እርግጥ ገንዘብ ኩንታል ጤፍ ይገዛ ይሆናል ፥ አንድ ጉርሻ ፍቅርን ግን አይገዛም ! እርግጥ ገንዘብ እልፍኝ ሙሉ ባለሟልን ያመጣ ይሆናል ፥ ግን ደሞ በልፍኙ ካሉ እልፍ ባለሟሎች ልቦና ውስጥ ፍቅር ንጦ ማውጣት አይቻለውም ። እርግጥ ገንዘብ ቤት እና መኪና ይገዛ ይሆናል ፥ የህሊና ሰላም ግን መግዛት አይቻለውም ፥ እርግጥ ገንዘብ ሃገር መግዛት ይችል ይሆናል የሃገር ፍቅር መፍጠር ግን አይቻለውም ፥ እርግጥ ገንዘብ ወርቅ መግዛት ይችል ይሆናል ፥ ወርቅ ትውልድን ማንበርከክ ግን አይቻለውም ።
በገንዘብ ልትገዙ የሞከራችሁት በገንዘብ የሚገዛ ነገርን አይደልም! ታማኝ ታማኝ ነው ስለዚህ ይታመናል ። ስሙም ግብሩም ንዋይ እና ንዋያዊ አይደለም ። ሲሳይ ሲሳይ ነው ፥ ለናንተ በረከት ቢሆናችሁ እንጂ ፥ ከህመማችሁ ቢያክማችሁ እንጂ የናንተን በረከት የሚፈልግ ሰው አይደለምና ። ሙሉ ሰዎችን በገንዘብ ማጉደል አይቻልም ።
የመንፈስ ሙሉነትን በንዋይ ማደፍረስም ሆነ ማፍሰስ አይቻልም ! እውነት በገንዘብ ቢገዛ ኖሮ ፥ እውነት የሚባል ነገር ባልኖረ! የእውነት ትልቅነት ንዋይንም ማለፍ መቻሉ ነው ! ታማኝ ቅዱስ ስም ነው ፥ ሲሳይ ቅዱስ ስም ነው ፥ ብፁዕ የሆኑት ግን በግብራቸው ነው!!!! ድል ለእውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች !