>

እፎይታን ያየህ ና ወዲህ በለኝ! [አስፋ ጫቦ Dallas Texas USA]

እንደ መግቢያ
Ato Assefa Chaboዛሬ በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግስት ከተሾሙት 21 ሚኒስቴሮች ውስጥ ስለሶስቱ (3)ለመጻፍ ፍልጌ ነበር። ትዝ ሲለኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለካ መንግስታችን አይደለም ብሏል። እንግዲያውስ “የጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መንግስት” ልበለው አልኩኝ። ቆም ስል ለካ የኃይለ ማርይምም መንግስት አይደለም። የጠቀለለው ነገር የለማ።ለዚህ የሾመባማቸው ሳይሆኑ ያልሾመባቸው ቦታዎች” እዩን! ስሙን!” ብለው በአደባባይ ይናገራሉ። የመከላከያ ሚኒስቴር፤የገንዘብ ሚኒስቴር፤የመገናኛ ሚኒስቴር።፣ የሕዝብ ደህንነት ሚኒስቴር፤የእርሻ ሚኒስቴር አልተነኩም። በነበሩበት ረገትዋል።መንግስት እንደሚያምነውም እነዚህ የሚነስቴር መስርያ ቤቶች “የኪራይ ሰብሳቢዎች!” ጠቅላይ መመርያ ናቸው። ሞተሩም መዘውሩም ያለው እዚያው ነውና። የኪርራያ ሰብሳቢ ማለት መለስ ዜናዊ ያመጣብን የፈረንጅ ቅኔ መሆኑ ነው። ቅኔው ሲፈታ “ዘራፊ!” ማለት ይመስለኛል። ይመስለኛል ያልኩት የተሻለ ትርጉም ካለ ብዬ ክፍት ቦታ ለመተው ነው።
የሚኒስቴር ስም ከተነሳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ፤የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ፣ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጌታቸው አምባዬ ያሳዝኑኛል። በዚህ በአስቸካይ ጊዜው አዋጅመሠረት ኮማንድ ፖስት የተባለው የሚሰጠውን” ግደለው፤ቁረጠው ፍለጠው!” መርዶ በአደባባይለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚነግሩን እነዚህ ናቸው። በሉ የተባሉትን ማለት ነው! በአንድ በኩል ቢያሳዝኑኝም “ባይበላ ይቅር!” ማለት አይችሉም እንዴ? እላለሁ ። እንደ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ማለት ነው። “ተዘከረርኒ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ!” አለ በቀኝ ጎኑ የተሰቀለው ወንበዴ ። “በመንግስትህ አስታውሰኝ!” ብሎ ገነት ገብቶ አደረ ነው የሚሉን የክርስትና አስተማሪዎች። መፀፀት ማለት ነው! ስለዚህም “በቅርቡ የወያኔ መንግስትስለሰጠው ሹመት ትንሽ መተንፈስ እፈልጋለሁ!” ያልኩ እንደሁ እውነቴን መተንፈሴ ነው ብዬ አምናለሁ። “ያመነ ይድናል!” ማለትን ክርስትና በሞኖፖል የያዘውአይመስለኝም::
ወያኔ “በጥልቅ ተሐድሶ!” ላይ ነኝ ነው የሚለን። “ጥልቅና ተሐድሶ” ቃላቶች ናቸው።ቃላቶች ደግሞ በሐሳብ፤ በእምነነት፤በስሜት(Emotion,Feelings)፤ በድርጊት፤በምኞትና በሌላም የታጨቁ ናቸው። የሕዝብ ንብረቶች ናቸው። ሰውን፤ አድባሩን፤አውጋሩን፤እድሩኑ፣ መከነ መቃብሩን፤መሬቱን ፤ቤትንብረቱን፣ታሪካችንን፤አንድነታችንን፤ፍቅራችንን፤ትብብራችንን ሌላውን ተቆጥሮ ፣ተሠፍሮ፤ተነግሮ የማያልቀውን ሁለንተናችንን እንደአባከኑትና እንዳውደሙት ቃላቶችንም እያባከኑብን ፤እያውደሙብንና መሠረታዊ ትርጉማቸውን እየገፈፉብን ነው።ተሰፋዬ ገብረ አብ የዘጋጅ የነበረው እፎይታየሚባል መጽሔት ነበረቸው። ፋና የሚባል ራዲዮና ተሌቪዝንም አላቸው።ዋልታ የሚባልም ነገር አለ:: Ethiopiafirst የሚል ድሕረ ገጽም አላቸው።ሚሚ ስብሐቱና መሰሎችዋ አሉ። ባይሆን ደህና እንደጀመሩት ተራራ
Page 2 of 7
ያንቀጠቀጠ ትውልድ ቢሉ የሚሻል ይመስለናኛል። አድባር አውጋር አፍራሽ!! ስምን መል አ ክ ያወጠዋል የሚሆን ይመስለኛል።
አሁን ወያኔና የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚስማማበት አንድ ቁርጥ ነጥብ አለ። ወያኔ ኪራይ ስብሳቢዎች ነን ብሎ መናገር ከጀመር ይኸው አመታት አልፋፈዋል። ዘራፊና አውዳሚዎች ነን ማለት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብም ዘራፊ፣ ሌባ፣ አገር አጥፊ ናችህ ብሏል። በዚህ ላይ ስምምነት አለ። ልዩነቱ መፍትሔው ላይ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ “ከመሔዳች ህ ከመውደማ ችህ ሌላ ምናች ሁንም አልፈልግም !”ብሏል። ያ ቢሸፈቱ እልቂቱ ቄራ ላይ ደጋግሞ “Down! Down with Weyané!” ያለው ወጣት አጠቃሎታል። ወያኔ ደግሞ ጥልቅ ተሐድሶ ያለዋል። ያንን ነው “ፍየለ ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ!” የሚለው በቁርጡ የሚገለጠው።
የካቲት 1966 ካለፈ 43 አመት ሆነው።አብዛኛዎቻችን የዐይን ምስክሮችርም ፤አንዳንዶቻችን ተካፋይም ነበርን። አንዱ ጎልቶአሁንድረስ የሚሰማኝ “ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም!” የሚለው የህዝብ ድምጽ ነበር። አክሊሉ ሀብተወልድ ጠቅላይ ሚኒስቴሩነቱን ለቀቁና ልጅ እንዳላካቸው መኮንን ጠቅላይ ሆኑ። ያኔ ነው“ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም!” የተባለው። እንደሚታወቀው ፍጻሚው ለሿሚም ለተሿሚውም አልበጀም።
***
ወደጉዳዩ
የዚህ “የጥልቅ ተሐድሶ” ተሿሚዎችን ታሪክ ያገኘሁት ከማሕበራዊ ገጽታዎች ነው። ማሕበራዊ ገጽታዎች እንደማጥሪያ /ማበጠሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ሁነዋል ማለትነው። ፤ፈረንጅ Vetting! ይለዋል:: ትርጉሙ እነሆ:-
Vetting – Wikipedia
Vetting is the process of performing a background check on someone before offering them employment, conferring an award, etc. A prospective person or project may be vetted before making a hiring decision. In addition, in intelligence gathering, assets are vetted to determine their usefulness.
በኛ ብንተረጉመው “ለመሆኑ እሱ፤እሷ ማነው፤ማነች? ምን ነበሩ የት ነበሩ? ምን ሐብት-ንበረት አላቸው? በዘመድ አዝማድ ስም የተመዘገበ ወይም ያልተመዘገበ ሀብት ንብረት አላቸው? ከየት አመጡት? እንዴት አመጡት? ሀብት ንብረታቸው ከነበራቸውና ካላቸው ገቢ ጋር ተመጣጣኝ ነው? ግብር ከፍለው ያውቃሉ? ምን ያህል ከፈሉ?” የሚለውና የመሳሰለውን ለማወቅ ነው። የደበቁት፤የሚደብቁት ነገር መኖር አለማኖሩን ለማውቅ ያክል ነው። ነገሩ አጓጉል ሰው ስልጣን ላይ እንዳይመጣና በኋላ “የህንንማ አውቀነው ቢሆን ኖሮ!” እንዳይሰኘን ጥንቃቄ መሆኑነው። የሕዝብ አገለጋይ መሆን የጸዳ ሒሊና፤ዕውቀት፤ተመክሮ ብቻ ሳይሆን የጸዳ እጅም ይፈልጋልና ነው።
**
እንግዲህ በዚህ “ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም፦” መንፈስ አዲስ “ከተለዋወጡትጉልቻዎች” የሶስቱን(3) ወጥ መጣጣም እንሞክራለን::
Page 3 of 7
1.አንዷ ዶከተር ሒሩት ወልደ ማርያም የባህል ሚኒስቴር ሆነው “የተለወጡት “ናቸው።ስለ ዶክተር ሒሩት ሌላ የማይታመን ዜና ሰማሁና “ለመሆኑ ማናቸው?”(ጥናት መሆኑ አይደል) ብዬ የበለጠ ለማውቅ ፈታተሽኩ። ዛሬ መፈታተሽ ማለት Google ማድርግ ማለት ነው።አሪቡ ከሚባል ጣቢያ ጋር ያደርጉትን ቃለ ምልልስ አዳመጠኩ።
በአንደበታቸው አንደገለጹት ሒሩት የተወለዱት ደብረ ማርቆስ ፤ጎጃም ነው። አባታቸው አስተማሪ ሆነው እዚያ ስለተመደቡ! ጎጃሜ አገቡና ሒሩትና ሌሎችም ወለዱ። እናታቸው ጎጃሜ ናቸው ማለት ነው።አባታቸው ወደ አዲሳባ ተዛወሩ። ሂሩት አንደኛ ደርጃ ቁስቋም፤ሁለተኛ ደርጃ ተፈሪ መኮንን ተማረች።”አዲሳባንኮ አላወቀውም !”ይላሉ። “የማውቀው አዲሳባ ከስድስት ኪሎ እስከ ቁስቋም ነው” አሉ። ማለትም የቀረውን አዲሳባ ፤ደቡብ አዲስ አበባን ጨምሮ አያውቁም ማለት ነው።
አባታቸው ፤አቶ ወልደማርያም ከከምባታ ናቸው። ከካምባታ ማለትየግድ ከምባታ ናቸው ማለትም አይደለም። ከጋሞ መጣሁ ያለ የመጣበትን ተናገር እንጅ ብሔረሰቡን መናገሩ አይደለምና ነው። ደጉ ዘመን አለፈ እንዳትሉኝ እንጅ ምክንያት ኖሮት ካልተነገር/ካልተጠየቀ የሚጠየቅም አልነበረም::
ዶክተር ሒሩት ከምባቲኛ የሚችሉም፤የሚናገሩም አይመስለኝም። እናታቸውም ስለማይናገሩ! ማርቆስ መነጋጋሪያው ከምባቲኛ ስለ አልሆነ! እንግዳ ካልመጣ በስተቀር ቤታቸውም ከምባቲኛ የሚነገር አይመስለኝም። ማን ከማን ጋር ሊናገርበት! ይህ አዲስ ነገር አይደለም። በሚሊዮን በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤተሰብ ውስጥ የተለመደ፣የነበረ፣ያለ፤ የሚኖር ነው። ይህንን ሁሉ እዚህ ያነሳሁት ዶክተር ሒሩት አሁን የደርሱበት የደረሱት የደቡብ ክልል ድርሻ ይሆን እጣ ሆነው ነው ለማለት ነው። ደቡብ አዲሳባን እንኳን ሳያውቁ እንዳደጉ ነግረውናል። ሌላውን ባሕሪያቸውን ሳየው “ ወዶ ገባ “ይመስሉኛል። ብቻ ምርጫውም ጠባብ ነው። ኢትዮጵያዊ የሆንክ ሁሉ የምትወሽቅበት ሳጥን ፈለግ ተብሎ በሕገ መንግስት ተደንግጓልና! ክልል ነው የሚባለው? እኔ እዚህ ሐሪቡ ላይ ስታዘብም ሒሩት ቁርጥ ፤ቁልጭ ያሉ የአዲስ አበባ ልጅ ናቸው! ስምንተኛው ሽ ገብቷልእንዳትሉኝ ፈራሁ!
አሁን ከፍብሎ“ስለ ዶክተር ሒሩት ሌላ የማይታመን ዜና ሰማሁና “ወደ አልኩት እመለሳለሁ። እንደሚታየው ዶክተር ሒሩት የተማሩ፣ ዶክተርም የሆኑ ናቸው። ጀርመን ሁሉ ሔደው ተመረዋል።አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪነት ብቻ ሳይሆን የተላያዩ ከፍተኛ ሥልጣናትም ነበራቸው። ምክትል ፕሬዚደንትንም ደርጃ ደርሰዋል።የዩኒቨርስቲው “የኪራይ ሰብሳቢዎች” ተቆጣጣሪም ነበሩ። ሙስና ነው የሚባለው? ታዲያ ያንን ሁሉ ደርጃና ሥልጣን የገኙኑት በትምህርታቸው ፤በእውቀታቸው፤በሥራ ትጋታቸው ብቻ ሳይሆን በጓሮና በድብቅ መንገድ ነው ተባለ። ተብሎም አልቀረ ያ የዶክተር ሒሩት የተለየ የጓሮ መንገድ ምን እንደሆነ የሚያሳይ በራሳቸውና በጓሮው መንገድ ተባባሪዎቻቸው የተጻፈ ማስረጃ ይፋ ሆነ። “በልጅ ፊት አይነገርም!” የሚባለው አይነት ነው::እኔ አሁን የምለውን የምለው ከዚያ ማስረጃ ነው።
በጓሮ መንገድ ሲኬድ ጨለማ ነውና በራስም በሌላም ላይ ጉዳት ማድረሱ ያለ ነው። የጨለማ መንገድ ነውና! በዚህ ዶክተር ሂሩት ካሳዘኗቸው፤ከበደሏቸው፤ካጉላሏቸው አንዱ የሒሩትን Email ጠለፈ(hacked)::ጠልፎምአልቀረየጠለፍና አደባባይ ዘረገፈው። emails ሒሩት ከሌሎች የዩኒቨርሲው ባለሥልጣናት ጋር ያላቸውን ከጋብቻ ውጭ የግብረ ሥጋ ግኑኝነት የዘከዝካል።
Page 4 of 7
ዶከተር ሒሩት ባለትዳር ናቸው ።ነበሩ! ይህ ከትዳር ውጭ ያለው የግብረ ሥጋ ግንኙት የሚፈጸመውደግሞ ከሌሎች ሁለት ባለትዳሮች ጋር ነበር።የዪኒቨርስቲው ባለሥልላጣኖች! ጉዱአደባባይሲወጣ ከዚህም የተነሳ የሶሱቱም ትዳር ፈረሰ ።”አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው!” የሚባል ነው ይሉኛል በወቅቱ ዩኒበርሰቲ የነበሩ::እኒህ ዶክተር ሒሩት ናቸው “በጥልቅ ተሐድሶ!” የባሕል ሚኒስቴር የሆኑልና።
ሌላ ምን እላለሁ!” ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም!” ከማለት ሌላ ምን ይባላል?
***
2. ሁለተኛው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሀነ ናቸው ።በ፵ ሚሊየን ብር ያለአግባብ ግዥ ሊጠየቁ የሚገባቸው ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነን ለሚኒትርነት ማዕረግ? ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሠራተኞች አንዷበሚል የጥቁር አነበሳ ሆስፒታል ሥራተኞች ያቀረቡት በየድሕረ ገጻቱ ሁሉ ወጥቷል። የዐይን ምስክር ቃል ብቻ ሳይሆን፤በጥናት ማስረጃ የተደገፈ፤የተመጠነና የተመዛዘነ ሆኑ አየሁት። የፕሮፍፈሰሩን ደካማ ጎን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ጎናቸውንም ያነሳል። ጥሩ አለቃ ለእድገት ወይም ልዝቅጠት መመዘኛ (Evaluation)ያዘጋጀው የሚመስል ነው።
በስድስት ነኡሳን ክፍሎች የተከፋፈለ ነው። ከዚህ ውስጥ አምስቱ “አባ መንጥር !አባ በዝብዝ!” የሚል ተጨማሪ ማእረግለፕሮፌሩ የሚያሰጣቸው ይመስለኛል። እኔ እዚህ ስደሰተኛው፤”የሆስፒታሉን ግማሽ ክፍል እንዲፈርስ የማድርግ ውሳኔ” የሚለው ላይ ትንሽ የመለው አለኝ።
ይህ ሆስፒታል ቀድሞ የልዑል መኮንን ሆስፒታል ሊባል የነበረው ነው። ሊባል የነበረው ያልኩት የልዑል መኮንን ሆስፒታል ተብሎ ተመርቆ አልሰራም። ከመመረቁ በፊት ደርግ መጣና የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብሎ ሠየመው።
የልዑል መኮንን ሆስፒታል ከኋላው ታሪክ አለው። የንጉሱ ልጅ በመኪና አደጋ ሞቱና የኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ መዋጮ አድርጎ መታሰቢያ ሆስፒታል ይስራ ከሚል የመጣ ነው። ልጅ ሆኜ ትዝ የሚለኝ ነገር አለ። ጥዋት ጥዋት ትምህርት ቤት ስንሔድ አራዳ አጃንስ በር ላይ ቆም እንልና ራዲዮ እንስማለን። ጨንቻ ከተማ ያለው ብቸኛው ራዲዮ ይኸው ነበር። የማስታውቂያ ሚኒስቴር መሆኑ ነው።ሁሌ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሆስፒታሉ ማሰሪያ ያዋጣው ገንዝብ ልክ በጠቅላይ ግዛት፤በአውራጃ፤ወረዳ መንደር የአውጭው ስም ጭመር ይነበባል። ለስንት ጊዜ እንደሆነ አላውቅም። ለዘለዓለም ጥዋት ጥዋት የተነገረ መስሎ ይስማኛል። ይህ ማለት እንግዲህ የልዑል መኮንን ሆስፒታል የተገነባው በኢትዮጵያ ሕዝብ አንጡራ ገንዘብ መሆኑ ነው።
ደርግ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብሎ መሠየሙ ራሱ ታሪካዊ ነው። ጥቁር አንበሳ ንጉሱ አገር ጥለው ሲፈረጥጡቱ ወጣት መኮንንች ተሰበስበው የመሠረቱት የአርበኝነት ግንባር ነው። ሕብረብሐር ብቻ ሳይሆን ከጣሊያን ጦር ከድተው የመጡ ኤርትራዊያን አርበኞች ጭምር ያቀፈ ነበር። ለዚህ ሁሉ መጀመሪያ በ1943 አስመራ አሁን ደግሞ አዲስ አበባ የታተመውን የአቶ ታደስ ሜጫን “ጥቁር አንበሳ” መጽሕፍ ማንበብ ጥሩ ነው። “ጥቁር አንበሳ” የሚለውን የመጽሕፉን ርእስ “ሕዝበ ኢትዮጵያ ንሰአ ወልታ ወኩናትወተንስእ ውስተ ረዲትየ” የሚል በአዲስ ጨርቃ ቅርጽ ከቦታል። የአቶ አዲስ አለማየሁን
Page 5 of 7
“ትዝታ”ም ማንበብ ነው። አቶ ታደስ ሜጫ ለአካለ መጠን ሳይደርሱ ነበር ጥቁር አንበሳን የተቀላቀሉት። አቶ አዲስ አለማየሁን ለ5 አመት ጣሊያን አገር ግዞት ድርጓቸዋል።
ለዑል መኮንን ሆስፒታል ሌላም ታሪካዊነት አለው። የዛሬው እርዳታ ማስተባበሪያ የተጸነሰው ገና በቅጡ ባላለቀው እዚያ ውስጥ ነበር።የአየር ኃይሉ ኮሎኔል ተሰማ አባደራሽ እዚያ ተፍ ተፍ ሲሉ አግንቼ አነጋጋሪያቸው ነበር። በወቅቱ የአውራጃ አስተዳዳሪ ስለነበርኩና አውራጃዬ በተለይም ኮምሶ ወረዳ ድርቅ ገብቶ ስለነበር እርዳታ ለማፈላለግና ለኔም መንቀሳቀሻ የተሻለ ላንድሮቨር ለማግኘት ነበር።እርዳታ ማስተባባሪያም ታሪካዊ ስለሆነ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሌላም ታሪክም ማዕከል ተብሎ ሊታይ ይችላል።
አኩስም፤ላሊበላ የጎንደር ቤተመንግስት የተዘመረላቸው ታሪካዊ ቦታዎች ናቸው። ያልተዘመረላቸው የብርበር ማርያም፤ የናጋሳ ጫካ ፤የግንዳ-አንሳው መድሐኔ ዓለም፤ የጥቁር አነበሳ ሆስፒታል ያልተዘመረላቸው ታሪካዊ ማዕከላት ናቸው።
ታሪክን የጠብቁታል፤ይነከባከቡታል እንጅ አያፈርሱም። ከዚያ የስውረን ለማለትም አሁን ትንሽ የረፈደ ይመስለኛል።ቢሆምታሪክን ማፍረስ የሞከረ ለሹመት ለሽለማት በመብቃት ያለበት አይመስለኝም። አገርማ ደህና ቢሆን የሚያስጠይቅ ነበር!!
*****
3. ሶስተኛው የመንግስት ቃለ አቀባይ ሆነው የተሾሙት ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ናቸው። ዋዜማ ራዲዮ ስለዶክተር ነገሪ ያዘጋጀውን ቋጠሮ ድሕረገጽ ላይ አነበብኩት። የዋዜማውሌላው ዘማናይ አቀረራረብ ሆኖ ያገኘሁት ነበር። የዶክተር ነገሪን የተወሰኑ የቀደሞ ታማሪዎች አነጋግሮ የሰጡትን መልስ አስፍሯል። ሁሉም የተጠየቁት የቀድሞ ተማሪዎቻቸው የሚስማሙበት አንድነጥብ አለ።ይህም “ነገሪ በአማርኛም ይሁን በእንግሊዚኛ ማስተትማርም ማስረዳትም ብቁ አይደሉም!” የሚል ነው። አንዷ ለአስተማሪነታቸው ከ10ነጥብ 6(60%)ነበር የሰጠችው። በትምህርት ህግ ከሆነ ይህ C-(C minus) የሚሉት ነው። ፈተናውን ወድቀዋል ወይም ተነገዳግደውዶ አልፏል ማለት ነው።
ይህ አዲሱ ሹመታቸ ከሌላው በተጨማሪ አንደበት ርቱእነትን የሚጠይቅ ነው። የወያኔ ቃለ አቀባይ መሆን “ፈላጊ የሌለው ሸቀጥ ግዙኝ ግዙኝ” እንደማለት ይመስለኛል። ከዶከተር ነገሪ በፊት የነበሩት ሶስቱ ሊሸቅጡት አልተቻላቸውም ነበር።ሁለቱን ይህ ዳያስፖራ የሚባለው አንዱን እዚህ አሜሪካ ሌላውን ጀርመን አግኝቶ ሲያበሻቅጣቸው አይቻለሁ። አዘንኩላቸውም። ሌላው፣ ከማል በድሪ የሚባለውን፣” ምን የመስለ የሕግ ባለሙያ ነበር!” እያሉ የማውቃቸው ልጆች ይነግሩኛል። ከማል በድሪ ባከነብን ማለት ነው።
ዶክተር ነገሪ ለተናጋሪነት ብቁ መሆን አለመሆናቸውን በሳቸውን በአለቆቻቸው መካከል ያለ ይሆናል። እዚህ ማንሳት የፈለግኩት” ለመሆኑ ዶክተር ናቸ ው?” የሚለውን ነው።ዶክተር ሳይሆኑ ከሕንድስ አገር ይህ ደግሪ ከሚሸጥበት መደርደሪያ ላይ የገዙት ነው የሚል በድሕረገጾች ተለጥፎ አነበብኩ። ይህ ነገሪ ዶከተር ሆኘበታለሁ የሚባለውን ወፍጮ ቤት፣Dgree Mill!ይሉታልና፣ ሲፈጩና ሲያስፈጩ የነበሩ ናቸው የሚባሉት የሕንድ ፖሊስ ጠራርጎ እስር ቤት እንዳስገባ የሚያሳይ የህንድ ጋዜጣ ጭመርተለጥፎ ነበር።
Page 6 of 7
ከ1981 ጀምሮ ድግሪ መግዛት ወይም ማዘዝ ኢትዮጵያ ውስጥ የደራ ገበያ እንደሆነ አነባለሁ። አበበ ገላውን ጨምሮ ሌሎችም “ማን ከየት እንደገዛ!” የሚያሳይ የስነድ ማስረጃ ሲያቅርቡም አይቻለሁ። Civil Service College የሚባል በመለስ ዜናዊ ጠንሳሽትና በዶከተር ፋሲል ናሆም ዘዋሪነት የተቋቋመው ዋናው አላማ የህንን የኢትዮጵያ የመንግስት ሥራተኞ ባልሥልጣንን (CPA) “እዚህ ለመቀጠር ይህን ድግሪ አመጣ!” የሚለውን መመዘኛ በአቋራጭ ሩጦ ለመቅደም ነበር።ብዙ የኢ ሕ አ ደ ግ ባለስልጣናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ድግሪያቸውን ያገኙት ቢሯቸው ቁጭ ብለው በስልክ እያዘዙ እንደነበረ የቀድሞ መምሕሮቻቸው ይናገራሉ። ለዚህ አንድ ማስረጃ አድርገው የሚያቀርቡት አሁን አውስትራሊያ የሉትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሴት ወይዘሮ ነው።
ነገሩ የ”ዶክተር” ነገሪ ሌንጮም ዶክተርነት ከዚህ ከትልቁ ምስል ውስጥ የሚታይ ነው።አሁን ሌላ መንግስት ቢመጣ ባለፈው 26 አመታት “የተገዙና ያልተገዙ ደግሪዎች” አጣሪ ኮሚሽን ማቋሄቋም ሊኖርበት ነው ማለት ነው?
***
ለመጠቅለል
The Fish Smells from the Head ይላል ፈረንጅ “የ አሣ ጥንባቱ ከወደ አናቱ!” ለማለት። ወያኔ “በጥልቅ ተሐድሶ!” ጠልቆ ካመጣቸው ሶስቱ በከፊል ይህ ጠርንአላቸው! አለባቸው! ማሕበራዊ ገጾች እንደጀመረቱ ሌሎችንም ያወጣሉ ብዬ አስባለህ። ነገሩ፣ሲጠልቁ ቢውሉ፣ቢያድሩ ምን ያሕልም ቢጠልቁ ያው “ውሀ ቢወቅጡት እምቦጭ!: ነው ሆነ።ይህም ማለት ጥንባቱ ከራስ ጠጉሩ እስከ የእግር ጥፍሩ ሆነ ለማለት ነው። መፍትሔው ህዝቡን ማዳመጥነው! አማራጭ የሌለው ሆኗልና! ወይም ቢሸፈቱ የእሬቻ ለት የሰው ማረጃ ቄራው ላይ “Down! Down!….” ያለውን ወጣትም አዳምጦ ከ Down በፊት የሚሔዱበት መሔድ ጥሩ የመስለኛል። ያለበለዚያ የሚወርዱበት ብዙ ያዘጋጁት ቦታ እንዳለም አለመርሳት ነው!
አሜን
ህዳር ፭ ፪፻፱
ምርቃት
ይኸኛው ደግሞ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩትን እንኳን ደስ አልዎት ለማለት ያደርጉትን ከፍተኛ ጥረት አንዱFacebook ላይ ያለጠፈውን አግንቼ ነው። Comrade ያለፈ የኮሚኒስት ዘመን ቃል ነውና ቢጠፋቸው ምን አለበት ለማለት ነው!Facebook ጥሩ መጥፎውና አስጠያፊው ም እንደተጠበቀ ሁኖ ለኔ ትላቅ ትምህርት ቤት ሆኖኛል። ወጣቱን ትውልድ የማገኝበት ትልቁ መድርኬ ነው ከ5000 ወዳጆቼ (Friends)አብዛኛው ወጣት ነው። በልደታቸው ቀን “እንኳን አደርሳችህ!” ስለምል ወጣትነታቸውን አውቀዋለሁ

Filed in: Amharic