>

ከዲሲ ግብረ ሀይል የተሰጠ መግለጫ!

ከዲሲ ግብረ ሀይል የተሰጠ መግለጫ! 

በኤኢሳ ዋን (AESA ONE) ላይ መሳተፍ በወገናችን እልቂት መቀለድ ነው !!

ግብረ ሀይልኢትዮጵያዊ ክብርና ሞገሳችንን ገፈው ህዝባችንን ጥሪቱን አሟጠው በንቀት እየተጫወቱ ያሉት ቡድኖች የሀገር ውስጡ አልበቃ ብሏቸው እነሆ ላለፋት 4 ዓመታት በውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ ለመበታተን ያደረጉትን ሴራ ህዝባችን አንድ በመሆን በቂ ምላሽ ሰጥቶ አክሽፎታል፤ ሆኖም ዛሬም ለ33 አመታት የቆየውን የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽናችንን ከኢትዮጵያ ህዝብ በግፍ በተዘረፈ የደም ገንዘብ ሊበታትኑት ኢትዮጵያን በኢንቨስትመንት ስም እራቁቷን እያስቀራት ባለው አላሙዲ አማካኝነት ለአምስተኛ ግዜ ቨርጂኒያ አሌክሳንድሪያ ውስጥ በሚገኘው ማውንት ቨርነን ሃይ ስኩል ከጁላይ 3 እስከ ጁላይ 9 የሚካሄድ የመከፋፈያ ዝግጅታቸውንአዘጋጅተዋል።

በዚህ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ማንኛውም አገር ወዳድ ባለመካፈል ወገናዊነታችሁን እንድታሳዩ ጥሪአችንን እያስተላለፍን፤ በተጨማሪም አርቲስቶቻችንን ክብር የሰጣችሁ ወገናችሁን ፀረ ኢትዮጵያ በሆነ ዝግጅት ላይ ባለመካፈል አጋርነታችሁን አሳዩ እያልን፤ በዚህ የደም ዝግጅት ላይ የወገናችሁን እልቂት ችላ ብላችሁ በምትሳተፉ አርቲስቶች ላይ ማህበረሰቡ በማናቸውም ዝግጅቶቻችሁ ላይ ማእቀብ (boycott) እንደሚያደርግባችሁ ከወዲሁ ልትረዱት ይገባል ።

ይህንኑ ዝግጅትም በመቃወም በዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ሀገር ወዳዶች የተለያዩ የተቃውሞ ዝግጅቶች ያዘጋጁ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን።

የዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል!!!

 

Filed in: Amharic