>
5:13 pm - Friday April 20, 3387

ፈይሳ ሌሊሳ ውስጤ ነው! [ኣንዱዓለም ቡከቶ ገዳ]

Feysa Lilesa Rio2016 silverሻ/ል አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ሮም ላይ ካሸነፈ በኋላ ብዙ አትሌቶቻን ጫማ አድርገው ግን በባዶ ጭንቅላት እና በታላቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ሮጠው ለሀገራችን በማራቶን ህዝቡ በሚፈልገው መጠን ሜዳሊያ ለማስገኘት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
ትላንትና ግን ታሪክ ተሰርቷል፡፡ አቤ ለኢትጲውያንም ሆነ ለአፍሪካውያን ሯጮች የመጀመሪያ የሆነውን የወርቅ ሜዳሊያ በማራቶን እንደስገኝ ሁሉ ፈይሳ ሌሊሳም ለመጀመሪያ ግዜ የአፍሪካ አትሌቶች ከደሃ ህዝብ ውስጥ ድንገት ወጥተው ህይወታቸው ተአምራዊ በሆነ ሁኔታ ሲለወጥ ፌራሪ እየነዱ ፍርፋሪ ባጣው ህዝባቸው ላይ ሙድ ከመያዝ ባሻገር እውቅናቸውን በመጠቀም ሊያከናውኑት የሚገባ ታላቅ ፋይዳ እንዳለ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳይቷል፡፡ መጀመሪያ ባላስተውለዉም ሩጫውን ድጋሚ ሳየው ሌሊሳ ሲሮጥ ከሁለት ሰአት በላይ በሚፈጀው በአድካሚው እና አልህ አስጨራሹ የማራቶን ውድድር ሩጫ በባህሪው ከሚጠይቀው ብዙም ያልተወሳሰበ ቴክኒክ በላይ በውስጡ እየተብላላ የነበረ ታላቅ ሃሳብ እንደነበረ መገመት አያዳግትም፡፡.በቀደሙት አመታት ድሃ አትሌት ከሀገር ፍቅር ባሻገር ገንዘብ አግኝቶ የእራሱንና የቤተሰቡን ህይወት ለመለወጥ ጥርሱን ነክሶ ሲሮጥ በዛውም ለሀራችን ሜዳሊያ ይዘንብ ነበር፡፡አሁን አሁን ግን አትሌቶቻችን በውች ሀገራት በየጉራንጉሩ እየሮጡ ገንዘብ ስለሚያከማቹ ይሄንን (የሽቀላ) ሞቲቭ አጥነዋል፡፡ፈይሳ ሌሊሳ ደግሞ በአዲስ ሞቲቭ ከገንዘብም ከመታወቅም ሌሎች ተመሳሳይ እሩጫዎች ላይ ከመጋበዝም በላይ በሆነ የተጀከበረ ሞቲቭ ስሎረጠ እታአችሁት ከሆነ ሩጫውን ጨርሶ ከገባ በኋላ እራሱ ቁጭት እንጂ ድካም አይታይበትም ….አቦ …..”ሺ ቢወለድ ሺ ነው ጉደ የፈይሳ አይነት ይበቃል አንዱ” ነው ጉዳዩ፡፡
በነገራችን ላይ አትሌቶች ሁሉ ለሀገራቸው ክብር ሲሉ ወዛቸውን ጠብ አድርገው ለሚያመጡት ማናቸውም ሜዳሊያ ክብር አለኝ …..ግን አንዳንዴ ክብሬ ለሜዳሊያው ብቻ ይሆንብኛል! ….ገና በለጋነቱ ስለ ወገኑ ሞት እየተጨነቀ ከራሱ ምቾት በላይ በወያኔ እየተጨፈጨፉ ላሉ የሀገሩ ልጆች ወደውስጥ እያነባ የሚሮጥን እትሌት ከሌላ አንድ ለ22 አመት ሀገሪቷን እፍኖ ረግጦ የገዛ ጨቋኝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሲሞት ስታዲየም ከቢጤዎቹ ጋር ተሰብስቦ “ጀግና አይሞትም” እያለ ከሚነፋረቅ እና “ዲሞክራሲ ለኢትዮጲየውያን ቅንጦት ነው!” ከሚል ሻለቃ አትሌት ባስበልጥ መብቴ ነው!…..ሜዳሊያቸውን እኩል ባይም ልፋታቸውን እኩል ባከብርም ስለ ሰውነታቸው እና ልእለ ስብናቸው ያለኝ ግምት ግን በሌላ ሚዛን የሚሰፈር በመሆኑ አንዳቸው ከሌላኛው ሊበልጡ ግድ ይላል፡፡ እና ትላንት ፈይሳ ሌሊሳ ባደረገው ነገር ሩጫ ከፍርጠጣም በላይ ታላቅ መልእክት ሊተላለፍበት የሚችል ታላቅ ጉዳይ እንደሆነ አትሌቶችን አስገንዝቦን አልፏል(እኔ ማነኝ ግን?) …”ክብር ለማይገባው የታሪክ አተላ(ለሮቤል) በርትተን ሰፊ የነቆራ ፖስቶችን እንደሰራን ሁሉ ክብር ለሚገባው ሌሊሳ ደግሞ ሳምንቱን ሙሉ በርትተን ክብር እንስጥ” የዛሬው የኮሚኒኬሽ ቢሮአችን መልእክት ነው! መልካም ምሳ! ሎል!
ከዚህ ቀጥሎ የምጽፈው ጽሁፍ ከሰሞኑ ወያኔ ሰላማዊ ህዝብን በመፍጀቷ በጣም ተበሳጭቼ ስለነበረ ቀልድም ጠፍቶብኝ ሙዴም ተከንቶ አእምሮየንም ነካ እያደረገኝ የጻፍኩት ስለሆነ ለእብደቴ ይቅርታ! አስተካክላችሁ አንብቡት እንግዲህ….

1ኛ….ሰሞኑን ጉድ ስለማየታችን

ሰሞኑን መቼም ጉድ እያየን ነው!የበሰበሰው የወያኔ አገዛዝ እዚህም እዚያም እየፈነዳበት ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ድሮውንም ለይስሙላ እንጂ ከኢዲአሚን እና ከቦካሳ የማይተናነስ ሰው በላ ዲክታተር እንደሆነ ለአለም በማሳየት ላይ ይገኛል ፡፡በነገራቸን ላይ የቦካሳ ሚስት የሀገሪቱን ሀብት በከፍተኛ ስግብግብነት ወጥቃ የያዘች ሀብታም አሳማ ነበረች ….እና ከሀገራችን እንትናን ትመስላለች ብያለው ?አታነካኩኝ አቦ!….እቺ አልማዝ አያና ደግሞ ቀላል ትሮጣለች እንዴ !? በእውነት እንዴት እንደወደድኳት አትጠይቁኝ !? ግን የሸገር ልጆች ትላንት ለምን ሰልፍ ቀራችሁ በናታችሁ !? በነገራችን ላይ ያ ሁሉ ደም መጣጭ የአጋዚ ቫምፓየር መግብያ መውጫውን ይዞባችሁ ሰልፉን መቅረታችሁ ሳይሆን የገረመኝ አልማዝ አያና በማጣሪያው ምንም ለማይጠቅማት ዙሩን አክርራ ለፍጻሜው ጉልበቷን መጨረሷ ነው! ዋናው ግን ሁለት ወርቅ ባለማምጣቷ የተከበረውን እና በወያኔ ቡችሎች ብቻ የሚናቀውን የኢትዮጲያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቋ ነው…ወያኔ በየቀኑ ንጹሃን ወጣቶችን እየገደለች በጌታቸው ረዳ አማካኝት ሙድ ትያዛለች እንደአልማዝ አያና አይነቱ ደግሞ “ሁለት ወርቅ ስላላመጣው ይቅርታ!” ይላል….ይገርማል! እንጀራ ውስጥ ጄሶ ቀላቅሎ መሸጥ አይ ሀገር ወዴት እየሄደች ነው ግን !? ……ወያኔ ብላ ብላ “መልካም ምሳ!” እያለች ሰልፉ በመቅረቱ በዛ የልፍደዳ ቢሮዋ አማካኝነት ሙድ ይዛ ሀላፊዎቹ ከአሁን ወዲያ እንኳን ምንም የለም ብለው ወደ በርጫቸው ከሄዱ በኋላ. አይ ሌሊሳ የኛ አንበሳ እንጥላቸውን ዱብ አያርገውም!? ቆይ ጫት ትን ቢላቸውስ !? ለኪ ሚቲ አቦ ! ረቢ ሲ ያ ጀቤሱ….አቲ ነማ ጀባ ዳ! what you have displayed yesterday was a selfless heroism…..hats off bro!
2ኛ….በደስታ ከቤት ስለመውጣቴ እና ከሚስቴ ጋር ስለመጨቃጨቄ ግን በመጨረሻ የሆነ ነገር ስለመከሰቱ

እኔ፡…..”እሺ የደስደስ ከቤት ልወጣ ነው! እሩጫውም አለቀ…..ቻው የእኔ ፍቅር ….አላመሽም ቶሎ እመለሳለው”
ሚስቴ፡……”ቆይ በዚህ ሰአት ለምን ትወጣለህ ?ጊዜውም ጥሩ አይደለም”
እኔ፡……”ከዚህ በላይ ጥሩ ጊዜ አለ እንዴ?! ጥሩ ያልሆነው እኮ ለወያኔ እርዝራዦች ነው የኔ ማር! ይልቁንስ ምን ለብሼ ልውጣ?”
ሚስቴ፡…”ነጭ እንዳትለብስ ደግሞ ዛሬ የታላቁ መሪያችን ሙት አመት ነው ፡፡ጎንደርን ለምን በግድ አላዘንክም ብለው እየፈጁት ነው አሉ !?”
እኔ፡…..”እና እኔ ምን አገባኝ የመለስ ሙት አመት ቢሆን ባይሆን! ለምን አስሬ አይሞትም!…እንኳን እሱን ፓርቲውን እንኳን ተሳስቼ መርጬ አላውቅም! ”
ሚስቴ፡….”ቢሆንም ማንም ሰው እንኳን ሞተ አይባልም!….ሰውዬው እኮ ከ19አመቱ ጀምሮ ለህዝቡ ሲለፋ ኖሮ ሲለፋ የሞተ ነው!”
እኔ……”…ቆይ “ለህዝቡ” ስትይ ለየትኛው ህዝብ ነው የምትይኝ ?አንቺ ሴትዮ ፖለቲካ አታናግሪኝ …ይኸው በእሱ የሚሊታሪ ራእይ የታነጹ ወታደሮች አይደሉ እንዴ “ለምን ነጭ ቲሸርት አደረጋችሁ?” ብለው አስፓልት ላይ ወጣቱን በጥይት የሚዘርሩት! ቡል ሺት! እንደውም ነጭ ሸሚዝ እና ነጭ ሱሪ አቀብይኝ …ማን አባቱ እንደሚናገረኝ አያለሁ! ና አልዲነክ!”
ነጭ በነጭ ሽክ ብዬ ልብሴን ለባብሼ ወጣሁ፡፡በር ላይ የቀበሌአችን ካድሬ እና ሁለት ፌደራል ፖሊሶች ቆመዋል፡፡ውጭው በጣም ይበርዳል ፡፡ወደቤት ተመልሼ ገባሁ
ማሬ እስቲ እረጅሙን ጥቁሩን ካፖርቴን እና ጥቁሩን ሱሪየን አቀብይኝ …ይሄ ነጭ ልብስ ብርድ ይስባል”አልኳት ልብሴን ሳሎን ውስጥ በፍጥነት እያወላለኩ፡፡
“እንካ ይሄንን ልበስ.. ድሮም እንደምትመለስ ገምቻለሁ” አለች እየተፍለቀለቀች….
“ድሮም እንደምትመለስ ገምቻለሁ” ስትል ምን ማለቷ ነው ግን? ወደ መኝታ ቤት እየተፍነከነከች ስትገባ “ድሮም የአዲስ አበባ ልጅ!” የሚል ቃል ጆሮዬ ጥልቅ አለ
“ምን አልሽ አንቺ?!” ……በሙታንታ እንደሆንኩ ተከትያት መኝታ ቤት ገባሁ
በጀርባዋ ተንጋላ ተኝታ ትስቃለች…አተኛኘቷ እና አሳሳቋ ለጠብ የመጣሁትን ሰውዬ ሌላ ሃሳብ ውስጥ ከተተኝ…ምራቄን እየዋጥኩ ለሰከንዶች ቁልቁል አየኋት..
ያለኝ አማራጭ ሶስት ነው
1ኛ.የአዲስአበባ ልጅ በፍቅር አንደኛ መሆኑን መናገር እና ምሳሌም ካስፈለጋት እዚሁ ማሳየት
2ኛ.የሸገር ልጅ አንዴ ከተነሳ በጀግነነት ከማንም የማያንስ መሆኑን መናገር እና ምሳሌም ካስፈለጋት የዘጠና ሰባቱን ማስታወስ… አይ የቅርብ ምሳሌ ካለች ደግሞ ቤቴ በር ላይ የቆሙትን አሳሞች ምን እንደማደርጋቸው ተከትላኝ ወጥታ እንድታይ ማድረግ
3ኛ …የኔ ማር እኔ እኮ የጠበስኩሽ ሰሞን ነው እንጂ የሸገር ልጅ ነኝ ያልኩሽ እውነቱን ለመናገር የክፍለሀገር ልጅ ነኝ ብሎ መገላገል
እስቲ ምከሩኝ ወዳጆቼ!
ይመቻችሁ

Filed in: Amharic