>
5:14 pm - Thursday April 20, 5493

የጎንደር ሕዝባዊ አመጽ ....[Hiber Radio]

Hiber Radio: የጎንደር ሕዝባዊ አመጽን ለማፈን ተጨማሪ ጦር በከተማዋ ገብቷል፣እጄን ለወያኔ አልሰጥም ያሉት የኮ/ል ደመቀ መጨረሻ አልታወቀም፣የአማራ ልዩ ሀይል ወገኑን ከሕወሃት ጦር እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ

colonel-Demeke-zewedu-gonder-up-raising-hiber-radio

በጎንደር ከትግራይ የመጡ የደህነት አባላት የወልቃይት የማንነት ኮሚቴ አባላትን አፍነው ለመውሰድ በወሰዱት እርምጃ በጎንደር የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ አሳሰበው የሕወሃት ቡድን ተጨማሪሰራዊት ወደ ስፍራው በማዝመት ተቃውሞውን ለማፈን እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ማምሳውን ጎንደር በርካታ የሕወሃት ሰራዊት ገብቷል። ለሕወሓት ደህነቶች እጄን አልሰጥም ያሉት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በቤታቸው ተከበው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም። በህዝቡ የኮሎኔሉን ደህንነት ለማረጋገጥ የታፈኑ አራት የሕወሓት አባላት የመከላከያ ደንብ የለበሱ ወታደሮች ታግተው የነበረ ቢሆንም ጠንካራ የተኩስ ልውውጥ ቤቦታው ስለሚሰማ እገታው ይቀጥል፣ኮሎኔሉ ይታፈኑ ወይም ያምልጡ የመጨረሻውን ማወቅ አለመቻሉን የህብር ምንጮች ገልጸዋል።ኮሎኔል ደመቀ በሌሌት ወደ ቤታቸው የመጡ የአማራ ክልል የማያውቃቸው የሕወሓት አፋኞችን በመቃወም እጄን አልሰጥም በማለት ሊገሏቸው ከተኮሱባቸው መካከል ሁለቱን ገለው ሕዝብ ከቦ ከከበባ ለጊዜው አውጥቷቸው ነበር።

የጎንደርን ሕዝባዊ አመጽ በወቅቱ እየተከታተለ የሚያሳውቀው አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ በበኩሉ ባወጣው መረጃ የኮሎኔል ደመቀ ደህንነት አጠራጣሪ መሆኑን ገልጿል።በመረጃው መሰረት በአሁኑ ወቅት ኮሎኔሉ የት እንዳሉ አልታወቀም።በጎንደሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የወልቃይት ጠገዴ የኮሚቴ አባላት መካከል ሆን ተብሎ ተቃውሞውን አስታኮ በሕወሓት ታጣቂዎች ሰባቱ ተገለዋል።

ትላንት ተቃውሞው የተነሳበት ቀበሌ 18 ወጣቶች የሕወሓትን ጦር ለመከላከል መቃወማቸውን ተከትሎ አገዛዙ የከባድ መሳሪያ ሳይቀር በንጹሃን ላይ ሲተኩስ የነበረ ሲሆን አንዳንድ ወጣቶች ባልሞት ባይ ተጋዳይት የአጸፋ ተኩስ ሲያደርጉ እንደነበር የደህነቶች ተሽከርካሪዎች ፣ሰላም የተሰኘው የሕወሓት ኩባንአ ባስ መቃጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል። ጎንደር በአሁኑ ወቅት መብራት የለም የጥይት ድምጽ ታልን ማምሻውንም ያልተቋረጠ ሲሆን በርካታ ንጹሃን የተገደሉ ሲሆን አንዳንዶች ቁጥሩን ከአርባ በላይ ሌሎች ሰላሳ አምስት በላይ ንጹሃን ተገለዋል የሚል ግምት ሲኖራቸው በተቃራኒው በሕዝቡ ላይ ሲተኩሲ ከነበሩት ቁጥራቸው አምስት የሚደርሱ የፌዴራል ፖሊስ ደንብ የለበሱ ሞተዋል።በትላንቱ ተቃውሞ ወቅት የትግራይ ልዩ ሀይል ፖሊሶች የፌዴራል ፖሊስ ልብስ ለብሰው የነበረ ሲሆን የሞቱት የትግራይ ልዩ ሐይል ታጣቂዎች ይሁኑ በእርግጥ የፌራል ፖሊስ አልታወቀም።

በጎንደር የተነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ መብራት የለም፣የ12ተና ክፍል ብሔራዊ ፈተና እና ማንናውም መንግስታዊ አገልግሎት እንደተዘጋ ነው።

ለወልቃይት ጠለምት አማራ ማነንታቸው ሲታገሉ ከነበሩት መካከል 7 ሰዎች በጥይት ተመትተው መሞታቸውን የዐይን እማኞች አረጋግጠዋል።::በሌላ በኩል ትላንት ከሕዝቡ ጋር አንዳንዶች የክልሉ ልዩ ሀይል የተባሉ ፖሊሶች ተቃውሟቸውን የገለጹ ሲሆን ሕዝቡም ወገናቸውን እንዲጠብቁና የሕወሓት አሽከር ሆነው የጥይት ቃታቸውን እንዳይስቡ ጥሪ አቅርቧል። ለስም የተቀመጠው የአማራ ክልል ሳያውቅ ከትግራይ ለአፈና በመጡ የደህነት አባላትና ልዩ ሀይሎች ሳቢያ አፍናችሁ አትወስዱም በሚል የተነሳው ተቃውሞን ተከትሎ ዘግይተው የፌዴራል ዩኒፎርምም የለበሱ የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት ጎንደር ላይ በሕዝቡ ላይ ሲተኩሱ ታይተዋል የሚል መረጃ ወጥቷል። ሰሞኑን የአማራ ልዩ ሀይልንም ዩኒፎርም የለበሱ በቤት ለቤት አሰሳ ወታቶችን ለማፈስ ሊሰማሩ ይችላሉ ሁኔታው ከዚህ የከፋ ደም መፋሰስ ሊአስከትል ይችላል ብለዋል።

በንጹሃን ላይ የተወሰደው የግፍ ግድያ ያላበሳጫቸው አንዳንድ የሕወሃት ደጋፊዎች የጥቃት ዒላማ የሆነው ሰላም ባስና በግልጽ በጎንደር ከተማ የአዜብ መስፍን የስጋ ዘመድና የሕወሃት አባል ህንጻ ላይ ጥቃት መከሰቱ ሲያበሳጫቸው ታይቷል። አንዳንዶች የህወሃት ንብረት የትግርይ ሕዝብ ንንረት አይደለም የእነ ስብሃትና መሰሎቻቸው መጫወቻ ነው ስትሉ የነበረው ተቃውሞ የት ደረሰ ሲሉ ይጠይቃሉ።

የጎንደርን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በተቃውሞ ወደ ጎንደር የሚያስገቡ ጎዳናዎች ላይ የተቀመጡ ማገጃዎች ማምሻውን ሳይነሱ እንዳልቀረ የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።ለዚህ ምክንያታቸው ወደ ከተማው እየገባ ያለው ሰራዊት ከትግራይ የመጣ መሆኑን ገልጸዋል።ጎንደር ውጥረቱ እንደነገሰ ነው።የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ ጭምር በጎንደር በብዛት እየከተመ ሲሆን የሕወሓት ባለስልጣናት በጎንደሩ ቀውስ በቀጥታ አጋዚንና የፌዴራል የሚል ዩኒፎርም ያለበሱትን በሕዝቡ ላይ እንዲተኩስ አሰማርተዋል። በሌላ በኩል የጎንደሩ ሕዝባዊ አመጽ ወደ ሌሎች የአማራ አካባቢዎች በፍጥነት እንዲዛመት እና የሕወሓት ጸረ አማራ ጥቃት ተጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ በየቦታው ተመሳሳይ እርምጃ በሕወሃት ንብረቶች ላይ እንዲቀጥልና ሕዝቡ ተቃውሞውን እንዲገፋበት የተለያዩ ወገኖች ጥሪ ቀርቧል።የወልቃይት የአማራ ማንነትን በሰላማዊ መንገድ ለማስከበር የተንቀሳቀሱት እነ ኮ/ል ደመቀ ላይ የተወሰደውን እርምጃ በውጭ የሚገኙ የወልቃይት አማራ ተወካዮች አውግዘው ሕዝቡ ከኮሚቴው ጎን መሆኑን ገልጸዋል። አገዛዙ በተለመደው ስልት በሰላም ጥያቄ የሚአቀርቡ ኮሚቴዎችን በአንድ ጊዜ ሕገ ወጥና ከአሸባሪዎች ጋር ግኢንኙነት ያላቸው ሲል በመገናና ብዙሃኑ ሊከስ ሞክሯል። ሰሚ አላገኙም።

ሕወሓት በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን ያሉ የአማራ ተወላጆችን በእስር ቤት <<ሽንታም አማሮች>> በሚል ጭምር አስሮ የተለያዩ አሰቃቂ ግፎችን መፈጸሙን ከእስር ከወጡት መካከል የመኢአድ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ዘመነ ምህረት መግለጻቸው አይዘነጋም።

የጎንደር ሕዝባዊ አመጽ በአግባቡ አመራር አግኝቶ ተቃውሞው በሕወሓት አፈና ሳይቸፈለቅ ሁሉንም የአማራ አካባቢዎችን እንዲያዳርስ ሕዝቡ በየቦታው በራሱ የሚታዘዝ የጎበዝ አለቃ እንዲአደራጅ ጭምር ሀሳብ የሚሰነዝሩ ወገኖች ታይተዋል። በጎንደሩ የትላንትና የዛሬ የአገዛዙ ወታደሮች በንጹሃን ላይ እየወሰዱት ባለ እርምጃ በትክክል የሞቱት ሰዎች ቁጥር ማወቅ ባይቻልም በትንሹ ከሰላሳ በላይ ንጹሃን መሞታቸው እተነገረ ነው።ጎንደር ሆስፒታል በወታደሮች መከበቡን ለማወቅ ተችሏል።

ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Filed in: Amharic