ፈይሳ ሊሌሳ በሪዮ ኦሎምፒክ በተደረገው የማራቶን ሩጫ ውድ ድ ር 2:10:05 በማምጣት የብር ሜዳሊያ ለሃገሩ ኣስገኝቶኣል። ይህም ብቻ ኣይደለም፤ ፈይሳ ሊሌሳ በተገኘችው ኣጋጣሚ በኢትዮጵያ ውስጥ በኣምባገነኑ ስርዓት በየቀኑ በኣጋዚ ወታደሮች ለሚገደሉት፣ ለሚሰደዱት፣ ለሚታሰሩት ወገኖቹ ከ 42 ኪሎ ሜትር እልህ ኣስጨራሽና ኣድካሚ ውድድር በኃላ በድል ሲቀዳጅ ኣጋርነቱን እጁን በማጣመር ለዓለም ኣሳይቶኣል። ብቻውን ሮጦና ለድል በቅቶ ለብዙዎች ድምጽ መሆን የቻለ የወቅቱ ጀግናና ኣንበሳ፤ ፈይሳ ሊሌሳ።