>
5:13 pm - Monday April 18, 8467

እውን እነ ሌ/ኮ መንግስቱ ሃ/ማሪያም የዛሬ 25 አመት ከአገር ሲወጡ ፓይለቶቹን አሰገድደው/ ፕ/ቱ ተገደው ነበር? [ታምሩ ገዳ]

“ ሻለቃ ደመቀ ባንጃው አውሮፕላኑ ውስጥ እንደ ዶሮ ጠምዝዘው እንዳይገሉኝ ፈርቼ ነበር” ረዳት አብራሪው ያሬድ ተፈራ

Mengistu Hailemariam by Tamiru Gedaየቀደሞው የኢትዮጵያ ርእሰ ብሄር የነበሩት ሌተና ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም የቱን ያህል ወደድናቸውም ፣ጠላናቸውም ፣የታሪክ አጋጣሚ ይሁን ፣የእድል፣ አሊያም የብልጣብልጥነት ሚዛኑ ማየል፣ ኢትዮጵያን በጥሩ ይሁን፣ በመጠፎ፣በጡጫ ፣አሊኣም በፍቅር ፣ በአንድነት ይሁን በደም ማፍሰስ ለድፍን አስራ ሰባት አመታት መግዛታቸው የምናውቅ እናውቃለን ። ነገሩ የቅርብ ጊዜ ታሪክም ነው።

ታዲያ እኚያ ብዙዎች ዛሬ ድረሰ ሰማቸውን በተለያዩ መድረኮች በመጥፎ/በጥሩ የሚያነሷቸው ፕ/ት መንግስቱ ሃይለማሪያም በሰልጣን ዘመናቸው ማክተሚያው አቅራቢያ በደጋፊዎቻቸው አምነት “ቆራጡ እና ረመጡ መንጌ ከወንበራቸው ስር ሆነው ከኢትዮጵያ መሬት ላይ አንድ ጥይት እና አንድ ሰው እስኪቀር ድረስ የሰማእትነት ጽዋ የቀበላሉ እንጂ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ለገንጣዮች ፣ለእሰገንጣዮች እና ለበላተኞች ጥለው አይኮበልሉም /አያድረጉተም”በማለት ሽንጣቸውን ገትረው ለፕ/ቱ ያላቸን ልዩ አክብሮት ዛሬ ድረስ በማህበራዊ ደህረ ገጾች እማካኝነት ሲገልጹ ማየት እየተለመደ መጥቷል። ለምሳሌ ያህል ባለፈው አመት በሊቢያ ላይ 30 የሚጠጉ ወንደሞቻቸን በአሸባሪው በአይሲስ ሲገደሉ አዲስ አበባ ላይ ለተቃውሞ ከወጡ ት መካከል”መንጌ አተመጣም ወይ መንጌ አተመጣም ወይ “ በማለት “የ ኢሃዲግ መንግስትን በአስጠቂነት የፕ/ት መንግስቱ አገዛዝን ደግሞ በተበቃይነት’ ሚዛን ለማስቀመጥ መሞከራቸውን ታዘበናል ።
ታዲያ ያ ሁሉ የተባለላቸው እርሳቸውም ቢሆኑ ስልጣን በመልቀቅ በኩል ፍንጭ ሳያሳዩ ለአስር አመታት በሰልጣን ላይ የቆዩት ፕ/ት መንግስቱ ዛሬ ወደ ሃራሬ/ዙምባባዊ ለመሰደዳቸው ምክንያቱ የውስጥ ጫና(መጠነኛ / ውስጣዊ መፈንቅለ መንግስት?) ወይስ የውጪ ሃይሎች(የእነ አሜሪካ )ግፊት አሊያም የርሳቸው በፖለቲካው ተሰፋ መቁረጥ ሳቢያ ይሆን? ብሎ መጠየቅ ታሪክን ለማወቅ እና ሃሳብን ለማንሸራሸር መጠቀሙ አሌ አይባልም።

በሳምንቱ መጀመሪይ ላይ ኢትዮጵያ ነክ ዜናዎችን ሰዳሰስ ከ አንድ የመረጃ መረብ ላይ “ሌ/ኮ መንግስቱን ይዘው ከአገር የወጡት ካፒቴን በአወሮፕላኑ ወስጥ የሆነውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲነግሩን” በሚል ርእስ ምንጩ ድሮ (ቀደመ 1983 አም)ህዋት/ኢሀዲግ ኢትዮጵያን ሳይቆጣጠር የቡደኑ ዋንኛ የፕሮፓጋንዳ አካል የነበረው እና ዛሬ በግል ራዲዮ ስም ብቅ ያለው ራዲዮ ፋና/ፋና ኢፍ ኤም 98.1 ዘውትር አርብ ከ9.00 እስከ 11.00 ሰአት በሚያቀርበው “የደራ ጫወታ” በሚለው በጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ እና አርቲስት አዜብ ወርቁ የተሰናዳ ፕሮግራም መሆኑን ተመለከትኩኝ ።ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ25 አመት በፊት በወረሃ ግንቦት 19 83አም ምን ታሪክ ተካሂዶ ነበር ? በሚል መጠይቅ ዙሪያ ያውጠነጠነ ነበር ።

በፕ/ት መንግስቱ ወደ ሃራሬ መሰደድ ዙሪያ የደራ ጫወታ እንግዳ ሆነው በእለቱ የቀረቡት በወቅቱ ረዳት የአውሮፕላን አብራሪ የነበሩት የአሁኑ ዋና ፓይለት ካፒቴን ያሬድ ተፈራ ለ ደራ ጫወታ የራዲዮ ፕሮግራም ታዳሚዎች ወጋቸውን ሲያቋድሱ ሰምቻለሁ። እኔም ከፊሉ ቃለ ምልልስን በወፍ በረር ለመቃኘት ሞክሪያለሁ ። ” ነገ ጠዋት / ማክሰኞ ግንቦት 13 /1983 አም በጣም ወሳኝ( VIP)በረራ አለህ ተባልኩኝ። በበነጋታው ከአውሮፕላን ጣቢያ ስደርስ የሚሄዱት ባለሰልጣን ሌ/ጂ ተሰፋዮ ገብረ ኪዳን እንደሆኑ እና ጉዞውም ወደ ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እንደ ሆነ ተነገረኝ። ለጉዟችን የተሰጠን ነዳጅ ግን የ45 ደቂቃ ከሚፈጀው ብላቴና ማሰልጠኛ ከሚሰፍርልን በላይ ነበር ። እኔም ለምድን ነው ይህ ሁሉ ነዳጅ የሚያሰፈልገው? ብዬ ጠየቅሁ።” የሚሉት ረዳት አብራሪው ያሬድ ተፈራ በወቅቱ ውዥንብሮች እንደ ነበሩ በማውሳት በጊዜው በርራውን የሚፈቅዱት/የዲስፓቸ ር ሃላፊው “በረራው ምስጢራዊ በረራ ነው። ከብላቴና በሁዋላ አ/አ ላይ ሳታርፉ በቀጥታ ወደ አስመራ ተበራላችሁ ።ከአስመራ በሁዋላ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ነው “ ተባልን ። አወሮፕላኑ በተለምዶ ለ ልዩ እንግዶች(ቬ አይ ፒ) የሚቆመው ከተለየ ቦታ ሲሆን የዚያን እለት ግን ከጥገናው ክፍል /ሃንጋር ውስጥ ነበር።ከ7.30 ሰአት በላይ የሚያስበረን ነዳጅ ተቀዳልን/ፉል ታንክ ነበር። እኛም ለጉዞ በዝግጅት ላይ ሳለን በአንዲት የትራፊክ ፖሊስ ሞተር ባይስክል የተመሩ 3 ላንድ ክሩዘር መኪኖች መጡ ። ልዩ እንግዳው የተባሉት ሌ/ጄ ተስፋዩ ገ/ኪዳን ሳይሆኑ ፕ/ት መንግስቱ ሃይለማሪያም ነበሩ። ዋናው ፓይለትም ካፒተን / ኮለኔል መኮንን አደላ በደምቡ መሰረት ከአውሮፕላኑ ወርደው ለፕ/ት መንግስቱ ሰላምታ አቀረቡላቸው ። በወቅቱ ዋናው ካፒቴን መኮንን ውስጣቸው የመረበሽ ስሜት የታየባቸዋል ። ሰባት የሚሆኑ የወታደር የደምብ ልብስ የለበሱ፣ የጦር መስሪያ የታጠቁ ጠባቀዎቻቸውን እና ፕ/ት መንግስቱን ያሳፈረችው ዳሽ -5 የበረራ አወሮፕላን ከሁለት አስተናጋጆቿ ፣ከ ሁለት ቲክኒሻኖቿ እና ከሁለት አብራሪዎቿ ጋር በመሆን በረራውን በአዲስ አበባ የሰአት አቆጥጠር ከጠዋቱ 2.30 (8.30am) ላይ ከምድር ወደ ሰማይ ተምዘገዘገች ። ጉዞም ወደብላቴና ተባለ። “ብላቴን የጦር ማሰልጠኛ ለመድረስ ስንቃረብ ዋናው ካፒተን መኮንን ባሰቸኳይ እንደሚፈለጉ ከሻለቃ ደመቀ ባንጃው በኩል ተነገራቸው ።”ይላሉ ረዳት ፕይለቱ ያሬድ።
Mngsitu Hailemariam by Tamriu Geda 2በመቀጠልም ካፒቴን መኮንን ጉዞው ወደ ብላቴና ማሰልጠኛ ሳይሆን “ ጓድ ፕ/ት መንግስቱ ናይሮቢ/ኬኒያ አስቸኳይ ሰብሰባ አለኝ ወደ ዚያ ውሰዱኝ ብለዋል ሲሉ ብሰጭት ብለው ነገሩኝ።” ይላሉ ረዳቱ ፕይለት ያሬድ። በወቅቱ ከዋናው ካፒቴን መኮንን እንደሰሙ የሚናገሩት ያሬድ “ዋናው ካፒቴን ካርታ የለኝም ቢሉም አንተ ደግሞ የኢትዮጵያን ካርታ እንደ እጅህ መዳፍ አይደል የምታውቀው ? በዚህ በሩዶልፍ ሀይቅ በኩል ትሄዳለህ አሉኝ።እንግዲህ ምን ይሻላል? ሲሉ ጠየቁኝ ። ምንም አይነት የራዲዮ ግንኙነት እንዳናደርግም ማስጠንቀቂያ ተሰጠን ። በአካባቢው ይበር በነበረ በሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን እርዳታ አማካኝነት ወደ ናይሮቢ ግዛት ሰነጠጋ ሻለቃ ደመቀ ባንጃው የራዲዮ ግንኙነት ማድረግ አንድንችል ፈቀደሉን ። የበረራውን ምንነት የማያውቁት የኬንያ የአየር ተቆጣጣሪዎች /አቪዩሽን ባለሰላጥናት ማነነታችንን ሲጠይቁን በውስጣቸን ቪ አይ ፒ እንደጫንን እና ወደ ናይሮቢ እንድንጓዝ መገደዳቸንንም ጨምረን ነገርናቸው ። የኬኒያ የአቪዪሽን ባለ ሰልጣናቱም ከዋናው ተርሚናል ፈቀቅ ብለን እንድናርፍ ፈቀዱልን ። ሞተሩ ሳየጠፋ እንድናቆም ከ እነ ሻለቃ ደመቀ ተነግሮን በወቅቱ በናይሮቢ /ኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲጠሩ ተነገረን። አምባሳደሩን በመጠባበቅ ላይ ሳለን ተክኒሽኖቻችን አውሮፕላኑን ፍተሻ ሲያደርጉ አንዱ ጎማ ተንፍሶ ነበር ። እኔም ደነገጥኩኝ። ተክኒሻኖቹ አደጋውን በመጋፈጥ ሞተሩ ስይጠፋ ጎማውን ቀየሩት። ብዙም ሳይቆዩ ፕ/ት መንግስቱ በጥቁር ማርቸዲስ ትወሰዱ ።እኛም እዚያው ሳለን የፕ/ት መንግስቱ ከአገር መወጣትን በትመመለከተ በናይሮቢ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስቴሽን ሹም ነገሩን ። የፕ/ቱ ሁለቱ ጠባቂዎቻቸው ግን ከአውሮፕላኑ አጠገብ በመሆን እና እኛን በማስወረድ አውሮፕላኑ ለፕ/ቱ ብቻ መሆኑን ነግሩን ። ፕ/ት መንግስቱ ወይም ዳሽ- 5 አወሮፕላን ሲሉም ዛቱብን ።እኛም በናይሮቢው ኢንተር ኮንቲኔታል ሆቴል እንድናርፍ ሲደረግ የፕ/ቱ ዋና አጃቢ የነበሩት ሻለቃ ደመቀ ባንጃው ‘ብሞተም አገሬ ልሙት’ ብሏል፣ከ እኛ ጋርም ወደ አገር ቤት እንደሚመለሱ ለካፒቴን መኮንን ነገሯቸው ። እኔ ደግሞ የሻለቃ ደመቀ ባንጃው ከእኛ ጋር ወደ አገር ቤት አብሮ መመለሰን በጣሙን ፈርሁ። ምክንያቱም ሻለቃው ብዙ ወታድራዊ ሰልጠና የወሰዱ እና የዳበረ የካራቴ ሙያ ያላቸው በመሆናቸው እንደ ዶሮ አንገቴን ጠምዝዘው እንዳይገድሉኝ ስለፈራሁዋቸው ነበር ። “የሚሉት ካፒቴን ያሬድ ሻለቃ ደመቀ ለምን ወደ አገር ቤት ለመመለስ ወስኑ? ከ ፕ/ት መንግስቱ ጋር ለምን ወደ ሃራሬ /ዙምባብዊ አብረው አልተሰደዱም ነበር ? ለሚለው የጋዜጠኖቹ ጥያቄ ሲመልሱ”ብዙ አብሬዎት ትጉዣለሁ ። ጥሩንም ሆነ ደጉን ጊዜ አሳልፈናል። አሁን ግን ሰደት በቃኝ ። መሞቴ ላይቀር ልጆቼን እና ቤተሰቤን አይቼ አመጣልሁ አልኳቸው ። መንግስቱ በ707 ቦይንግ አውሮፕላን ቻርተር አድርገው ጠባቂዎቻቸውን አሰከትለው ወደ ሃራሬ ነጎዱ ።”አሉኝ። በእኔ በኩል በሻለቃ ደመቀ ባንጃው እንደገና እንዳንጠለፍ ሰግቼ ነበር።” ያሉት የ ያኔው እረዳት የአሁኑ ዋና ካፒቴን ያሬድ ላለፉት 25 አመታት ከጋዜጠኞች በኩል የቀረበላቸው ጥያቄ ባይኖረም እራስቸው ግን “ሰላማዊ የአውሮፕላን ጠለፋ”ያሉት ያንን አጋጣሚ ካጓደኞቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚይወጉት ስይገልጹ አላለፉም።
የዚህ ሁሉ መላ ምት እና ምስጢራዊ ጉዳዩ ማጠነጠኛ የሁኑት ፕ/ት መንግስቱ በበኩላቸው በወቅቱ ወደ ኬኒያ ያመሩት ሻቢያ የአሰብ ወደብን ለመቆጣጠር በመቃረቡ በጅቡቲ፣ በሶማሊ ላንድ እና በሞምባሳ /ኬኒያ በኩል የጦር መሳሪያ ለማስገባት እና የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ለማድረግ ለመነጋገር እንደነበር እና ናይሮቤ ሲደረሱ ግን ሁኔታዎች ተለዋውጠው በዚያው እንዲቀሩ በቀደሞ ጓዶቻቸው ደባ እንደተፈጸመባቸው እብዝተው ይናገራሉ። በሌላ በኩል ለመንግስቱ እና ለቤተሰቦቻቸው የፖሊቲካ ጥገኝነት እሰከ አሁን ድረስ የሰጠችው የዙምባብዊ እድሜ ጠገቡ ፕ/ት እና የ መንግስቱ ሃይለማሪያም የቀርብ ወዳጅ ፕ/ት ሮበርት ገብሬል ሙጋቤ “ፕ/ት መንግስቱን ወደ ሃራሬ በመወሰድ እዚያው እንድታሰቀምጣቸው እና ለወለታውም ዋሽንግተን እና ሸሪኮቿ ገንዘብ እንደሚከፈሉ ቃል ገብተው ቢሆንም ፕ/ት መንግስቱ ሃራሬን ከረገጡ በሁዋላ ግን ሁሉም ነገር የውሃ ሽታ መሆኑን ሙጋቤ አምርረው መናገራቸው ይታወሳል ። በሰልጣን ዘመናቸው ከ 500ሺህ በላይ የንጹሃን ሰዎች ህይወት እንደጠፋ እና ለወንጀሉም መንግስቱ ተጠያቂ ተድረገው በ ወቅቱ የአ/አ ገዢዎች እንደሚፈለጉ እና ሃራሬም ፕ/ት መንግስቱን አሳልፋ እንድትሰጥ ጥያቄ ቢቀርብላትም ፕ/ት ሙጋቤ ግን መንግስቱ አሁንም ቢሆን የዙምባብዊ እንግዳ በመሆናቸው ተላልፈው እንደማይሰጡ ይናገራሉ። ፕ/ት መንግስቱም በተለያዩ ጊዜያት የተባሉት ወንጀሎችን ያለመፈጸማቸውን የተናገሩ ሲሆን የፕ/ቱ የቅርብ ወዳጃቸው የሆኑት እና በዙን ጌዜ በሰልክ የሚያገኟቸው ብርጋዴር ጄነራል ታመነ ድልነሳው በ2010 አኤአ የሄንኑ ጥያቄ በተመለከተ ከምድረ አሜሪካ ከላስ ቪጋስ ከተማ ዘወትር እሁድ ምሽት ላይ ከሚተላለፈው ከህብር ራዲዩ የቀረበላቸው ሲሆን ብ/ጄ ታመነም “ ፕ/ት መንግስቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ሲመጣ ያለማንም አስገዳጅነት ወደ ኢትዮጵያ መጥቼ ለፍርድ እቀረባልሁ በለውኛል ።” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል ።
ኒዮዮርክ ታይምስም በወቅቱ የፕ/ት መንግስቱ ስደትን በውተመለከተ ባለቤታቸው ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻው የቤት እቃዎችን ለማሰንዳት እና ለሁለት ልጆቻቸው በ አንግሊካል ቅዱስ ዮሃንስ ኮሌጅ እንዲማሩ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ሲሉ ለሁለት ወራት ሃራሬ ከተማ ውስጥ ቀደም በለው ደፋ ቀና ሲሉ መክረማቸውን በዙምባብዊ የኢትዮጵያ ማህበረስብን ዋቢ አድረጎ ዘግቧል። ታዲያ ይህ ሁሉ እየተባልን ሳለን ይህ ሁሉ እየተነገረን ሳለን የማንኛውን ወገን መረጃን እንመን?። ወያይት አይከፋም፣ ብዥታንም ያጠራል።

Filed in: Amharic