>

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች-ፖሊስ እና ሰራዊቱ በሕዝብ ላይ አልተኩስም ብለዋል ወቅታዊ ሪፖርታዥ [ክንፉ አሰፋ]

TPLF logo 2በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የሕወሃት ቁንጮዎች ትእቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት።ከድርድር ይልቅ ከሕዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል።

አብዛኛው የፖሊስ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ “ሕዝብ ላይ አልተኩስም” ማለታቸውየህወሃት አመራርን ጭንቅ ውስጥ አስገብተውታል።

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች። በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገባም የሚወጣም የለም። መንገዶች በሙሉ ተዘጋግተዋል።  ስልክ እና ኢንተርኔት ጠፍቷል።

በአዲስ አበባ ዙርያ ባሉ ከተሞች ሰኞ መስከረም 23 ቀን የተጀመረውን ሕዝባዊ አመጽለማዳፈን በህወሃት የተወሰደው የአፈሳ እርምጃ አመጹን አላቆመውም። ሰኞ ማምሻውን በሺዎችየሚቆጠሩ ዘጎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ በወሰዳቸው ሳብያ አመጹ በዛሬው እለት ተባብሶቀጥሏል።  የአካባቢ ፖሊሶችም ከሕዝብ ጋር በመሆን በአመመጹ እየተሳተፉ በመሆኑ የስራአቱንቁንጮዎች ጭንቀት ውስጥ ከቷቸዋል።

ሰበታ ላይ የነበረው የቱርክ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ እና የሃይል ማመንጫ ኩባንያበትናንትናው እለት መውደሙን ሮይተርስ ከስፍራው ዘግቧል። በሆለታ በነበረው አመጽ ሚስ ሻሮንሬይ የተባለች አሜሪካው የግብርና ኤክፐርት መገደልዋንም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቦ ነበር። ይህዜና በአለም የመገናኛ ብዙሃን ከተሰማ በኋላ ህወሃት የስልክ እና የኢንተርነት አገልሎት እንዲቋረጥአድርጓል።  የአመጹ ዜና ወደ ሌሎች እንዳይሰራጭ ታቅዶ የተደረገው  ይህ ድርጊታቸው የህዝብንቁጣ እያበረታው መጥቶ ካድሬዎችን እየለቀሙ መምታት እንዲጀመር አስተዋጽኦ አድርጓል።

ሕዝብ በጋራ ተነስቶ የህወሃት ተላላኪዎችን እያስጠነቀቀ ሲሆን እንቢ ያሉት ላይ እርምጃእየተወሰደ ይገናል። የወንጂ ስኳር ፍብሪካ ከፉተኛ ቃጠሎ የደረሰበት ሲሆን፣ ኩሪፉቱ የሼክአላዓሙዲን የከብት ማድለቢያ ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። በቀርሳ ወረዳ አንድ የህወሃትተላላኪ በህዝብ ተገድሏል፣ በሆሮ ጉድሩ እና በጉጂም የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ላይ ሕዝብ እርምጃወስዶባቸዋል። በድሬ ዳዋ ዲፖ ጋዝ ስቴሽን ቤሳት ጋይቷል።

የናይጄሪያዊው ኪሎ ዲንጎቴ ንብረት የነበረው ዲንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ  ሙሉ በሙሉበህዝባዊ አመጽ መውደሙን የአፍሪካ ሜድያ ኔትወርክ ዘግቧል። ጉጂ ዞን ያለው የሼክ አላሙዲንየወርቅ ማእድን በትላንትናው እለት መውደሙን ማህበራዊ ድረ-ገጾች ዘግበዋል።

ባዶ እጁን እየወጣ ሲገደል የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ አሁን ራሱን ራሱን የሚከላከልበትመሳርያ እየያዘ  መውጣቱን የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ። በአለም ገና ዳሽን ባንክ እና ከገዥውፓርቲ ጋር ንክኪ ያላቸው መኪናዎች ተቃጥለዋል።

በአርሲ፣ በመቱ እና በጂማ በተማሪዎች የተቀሰቀሰው አመጽ እንደቀጠለ ነው። የጅማወህኒ ቤት ተቃጥሎ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ የተደረገው ትላንት ምሽት ላይ ነበር።

አዲስ አበባ ከእሬቻው እልቂት በኋላ የሙት ከተማ መስላለች። የንግድ እንቀስቃሴ በሙሉቆሟል። ሱቆች ዝግ ናቸው፣ የህዝብ ትራንስፖርትም የለም።  መርካቶም ጸጥ-ረጭ እንዳለች ነው።በዛሬው እለት ታክሲ በከተማዋ ባለመኖሩ አብዛኛው ሰው ስራ አልገባም። ከተወሰኑ የግል ትምህርትቤቶች  በስተቀር የመንግስት ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ተወስኗል። አንዳንድየግል ት/ቤቶች ወላጆችንን  ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት  እንዳይልኩ እየመከሩ ይገኛሉ።

ለአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ያደረገው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው። ሌላዎቹ ዩኒቨርሲቲ ግቢውስጥ ተማሪ ገብቶ የመማሩ ጉዳይ የሚታሰብ አይደለም።

በደቡብ ወደ ሻሸመኔ እና ወደ አዋሳ የሚወስደው መንገድ እሁድ ጀምሮ ዝግ ነው።በሰሜን ሱልልታ፣ ለገዳዲ፣ ቦሌ ቡልቡላ፤ በም እራብ በአስኮ፣  በቡራዩ፣  ሰበታ፣ አለምገና፣ብስራተ-ገብሬል፣ አየር ጤና፣ ወልሶ፣ ወደ ሆሳዕና እና ጅማ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉተዘግተዋል። በዚያ የሚተላለፍ ተሽከርካሪ ቢገኝ የድንጋይ ናዳ ይወርድበታል።

አጋዚ ይህ ሕዝባዊ አመጽ ከቁጥጥር ውጪ ስለሆነበት አዲስ አበባን ብቻ ከብቦ እየጠበቀ፣ንጹሃን ዜጋን በማፈስ ስራ ላይ ተጠምዷል።

ህወሃት በአማራው ሕዝብ ላይ በይፋ ያወጀው ጦርነት አልተሳካም። ራሱን ከመከላከልአልፎ አካባቢውን ከአጋዚ ነጻ እይደረገ ይገኛል።  በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር ነጻ ወጥተዋል።የባህርዳር ዩንቨርስቲ እስካሁን እንደተከበበ ነው። የኮሶበር ህዝብ የዳሽን ቢራን ጭኖ የነበረ ከባድመኪና ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል።

በባህር ዳር ወጣቶችን ሲያሰቃይ የነበረ የማንኩሳ ተወላጅ ማንነቱ ባልታወቀ አካል ተገድሎመገኘቱ በማህበራዊ ድረ-ገጽ ተዘግቧል።

የህወሃት ባለስልጣናት አሸንዳን በርችት፣ እሬቻን በጥይት ካስተናገዱ በኋላ በወገን ላይበደረሰው አሰቃቂ እልቂት መላው የአኢትይኦጵያ ህዝብ ብሄራዊ ሃዘን ላይ ነበር።

ብሄራው ሃዘን ላይ የነበረው ህዝብ ወደ ብሀራዊ አመጽ የገባ ይመስላል።  ሰላማዊ ሕዝብንእንደ ግራዚያኒ፣ እንደ ሞሶሎኒ በጥይት እና በመርዝ ጭስ ከጨረሱ በኋላ በቴሌቭዥን ወጥተውአዝነናል እያሉ፣ ቁስልን የባሰ ሲነካኩበት ከዚህ ውጭ አማራጭ የለም። ሕወሃቶች ይልቁንምለራሳቸው ይዘኑ። ሰላማዊውን ህዝብ እየጨረሱ ያሉት ሁሉ በተራቸው የሚያለቅሱበት ግዜ ሩቅአይደለም። በደም የታጠበ እጃቸው ገና ሳታደርቅ በቴሌቭዥን ወጥተው በሟች አጽም ላይመቀለዳቸው ሳያንስ በተለመደ የሽብርተኞች ዲስኩር ህዝብ ላይ እጅ መቀሰር ድፍረት ነው።

ግዜ ሊወስድ ይችል ይሆናል እንጂ  እነዚህ ነብሰ-ገዳዮች የእያንዳንዱ ነብስ ዋጋመክፈላቸው  አይቀሬ ነው።

የቢሾፍቱው ግድያ የህወሃት “ጥልቅ ተሃድሶ” ጅማሬ መሆኑ ነው። ግን ህዝብን እየረገጡብዙ ሊዘልቁ አይችሉም። ፍም እሳት የሆነ የአመጽ ትውልድ ተፈጥሯል። እነሱ ባሰሩ እና በገደሉቁጥር ሚሊዮን ሆኖ የሚነሳ ትውልድ። ምንም ነገር ሳይዝ በድምጹ ብቻ የሚያስፈራ ትውልድ። ህዝብን ጠላት አድርጎ ለመግዛት የሚሞክር ስርዓት ይህንን ሁሉ ህዝብ ከቶውንም ገድሎ ሊጨርስአይችልም።

Filed in: Amharic