>
5:13 pm - Saturday April 19, 4319

አቶ ሀብታሙ አያሌው በአስቸኳይ የውጭ ሀገር ህክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚንሲትሩ አሳሰበ!!!

አቶ ሀብታሙ አያሌው በአስቸኳይ የውጭ ሀገር ህክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚንሲትሩ አሳሰበ!!! በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደረስው አደጋ መንግሥት ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን ጭምር ፓርቲው አክሎ ገልጾአል ።
Blue party letter to Ethiopia PM 29062016መንግስት የዜጎችን ደህንነትና ጤንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም በሀገራችን በሕግ ከለላ ስር ያሉ ዜጎች ተገቢውን ሕክምና ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ በእስር ቤት እያሉ ተገቢውን ሕክምና ማግኘት ባለመቻላቸው ለሞት የተዳረጉ እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡

አቶ ሀብታሙ አያሌው በተለምዶ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በመባል በሚታወቀው ተቋም በምርመራ ወቅት በደረሰባቸው ህመም ሕክምናውን በሀገር ውስጥ ባሉ የጤና ተቋማት መታከም እንደማይችሉና ወደውጭ ሀገር ሄዶ ህክምና ማግኘት እንዳለባቸው የተገለፀ ቢሆንም ከሀገር እንዳይወጡ በፍ/ቤት ታግደዋል፡፡

በመሆኑም አቶ ሀብታሙ አያሌው በፍ/ቤት የተጣለባቸው ዕግድ ተነስቶ ወደ ውጭ ሀገር ሂደው እንዲታከሙ አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ እየጠየቅን ይህ ባይሆንና ህክምና ባለማግኘቱ በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደረስው አደጋ መንግሥት ኃላፊነቱን የሚወስድ መሆኑን እናሳስባለን።

ግልባጭ፣
– ለኢፊዲሪ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት
–  ለሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ

 

Filed in: Amharic