>
5:13 pm - Monday April 19, 4506

የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በደረሰበት ጫና ከአገር ተሰደደ፣ በአገር ቤት በጋዜጣው ስራ አስኪያጅ ላይ ፖሊሶች የግድያ ዛቻ አድርሰውበታል [ህብር ሬዲዮ]

Muluken-tesefaw-hiber-radio

(ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) በአገር ቤት የሚታተመው የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሙሉቀን ተስፋው በሚደርስበት ተደጋጋሚ ጫና ባለፈው ሳምንት ከአገር ወጥቶ የተሰደደ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በስዊድን ጥገኝነት መጠየቁ ታውቋል። ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በቀለም ቀንድ ዋና አዘጋጅነቱ ብቻ ሳይሆን ከቀለም ቀንድ በፊትም ይሰራባቸው በነበሩ የፕሬስ ውጤቶች ላይ የሚሰራቸውን ዘገባዎችና የሚያወጣቸውን ጽሑፎች ተከትሎ ተደጋጋሚ ጫና ይደርስበት እንደነበር ለማወቅ ተችላል።

የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በቅርቡ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በወልቃይት ሕዝብ የሚፈጽመውን የሰብኣዊ መብት ረገጣ ቦታው ድረስ ሄዶ ያጠናቀረውን ዘገባ ተከትሎ፣በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ መሰረት በማድረግ የቀረቡ ተከታታይ ዘገባዎች በወጡ ቁጥር ተደጋጋሚ ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስበት ስለነበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ጫና እየበዛ መምታት ለስደት እንደዳረገው ያገኘነው መረጃ ይገልጻል።

<< የክፉ ሰው ሽንት>> በሚል ርእስ በ2014 መጽሐፍ ጽፎ ለንባብ ያበቃው ጋዜጠኛ ሙሉቀን በአሁኑ ወቅትም በቀጣዩ ሰኔ ወር የሚወጣ ሁለተና መጽሐፉን ጽፎ መጨረሱም ታውቋል። ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በአሁኑ ወቅት ከሚሰራበት የቀለም ቀንድ ዋና አዘጋጅነት በተጨማሪ ቀድሞ በኢትዮ ምሕዳር ጋዜጣ በተሌአዩ ጊዜያት በአገር ቤት ያለውን የሰብኣዊ መብት ረገጣ የሚአጋልጡ ሰፊ ዘገባዎችን ችምር ሲአቀርብ መቆቱ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም በሙያው ሳቢያ በ2013 ታስሮ ከፍተኛ ድብደባና እንግልት ደርሶበት እንደነበር በጊዜው ኣለም አቀፍ የሰብዓዊ መብትና የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች የሆኑት አምንስቲ፣ሲፒጄና ፔን ኢንተርናሽናል ሪፖርት ማውታታቸው አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪአጅ ጋዜጠኛ አበበ ውቤ ባለፈው ሐሙስ በአዲስ አበባ ሲ.ኤ.ም. ሲ አካባቢ ማስተር ፕላን ሕጋዊ ነበሩ ቤቶችን በከፊል ሲፈርሱ ለማየት በመገኘቱ በሰባት ፖሊሶች ተይዞ ለሰዓታት ታስሮ መለቀቁንና እንደሚገድሉት እንደዛቱበት ለህብር ሬዲዮ ባለፈው ዕሁድ ቃለ መጠይቅ መስጠቱ አይዘነጋም።

በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ፋሲል ተካልኝ ሚያዚያ 6 ቀን 2008 አዲስ አበባ ፖሊስ አካባቢ ምሽት ላይመሳሪአ በታጠቁ በተፈጸመበት ድብደባ ራሱን ስቶ ከመንገድ ተጥሎ ወደ ሆስፒታል መወሰዱንና ሁለት ሰው ሰራሽን ጨምሮ ስድስት ጥርሶቹ መርገፋቸውን ራሱ የሰጠውን ምስክርነት ተጠቅሶ በዘሐበሻ ድህረ ገጽ መዘገቡ አይዘነጋም።

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ከአገር ከመውጣቱ በፊት ከህብር ሬዲዮ ጋር በወልቃይት የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ተያይዞ ቀርቧል።

Filed in: Amharic