራተኛው ቅርንጫፍ የሚባለው “የህዝብ መገናኛ” Mass Media ሶስቱንም ሲያበጁ “አበጀህ !”ሲያጠፉ” አጠፋህ!” ፤ሲማግጡ “ማጋጥክ!” የሚለው ነው። ትራምፕአልስማ ሆኖ እንጅ ይህ ነገር ወደ 300 አመት ሊሆነው ነው።የኢትዮጵያ ጠርን አለው ልበል?
“ኤረ ወየው ወየው! መጨረሻውን ላየው!” ይላል የኛ ሰው። የትራምፕ መጨረሻው ምን ይሆን?

********

በቨይታምን ጦርነት ዘመን የተሰለፈውን ያክል የአሜሪካ ህዝም በየግዛቶቹና በየከተማዎቹ ሁሉ ይስለፈላል።ትላንትን የፕሬዝዳንቶች ቀን (Presidents Day)ተብሎ በሚከበረው ለት ሕዝብ በገፍ ወቶ ተሰለፈ። የያዙት መፈክር ይናገራል! “Dump Trump! ያላል አብዛኛው። “ትራምፕን ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ወርውረው!” እንደማለት ነው። ሌላው “የኔ ፕሬዚዳንት አይደለም !” (Not My President! የሚል ነው። ይህ እንግዲህ የአሜ ሪካ ህዝብ ነው። ትራምፕ ደግሞ የኔ ጠላት ሁሉ የአሜሪካ ህዝብ ጠላት ነው ብሏል። ቀርብ ብለው ሲተርጉሙት፤የአሜሪካ ህዝብ ጠላቴ ነው እንዳለ የሚያስቆጥር አንድምታ ያለው ይመስለኛል።ሕዝቡ ነዋ “ወግድልን!”የሚለው።
የትራምፕ መጨረሻ ተንታኞች ሁለት አማራጭ እይታ አሏቸው። አንዱ በቅርቡ ይወጋዳል (Impeached)የሚል ነው። ይህ የተጧጧፈው የሕዝብ አመጽ ወደዚያ ያመራል በሚል ነው። ሁለተኛው አማራጭ የመንፈቁን ምርጫ (Mid Term Election) መጠበቅ ነው። ለአሜሪካ ምክር ቤት በየሁለት አመቱ መርጫ ይደርጋል ፤ በዚህ መርጫ ዴሞክራቶቹ የላይኛናውንም የታችናኛውንም ቤት (Senate and House) መቀመጫ የሸናፋሉ። በአሸናፉ ማግስት መጀመሪያ የሚያረቁት ሕግ የትራምፕን ማሰወገጃ ሕግ (Impeacheament) ነው ይላሉ። የዚያ ሰው ይበለን!
ትራምፕ በእንግሊዝኛው ሲጻፍ ሁለት አጻጻፍ ለው። አንደኛው በ u ሌላው በ a ። በ a የሚጻፈው ትራምፕ Tramp “አልባሌ ፣ማጋጣ …”እንደማለት ነው። “እርግጠኛ ስሙ ይኸኛ ይሆን” የሚያሰኝ ነገር ያመጣብኛል።የአንጎል ጅምናስቲክ mental acrobatics መሆኑ ነው።
*****
ከዚህ ከአለም ጉዳይ ሳንወጣ ፤ግሬስ ሙጋቤ፤የዚምባበዌው ፕሬዚዳንት የሮበርት ሙጋቤ ባሌቤት ስለባሌቤትዋ የሰጠችው አስትያተትና በአደባባይ የተናገርችው ነው። “አይበለውና ሙጋቤ ሞቶ ተቀብሮ

Page 3 of 6

እንደገና ከመቃብሩ ተነስቶ ቢመጣም የዚምባብዌ አ ህዝብ በደስታ ይመርጠዋል!” አለች። ለሚቀጥለው የፕረዝዳንትና ምርጫ ሊገቡ ያሰቡትን “አትቋምጡ! አታገኟትም !”ለማለት ፈልጋ ነው።
ሙጋቤ አሁን 92 አመቱ ነው። ሥልጣን ላይ ደግሞ 37 አመት ሆኖታል። ባሌቤቱ እድሜዋ 51 አመት ነው። ብዙ ነገር አሳሰበኝ። አንዱ አሪት ውስጥ የአይሁድ ንጉስ የነበረውን ዳዊትን ነው። ከጠነዛ አልጋ ላይ ከዋለ በኋላ ወጣት ሚስት እየተፈለገ አብሮት እንዲተኛና ሙቀት እንዲስጠው ይደርግ ነበር ይላል መጽሐፉ። ይህ ሁሉ ታስቦ ቅዱስ ዳዊትም ተብሏል።
ግሬስ ሙጋቤ” አትቋምጡ!” ስትል መልእከቱ፤ዋንኛው ምልእክት ፣”አልጋ ወርሽ እኔ ነኝ !”ለማለት ነው። ድፍረቱ፤ የሕዝብ ንቀቱ፤ ፕሬዚዳንት መባሉ፤ሬፑብሊክ መባሉ ሁሉ ይደነቀኛል።
*****
ሶስተኛናው፤በሳምንቱ ውስጥ ከገርመኝ አንዱ የሰሜን ኮሪያው “ንጉስ “ሥራ ነበር። ንጉስ ያልኩት ማእረጉን ሁሌ መሪ (The Leader)ስለሚሉ ነው። በዚህ ላይ ከቅደመ-አያቱ ጀመሮ “ዘውዱ” ከዚያ ቤት አልወጣምና ነው ።
ማለዥያ አውሮፕላን ማረፊያ ትልቅ ወንድሙን ያስገድላል። አስተዳደሩ ኋላ ቀረ ነው። አስገዳደሉ ግን ዘመናይ ነበር። ድሮ ኢትዮጵያ ተሌቪዥን ላይ ያየሁትን Candid Camera አስትወሰኝ። ትንሽ ገንዘብ ይከፈሉና ሰው ላይ ሳይስቡ ውሐ የሚረጩ ፤የሚያስረጩ ያንኑ ቪዲዮ ሰርቶ የሚታዳደሩ አሉ። በዚህ አሠራር አንድ ፤ይህንኑ ስትሰራ የነበረች ሴትን “እዚህ ሰውዬ ላይ ውሀ እርጭበት !”ይሏትና ትራጫለች። የአሁኑ ውሐ ሳይሆን መርዝ ነውና ሰውዬ ይሞታል!
“VX’ በሚባል፣የደም ሥር ስተሮ የሚገል መርዝ ነው የገደለው” አለ የምርመራው ውጤት። የተባበሩት መንግስታት ድርጀት VXን ሕዝብን በጅምላ መፈጃ መሳሪያ ነው Weapon of mass destruction ነው ብሎ መድቦታል።
1984 አስታወሰኝ! Big Brother is Watching You! በየአውሮፕላን ማረፊያው የሚጠብቅ CCTV (Closed Circuit Telvision) ካሜራ አለና ሴትየዋም ተካፋዮችም ይያዛሉ። አገር ጠለው የፈረጠጡ አራት ሰሜን ኮርያውያንም እየታደኑ ነው።
ከዚያ በኋላ ያለው ትንሽ ትያትርነት ያለው ይመስላል። የሰሜን ኮሪያ አምባሳደር “አስከሬኑ ይሰጠን! መመርመርም የለበትም!” ይላል። “ የምርመራውንም ውጤት አንቀበልም!” ይላል።ትያትርነቱ እዚያ ላይ ነው። ሟቹ “ምናችሁም አላማረኝም!” ብሎ ተሰዶ ይኖር የነበር ነው። እንደጠላት ያዩትም ስለነበር ነው ያስገደሉት ማለት ይቻላል። አሁን ታዲያ ደርሶ “ቅቤ አንጓች !”መሆናቸ አይገርምም? ወይም የበለጠ አያሰጠረጥርም? ከዚህ ሌላ የተገደለውን ሰው ሬሳው አይመርመርብን ፤ከተመረመረም ውጠቱን አንቀበልም ማለት የበለጠ አያስጠረጥርም? ወይስ የድንቁራንን ደርጃ መግለጫ ነው?
እንዳለኩት ኋላ ቀር ቢሆኑም አገዳደላቸው ዘመናይ ነው። ከዚያ በተረፈ ያለው እውነትኛነት ፤እርግጠኛ ኋላ ቀርነታቸውን መስካሪ ይመስለኛል።

Page 4 of 6

ምስኪን የሰሜን ኮርያ ሕዝብ!! ምኑን ሰጣቸው!! ይሰውረን!!
አሁን በመጨርሻ ገደማ የተደረሰበት መረጃ አስረድ እንደሚባለው፤ይህ የተገደለው የመሪው ትልቅ ወንድም፤ስደተኛው ፤የሰሜን ኮሪያ ስደተኛ መንግስት መሪ እንዲሆን በሌሎች ስደተኞች በተለይም አውሮጳና አሜሪካ በሚኖሩር ተጠይቆ ነበር። ይህ ይሆናል ቃታውን ለመሰባ፤ይቅርታ መርዝ ለመርጨት ዋና ምክንያት የሆነው ይላሉ ውስጥ አዋቂ ተንታኞች ነን የሚሉ።
****
አሁን ደግሞ ወደቤተሰብና ወደማሕበራዊ መገኛኛዎች በተለይም ወደ Facebook ልመለስ።
Facebookትምህርት ቤት ሆናኛል ያልኩኝ መስለኝ። ጥሩውን፣ መጥፎንና ጥፉውንም ለማየት መንገድ ይከፍታል።ጥሩ ሲገኝ በርግጥ መነጋግገሪያችን ላይ ሐሳብ፤ቃላት፤አዝማማያ ሊሰጥ የሚችል ይሆናል።ያዳብራልም!ለዛሬ አንድ ካሳ አንበሳው የለጠፈውን እዚህ እንዳለ እለጥፈዋለህ። Kassa Anbessaw · Yesterday at 12:41am · ተክሌ syndrome በሰፊው እያስተዋልኩ ያለሁበት ሁኔታ ነው ያለው፤ ወያኔ ተረስቷል፤ ፌስ-ቡክ በአጼ ሚኒሊክ፣ በቴጌ ጣይቱ እና በአባት አርበኞች ተጥለቅልቋል፤ አባቶቻችን ነጻነቷን የጠበቀሽ፣ የተፈራች እና የተከበረች ሃገር አስረክበውናል፤ ይሄንን ጠብቆ ማቆየት እና እኛም ለልጅ ልጆቻችን የማስተላለፍ ታሪካዊ አደራ አለብን፤ ኑ! ሃገራችንን ከወራሪው ወያኔ ነጻ እናውጣት! ዳይ! ******************************* የግርጌ ማስታወሻ:- <ትክሌ syndrome> እውነታን አሸሽቶ ታሪክ ውስጥ የሚያሸጉጥ የበሽታ ምልክት ነው፤ ይህ በሽታ ጎልቶ የታየው ተክሌ ይሻው ላይ በመሆኑ <<ተክሌ syndrome>> ተብሎ ተሰይሟል
እኔ ግርዳ ላይም አመጥቼ ለጥፌው ነበር።ያለምንም ተጨማሪ አስተያየትና ማዳበሪያ! ይህንን ያነበበ አንድ ወዳጄ ከካናዳ ደውሎ ሳቅ በሳቅ ሆነ። ።”ምነው?” ስለው “ስለዚህ የአማራ መሸጫ ሱቅ ስለአቋቋመው ተክሌ ይሻው እምለው አጥቼ ይህ ሰው አለልኝ” አለ። ሱቅ የሚለው ተክሌ “ምጽአተ አማራ “ የሚል አንዳች የሚያክል መጽሐፍ ጽፏልና ነው። መጽሐፉን እየዞረ የሚሸጠውን ለማለትነው።መጽሐፉን አንድ ወዳጄ ከዋሽንግቶን ዲሲ ልኮልኝ ትንሽ አገላብጬ አስቀመጥኩ። ፈርቼ ያስቀመጥኩት የመጀመሪያው መጽሐፍ መሆን አለበት።
ሁለተኛው፣ትላንት Facebook ላይ የለጠፍኩት እንዳለ ይኸውና:-

Page 5 of 6

Assefa Chabo · “ያጋራ ቤታችን !ቅርሳችን! ውርሳችን!” የሚል ጽሁፍ ጀምሬ ነበር። አልሔድልኝ፣ አላልቅልኝ አለ። ውስጤ የቀረ ነገር አለ ማለቱ ነው ብዬ ተረጎምኩት። በዚያ ምክንያት ከኢትዮጵያ ታሪክ ውጭ ስለሰው ልጅ አብሮ የመኖር ታሪክ ማሰሰ ጀመርኩ። በዚህ አሰሳ Identity Politics የሚል አገኘሁ!” የማንነት ፖለቲክ!” ፓለቲካ ማለት። በዚህ ምክንያት ያገኘዃቸውን 3 ጽሁፎቸ1. Identity Politics are Ripping Us Apart2.Identity Politics Run Amak 3. Identity Politics/Philosophy Talk Facebook ላይ ለጠፍኩ። ዛሬ አራተኛው ይሁን አምስተኛ ቀን ሆኖታል። ዞር ብሎ ያየው በጣት የሚቆጠር ነበር።እኔ ደግሞ ወደ 7,000 ወዳጆች (Friends)አሉኝ። “ወዳጆቼን ምን ነካቸው!” ማለቴ አልቀረም። ከወር በፊት ጣቴተን በድል ምልክት(V) ቀስሬ የተነሳሁትን ፎትግራፌን ለጥፌ እንኳን ወደ 700 የሚጠጋ ሰው ጎብኚቶታል። ለዚህ መነሻ የሆነኝ ዛሬ በተለየ በዲያስፖራ የሚገኙ”የአማራና ኦሮሞ ሊቃውንት ነን” የሚሉ ከኢትዮጵያ ተፋተው ስለመንደራቸውና “ነን!” ብለው ስለሚያስቡት ጎሳ (ሥራዬ ብዬ ብሔረሰብ አላልኩም) ብቻ ያወራሉ። የቀረነውን ኢትዮጵያውያንን “እኛ!”ና “እነሱ!” በሚል ፈርጀውታል። “እኛ!” የሚሉት “ብቸኛ ተጠቂ!” “እንሱ!” የሚሏቸው “አጥቂ!” የኦሮሞ “ምሁራን ነን” የሚሉትማ ኢትዮጵያ የሚል ቃል ራሱ የሚያንገሸግሻቸው ያስመስሉታል። ከኢትዮጵያ ውስጥ የሚጠሩት ቃል ቢኖር “አማራ!” የሚል ቃል ብቻይመስላል። ዛሬ ደጎሞ ይህንን First Peoples የሚል የPBS Utube ይኸው ለጥፊያለሁ። እባካችንእናድምጠው! አድምጡት! ይህኛው ክፍል 1 ስለ አፍሪቃ ብቻ የሚያውጋው ነው። ሌላ 4 ስለቀሩት አሁጉራት የሚያወጋም አለ። እሱንም እንዳምጥ! ዋናው ነገር፤ለኔ ዋናው ነገር፣ ቆም ብለን “ነው እንዴ?!” እንድንል ነው። እይታችን ሰፋ እንዲል ነው! መንጽራችንን እንድንቀይር ነው! በተመዘገበ እውነት ላይ ተመስርተን እንድንወያይ ነው!” የጋራ ቤታችን!” ጉዳይ ስለሆነ የጋር ቤታችን በአክብሮት ጭምር እንድናይ ነው። “ባሌቤቱ የናቀውን አሞሌ ባለእዳ አይቀበለውም!” እንዲሉ PBS First Peoples 2of5 ( Africa ) youtube.com
በማነንት ፓለቲክ ላይ አንበቡ እናንብብ ለማለት ነው።
*****
አሁን ስለቤተሰባችን ትንሽ:-
Page 6 of 6
1. የካቲ፬ 4,2009፤ድሬዳዋ ከተማ ፤ከዚህ አለም የተለየው የትልቁ ልጄ፤ኤፍሬም አሰፋ፣ልጅሊዲያና አብነት ገብረጊዮርጊስ ጋብቻቸውን ፈጽመዋል።እመቤት አስፋ፤እህቴ ግምብነሽ ጫቦ፤ባሌቤትዋ ባልቻ ሙሊሳ ከልጆቻቸውና ከልጅ ልጆቻቸው ጋር ከአዲስ አበባ ተጉዘዋል።ስለሠሰርጉ የሚነግሩኝን ማዳመጥ” አንድ ሽህ አንድ ለሊት”ን The Arabian Night እንደማንበብ ነበር።የሊዲያ እናት ፣ተቀባሽ አንጣል፣ በስልክ ውስጥ ክንፍ አውጥታ የምትበር ነበር የመስለችኝ።እመቤት “አሴ ብችል ድሬዳዋ መኖር እፍልለጋለህ!” አለች። “ምነው?” ስላት “ሰው ሁሉ እንደልጅ ግልጽና ፊት ለፊት ተናጋሪ ነው!” አለችኝ።
ቅድመ አይትነት በሬን እያንኳኳ ነው ማለትነው።
2. ሌላው ከሎንዶን ካትሪን ጫቦ Cathleene Chabo ደውለችልኝ።ተዲ ባለፈው ወር Sandhurst Military Acadamy ገብቷል ለማለት። ተዲ ማለት ቴዎድርስ እሸቱ ጫቦ ማለት ነው። ካቲ የቲድ እናት ነች።
ተዲ Sanhurst Military Acadamy የገገባው ሁለተኛ ድግሪውን (Masters)ከተቀበለ በኋላ ነበር ። “አንዱ አይበቃም ነበር ወይ?” ስለው “ሁለተኛው ሲኖር ጀኔራል ለመሆን ያፋጥናል(accelerate) ብዬ ነው” አለ።
እንግዲህ በጥቂት አመታታ ውስጥ ቴዎድሮስ የሚባል የእንግሊዝ ጀነራል ሊኖር ነው።ለእንግሊዝም፤በተለየ ለኛ ታሪካዊ የሚሆን መስለኝ። መቅደላ አፋፉ ላይ አንድ ሐውልት ተከልን እንደማለት ይመስለኛል ነው።አሁን 150 አመት ሆነው አይደል?
የተሻለ ሳምንት ይጠብቀን!

Filed in: Amharic