>

የኢትዮጵያ ወይንስ የትግራይ አየር መንገድ? [ይሄይስ አእምሮ]

Old Ethiopian Airlines logoየ2008ን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ አንድ የኢትዮጵያ ይሁን የትግራይ ውሉ ባልታወቀ አየር መንገድ ውስጥ የሚሠራ ሰው በቤቱ ምሣ ጋበዘኝ። ተራ ጎረቤቱ እንጂ የሰማሁትን በሆዴ የማላሳድር ወሬ አራጋቢ መሆኔን አያውቅም። በሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት በቀድሞው አጠራር ስለኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ደግሞ ስለ”ትግራይ አየር መንገድ” እየተንገፈገፈ ሲናገር እንደማንኛውም ተጋባዥ አደመጥኩ። የምፈልገውን ወሬ ከጨበጥኩ በኋላ የተከፈተልኝን ቢራ እንኳን በቅጡ ሳልጨርስ ወደቤቴ አመራሁ – እንደልማዴ ልጫጭር።

ኢትዮጵያዊ የሆንክና አሁን የምነግርህን ከአሁን በፊት ያልሰማህ ሁሉ ይህን የወያኔዎች ቅሌት ልብ ብለህ ስማ! ኢትዮጵያ ዳግመኛ እንዳታንሠራራ ሆና በወያኔ መዶሻ እየተቀጠቀጠች መሆንዋንም አስተውል፤ ልጆችህ ሀገር አለን ብለው የማይኮሩባት አዲስ ኢትዮጵያ መፈጠሯንም ተገንዘብ፤ በተበተንክበት የስደት ዓለም ጠፍተህ እንድትቀር የተፈረደብህ ተስፋቢስ ትውልድ መሆንህን አትርሣ። ስለአየር መንገዱ የሚነገረው በባሰ ሁኔታ በሌሎች ላይ የሚሠራበት ወያኔያዊ አሠራር ነው – ለ25 ዓመታት የተሠራበት። በዚህ ተቋም እንዲህ የተሠራ በሌላው ምን ሊያቅታቸው?

ባለፈው ሰሞን አየር መንገዱ 27 ሆስተሶችን (የሴት አስተናጋጆችን) አስመርቋል። በሚያስገርም ሁኔታ ሃያ ሰባቱም ትግሬዎች ናቸው። አዲስ አበባን የማያውቁና ብዙዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ ቤተሰብ የሌላቸው ፍጹም ባላገር ሴቶች ናቸው። የተቀጠሩት ሁሉም ከትግራይ ምድር ነው። ለመሃላ እንኳን አንድም የሌላ ዘውግ አልተቀላቀለባቸውም – ቴክኒሻንና አብራሪም ሲመለመል እንዲሁ ነው። ከነዚህ ሆስተሶች ብዙዎቹ አማርኛ ቋንቋ አይችሉም፤ እርግጥ ነው – ከልጅነት እስከ ዕውቀት ዘመናቸው አማርኛ ከሚወገዝበት ክልል ተወልደውና አድገው የመጡ ወጣቶች በመሆናቸው በነሱ አይፈረድም። ነገር ግን የአየር መንገዱ አንደኛው የሥራ ቋንቋ የሆነውን አማርኛን ባለመቻላቸው ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ – ማኅበራዊነት (ሶሻላይዜሽን) ስለሚጎድላቸው ደግሞ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር በቀላሉ መግባባት ካለመቻላቸውም በተጓዳኝ ቋንቋ አለመቻላቸው ሥራቸው ላይ ትልቅ አሉታዊ ጫና እየፈጠረባቸው ነው። አንድ ተጨባጭ ምሣሌ እንይ። በእውነቱ ህወሓት የትግራይ ሕዝብ በቀጣይ ታሪኩ እጅጉን የሚያፍርባቸው ብዙ ሰቅጣጭ ተግባራትን እየፈጸመ ነው። ስለወያኔ ትግሬዎች ሁላችንም ማፈር አለብን። ሃያ ሰባቱም ትግሬ? ውይ … ውይ … ውይ …

ባለፈው አንድ ጊዜ ወደ አፋር ዋና ከተማ ወደ ሠመራ አንድ የሀገር ውስጥ በረራ ነበር። አንዷ አማርኛ እንደቁመት ያጠራት አስተናጋጅ ትግሬ “ህጅ አሥመራ ስለተቃሪብና ለቀቦቷቹ አጣብቁት” በማለት ለተሣፋሪዎች ማስታወቂያ በመናገሯ ተሣፋሪዎች አውሮፕላኑ ተጠልፎ አሥመራ ገብቶ ነው በሚል ተደናግጠው ክው ይላሉ። በኋላ ግን የቋንቋ ችግር መሆኑ ተነግሯቸው አሥመራ ሣይሆን ሠመራ እንደደረሱ ተገልጾ ይቅርታ ተጠይቀዋል – ተሣፋሪዎች። ሐሰት እንዳይመስልህ ሁሉም የአየር መንገዱ ሠራተኛ ሰምቶ የሚያላግጥበት እውነተኛ ታሪክ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱ “የትግሬ” ወይም በተወራራሽ የቃላት አጠቃቀም “የትግራይ አየር መንገድ” ነው የሚባለው። በዚህ ዓይነት መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ትግሬነትን አስጠልተውት እንዳይቀሩ እፈራለሁ – ከአሁኑ አንዳንድ ሁኔታዎች ተነስቼ እንደምታዘበው ይህን ጉዳይ በሚመለከት ችግር የለም ብሎ ራስን ማታለል የዋህነትና ከኃላፊነትም የመሸሽ ዝንባሌ ይመስለኛል። ብዙ ነገር መሠራት ሊኖርበት ነው – እንዴ? አያያዛቸው በጣም ያሣፍራል እኮ!

ከ27 አስተናጋጅ አንድ ሰባት ያህል እንኳን ለማስመሰል ከሌላው ብሔር ቢቀላቀል ምን ነበረበት? ይህን ምን ይሉታል? ምን ዓይነት መታወር ነው? ጭንቅላታቸው ውስጥ ጭቃ ነው ንፍጥ የታጎረው? የምትቀርቧቸው በተለይም ጤናማ ነን የምትሉ ትግርኛ ተናጋሪ የሆናችሁ የትግራይ ልጆች እስኪ ጠይቋቸው። ከሰው አይደለም ከእንስሳም እንዲህ ዓይነት ድንቁርና አይጠበቅም። በስመ አብ!

በሌላ ቦታ በዓይኔ በብረቱ ያየሁትን ነገር ሳልረሳው ጣልቃ ላስገባ መሰለኝ። ቦታው ሲቭል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሚባለው ድንጋይ ማምረቻ የትምህርትና የ“ኢንዶክትሪኔሽን” ማዕከል ነው። ከአንድ የመንግሥት ተብዬ መሥሪያ ቤት በስኮላርሽፕ ወደዚህ ማዕከል የተላኩ ሰዎች ስም ዝርዝር ተለጥፎ አየሁና ማንበብ ጀመርኩ። አንብቤ ስጨረስ ደነገጥኩ። ከተኮለኮለው ወደ ሃያ የሚጠጋ የስም ዝርዝር ውስጥ አንድም አማራ ዜጋ የለም። ሦስት ይሁኑ አራት ገደማ የደቡብና የኦሮሞ ስሞች አሉ – ቀሪው በሙሉ ከሐጎስና ከአብረኸት ውጪ ሌላ የለም። አዘንኩላቸው፤ አንዳንዴም አዕምሮው በዘረኝነት ልምሻ፣ በጠባብነት ምችና በድንቁርና መብረቅ ለተመታ ሰውም ማዘን መጥፎ አይደለም – “እንደነዚህ አታድርገኝ” ብሎ መጸለይ ከተመሣሣይ የአስተሳሰብ መካንነትና የአመለካከት ድውይነት ይሠውራል። ረጋ ብለው ሲያስቡት እነዚህ ወንድሞቻችን የገቡበት የዘረኝነት አዘቅት ከመለኮታዊ መቅሰፍት የማይተናነስና በቁም ነፍስ ይማር የሚያሰኝ ትልቅ አደጋ ነው። እናም ለነሱም እንዘን።

የአየር መንገዱ ዘበኛና ሴኪዩሪቲ ሁሉ ከትግራይ ነው የሚቀጠረው – ሁሉም የአየር መንገዱ የሥራ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በትግሬ ሊሸፈን የቀረው ጥቂት ጊዜ ነው – ጥረቱም በስፋትና በጥልቀት ቀጥሏል። የመለስን ራዕይ እውን ለማድረግ የአየር መንገዱ የትግሬዎች የማኔጅመንት አካል ሌት ከቀን እየደከመ ነው። ጥቂት ወታደሮች ከጋምቤላ ተቀጥረው የብሔር ተዋፅዖ ያለ ለማስመሰል ይሞክራሉ እንጂ፤ ሌላው ሁሉ ከትግራይ ነው የሚመጣው፤ እነዚህ ወታደሮችም አዲስ አበባንና የትግሬውን አገዛዝ መላመድ ስለሚቸግራቸው በየጊዜው ይጠፋሉ። እግዚኦ የሚያስብል ዘመን ውስጥ እንገኛለን።

የሚገርመው ደግሞ ሌላው ዜጋ ሁሉ ለነዚህ እፍኝ ለማይሞሉ አጭበርባሪና ዘረኛ ትግሬዎች ሁሉን ነገር አስረክቦ እግሩ ባወጣ በመሰደድ በተዋራጅነት ለመኖር ራሱን ዝግጁ ማድረጉ ነው። ቆንጆ ሀገሩን ለወሮበላ አስረክቦ ራሱን የሚያጠፋና በከንቱ ማስኖ የሚቀር ዜጋ ቢኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ ብቻ ነው። የነሱን ዘረኝነት ስናገር እኔም ዘረኛ የሆንኩ እየመሰለኝ አፍራለሁ – እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ሰው ዘረኛ ሊሆን እንደማይችል ሳስብ ግን እጽናናለሁ። በተለይ አማራ እስካሁን ያልሆነ ካሁን ወዲያ ዘረኛ ይሆናል ብዬ አልገምትምና ከኢትዮጵያዊነት ብቸኛ የመታገያ ሥልትና መንገድ ውጪ በወያኔ ቦይ ገብቶ እንዳይዳክር አደራችሁን እላለሁ። በርግጥ አማራ ሆኖ ስለአማራ አለማሰብ ብልኅነት አይደለም፤ ወዶና ፈቅዶ ባልተፈጠረበት፣ ይሁነኝ ብሎ ባልሆነበት ማንነቱ ሲጨፈጨፍና ሲሳደድ እንኳንስ ተመሣሣይ ዕጣ የተፈረደበት ዜጋ ሌላውም ሊረዳውና ከዕልቂት ሊታደገው ሰብዓዊና ዜግነታዊ ግዴታ አለበት። አማራን እያስጨረሰው ያለው በአማራነት ራሱን ለመፈረጅ መቸገሩ ነው፤ ከጥንት ከጧቱ ሰውነቱና ሥነ ልቦናው ሲታነፅ በኢትዮጵያዊነት እንጂ “ትግራይ አደይ፣ አምኻራ ሀድጊ፣ አምኻራን ተመንን እንተረከብኻ ቀዲምካ ንአምኻራ በሎ …” እየተባለ በዘፈንም በሽለላና በቀረርቶም በወንድሞቹ ላይ እንዲዘምት በአማራ ታሪካዊ ጠላቶችና በጣሊያን የባንዳ ልጆች እንደተገደደው የትግራዩ ወንድሜ፤ ከልጅነቱ ጀምሮ የሚኮተኩተውና የሚያበረታታው አክራሪ ሰው ቢኖር ኖሮ፤ አማራ ምን ሊሠራ እንደሚችል እኔ ሣልሆን ወያኔዎች ራሳቸው አሣምረው ያውቃሉ።

ተኝቷል የሚባለው የአማራው ልሂቅ እንኳን ይህን በአማራው ላይ እየወረደ የሚገኘውን ወያኔያዊ ውርጅብኝ በማመንና ባለማመን መካከል ሆኖ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ዝም ብሎ ተቀምጧል – አብዛኛው። ስለአማራው መብት ቢጮኽ ከወያኔዎቹ ያነሰ መስሎ ስለሚታየው ይመስለኛል በዝምታው የጸናው። ለማንኛውም የነበረ ያልነበር ይሆናል – ምንም ነገር ባለበት አይቀጥልም፤ የመደንቆሪያ ጊዜ አለ – የመስሚያ ጊዜም አለ፤ የልደት ቀን እንዳለ ሁሉ የመሞቻ ቀንም አለ፤ ለጥጋብ ቀን አለው – ለረሃብም እንዲሁ። አሁን ያለ የሚመስለውም ነገ የለም። ሞኝነትም ብልጥነትም ያረጃሉ፤ ይሞታሉም። … የልብ መደፈንን በጊዜ ካልደረሱበትና መድኃኒት ካላገኙለት ግን ዳፋው ተዝቆ አያልቅም።

ከአዲስ አበባ መቀሌ ስትገባ እዚያ ያሉ የአየር መንገዱ ሠራተኞች በግልጽ “እንኳን ወደ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ በሠላም መጣችሁ” ይሉሃል። አፍረህ ዝም ትላለህ። አንድ ሰው ቢናገራቸው በቀጥታ ለዋናው የአየር መንገዱ ሥራ አስኪያጅ ለአቶ ተወልደ ይደውሉና የፈለጉትን እርምጃ ያስወስዱብሃል። አየር መንገዱ የተወልደ የግል ንብረት ያህል – በዚያውም የወያኔ የግል ሀብት ያህል እንጂ፤ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ለማወቅ ብዙ ጉድ ትሰማለህ፤ ታያለህም። ጆሮህንና ዓይንህን ማመን እስኪያቅትህ በትንግርቱ ትገረማለህ። ለካንስ ዕድሜ የሰጠው ብዙ ያያል? በበኩሌ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ሁሉ ወያኔያዊ ድራማ አያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። በጣም ቸኮሉ። ይገርማል – ሰው ሲቸኩል ይሉኝታንና ሃፍረትን ጨርሶ ይረሳል ማለት ነው።

ሠራተኛ ከየትም ሊቀጠር ይችላል – ከጎንደርም፣ ከባሕር ዳርም፣ ከድሬ ዳዋም ተቀጥሮ ሊመጣ ይችላል። ነገር ግን ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ቢመጣ ወያኔዎች ያን ምልምል ተቀጣሪ ትግሬ መሆኑን ሳያረጋግጡ የአየር መንገዱን ግቢ አያስረግጡትም። እጅግ፣ እጅግ በጣም የሚገርሙ “ሰዎች” ናቸው።

በሁሉም የሥራ ዘርፍ የነሱን ሰው ያሠለጥኑና ሌላውን አበሳጭተው ወይም አባረው በነሱ ይተካሉ። የሚተኳቸው ትግሬዎች ደግሞ በአብዛኛው ችሎታም ሆነ ዕውቀት ስለሌላቸው ሥራውን ያበላሻሉ፤ የብዙ ዓመት የሥራ ልምድና በቂ ሥልጠና የሚፈልግን አንድ ሥራ በለብ ለብ ለጥቂት ጊዜ በ”ሠለጠነ” ትግሬ መተካት ደግሞ በተለይ አየር መንገድን በመሰለ ተቋም ሊያስከትል የሚችለው ችግር ከባድ ነው፤ የሰውን ሕይወት በአየር ይዞ ለሚቀዝፍ የአየር ላይ መርከብ የወያኔ ዓይነት አሠራር ሀገራዊ ኪሣራን ማስከተሉ አይቀርም። ኦ … ኦ … ኦ … በጣም ንቀውናል ጎበዝ! “ትንሽ ሰው አያሸንፍህ” የሚባለው ምርቃት እንዴት ትክክለኛ ነው እባክህን! ትንሽ ሰው አሸንፎ ሀገር ያቀናበት ዘመን ደግሞ የትም የለም። ትንሽ ሰው ሲያሸንፍ ሁሉ ነገር ብርቅ ይሆንበትና ሀገር ምድሩን መቆሚያና መቀመጫ ያሳጣል። ወያኔዎችም እንዲህ ናቸው። ትንሽ ሰው ስል ግን በሰውነት አቋም ወይም በሥነ ተፈጥሯዊ የፍጥረታት ደረጃ ምደባ ሣይሆን በአስተሳሰብና ርዕዮተ ዓለም ረገድ ማለቴ ነው። በጂንማ ሁላችን እኩልና የአዳምና የሔዋን ልጆች ነን፤ ግን አንዳችን ቃየልን ሌላኛችን አቤልን እየሆን ለዚህች አጭር ምድራዊ ዕድሜ እንባላለን።

በዚሁ ሰሞን አንዱን የአየር መንገዱን ነባር ባለሙያ እንዲህ አሉት አሉ። “ይህን የያዝከውን ቦታ ልቀቅልን – በጣም እንፈልገዋለን። ደሞዝህን ግን አንቀንስብህም፤ ወደሌላ ቦታ እናዛውርህ። …” እርሱም እምቢ የሚልበት አቅም የለውምና ሳይወድ በግዱ ለቀቀላቸው። ሥራውን ግን እያበለሻሹት ነው ይባላል – ወሬ ተደብቆ አይቀርም መቼም – ከዚያው አካባቢ የሚናፈስ ትኩስ መረጃ ነው። ሥራ ሲበላሽ ማየት ደግሞ አያስችልምና ባለሙያው በዳር ሆኖ እያገዛቸው ነው። እነሱ ስለሀገር ባይጨነቁ እርሱ ግን እነሱን አልሆነም።

ኧረ! ሌላ በኢሳት የሰማሁትን ጉድ ደግሞ ልንገራችሁ – ያልተከታተላችሁ ካላችሁ። አንድ ወልቃይቴ ከወንድማገኝ ጋሹ ጋር እየተወያዬ ነው። ወያኔዎች ስላደረሱበት በደልም እያብራራ ነው። እንዴት አምልጧቸው እንደተሰወረባቸው ሲናገር አልደረስኩበትም ወይም አልፎኛል። ያደረሱበት ስቃይና መከራ እጅግ የሚዘገንን መሆኑ እንዳለ ሆኖ፤ ወደ አንድ ገደል ወስደው ምን እንዳሉት ሲናገር ብትሰሙት ከነዚህ ሰዎች ጋር ወደፊት እንዴት እንደምንኖር ግራ በመጋባት ትጨነቃላችሁ። “አየኸው ይሄን ገደል? ዘመዶችህን (ወልቃይቶችን ማለቱ ነው) እያመጣን የምንጥለው እዚህ ገደል ውስጥ ነው። አጥንታችሁ እዚህ ይከማቻል። ትግራይ ነፃ ስትወጣ በማሽን እየፈጨን ለትግራይ የእርሻ መሬቶች ማዳበሪያ እናደርገዋን … ምን አስቸኮለህ፤ አንተንም ገድለን እዚሁ እንጥልሃለን …” ነበር ያለው – ልበ ድፍኑ የወያኔ ካድሬ። ለመሆኑ ይህን ሁሉ ጭካኔ ማን አሰረጸባቸው? ለአማራ ያላቸውስ ጥላቻ እንዴት አይበርድም? ትግራይስ ነፃ የምትወጣው ከማን ነው? ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በምዕራቡ ዓለም ያልተቋረጠ ልዩ እገዛ ማሸነፋቸው ከ25 ዓመታት በኋላም እንደህልም የማይታመን ሆኖባቸዋል ማለት ይሆን? ጥልቅ እንቅልፉን የሚደቃው አማራ በህልማቸው እየመጣ እንዴት ቢያስፈራራቸው ይሆን እንዲህ አቅላቸውን ስተው የሚበረግጉትና በዚህን መሰል የማሰቃያ “ጥበብ” አማራውን የቁም ስቅል የሚያሣዩት?

እነዚህን ጉዶች ሰው ቢያቅተው ፈጣሪ እንዴት አቃተው? በኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ አለአንዳች ዕረፍት ከ25 ለሚበልጡ ዓመታት ጥሬ እንትናቸውን ሲለቁብን፣ በትዕቢትና በእብሪት ተነፍተው እንዲህ ሲያስታውኩብን ምን ነው ሃይ የሚላቸው አንድም ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ አካል ጠፋ? “የኢትዮጵያ አምላክ” እየተባለ የሚንቆለጳጰሰው አምላከ ሰማይ ወምድር ምን ሆኖ ነው እንዲህ በኛ ላይ የጨከነው? ምን ኃጢኣተኞች ብንሆን አለርህራሄ እንደክርስቶስ ይህን ያህል እንድንወገር መፍቀዱ ለምን ይሆን? ሀገረማርያም ኢትዮጵያ በነዚህ ጥፍራም ወያኔዎች ስትጠፋ፣ ባልተገራ ብልግናቸው እንዲህ ሲጨመላለቁብን በውነቱ ፈጣሪ በመንበሩ ካለ እንዴት አስቻለው? በትምህርትም ሆነ በልምድ እዚህ ግቡ የማይባሉ 27 ባላገር ትግሬዎች በዘረኝነት ከአንድ ክፍለ ሀገር ተለቅመው ይህን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የነበረ አየር መንገድ እንዲቀላቀሉና በዘረኝነት ግማት እንዲያከረፉት ከተደረገ፤ በሌላው ማኅበራዊና መንግሥታዊ ተቋምማ ከዚህ የበለጠ ወንጀል እንዴት አይሠራ?

የድፍረታቸው ምንጭ ምን ሊሆን ይችላል? የኛ ፍርሃት ወይንስ የነሱ “ጀግንነት”? የኛ “ትግስት” ወይንስ የነሱ ጀብድ? ምሥጢሩ ምን ይሆን? ጥቂት ሺዎች በብዙ ሚሊዮኖች ዘንድ እንዲህ ግፍ ሊሠሩ የሚችሉበት አገባብ አልገባህ ብሎኝ ተቸግሬያለሁና፤ የሚያብራራልኝ ባገኝ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል። ሕይወት ብቻ ሣትሆን ኢትዮጵያም እንቆቅልሽ ሆነችብኝ – መፈቻው የራቀ እንቆቅልሽ፤ ሀገር የማይሰጥበት ክፍለ ዘመናዊ ምሥጢር። ጥቂቶች በአንደርባቸው ሚሊዮኖችን አፍዝዘው ወደ ተናጋሪ ዕቃነት (ዞምቤነት) የለወጡባት የምትገርም ሀገር – ኢትዮጵያ! ሁሉም ነገር ግራ የሚያጋባበት ሁኔታ የተፈጠረባት አስገራሚ ሀገር። እንደብልኅ በዐርባ ቀን ቀርቶ እንደሞኝ እንኳን በአርባ ዓመት ልብ መግዛት ያልተቻለባት የዘመናችን ባቢሎንያውያን ሀገር – ኢትዮጵያ። ወደኋላ እንጂ ወደፊት የማይሮጥባት፣ ባሉበት ቆሞ መቅረትም ራሱ እርም ሆኖባት ወዳልነበረችበት የጥፋት ዘመን የኋሊት ሽምጥ የምትጋልብ ሀገር – አቢሲንያ።

ለኢትዮጵያ ቆመናል የምትሉ የሰላማዊም ሆናችሁ የብረት ትግል ተቃዋሚዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በውጪም ሆነ በውስጥ የምትገኙ የነፃነት ፋኖዎች፣ … አሁንና ዛሬ ወዴት አላችሁ? ከዚህ የበለጠ ውርደት የት አለ? ከዚህ በላይስ ምን እስኪያደርጉን ትጠብቃላችሁ? ሥጋችንን እስኪበሉ? ደማችንን በስሪንጅ እስኪመጡ? እነዚህ ቫምፓየሮች ከዚህ በላይ ምን እስኪያደርጉን ትጠብቃላችሁ?

“ወደሽን ቆማጢት …” እንዳትሉኝ እንጂ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ትግሬ ይሁን – ለጊዜው ግዴለም እንበል። ግን የተማረና በአግባቡ የሠለጠነ ትግሬ ቢሆን ምናለበት? ወያኔዎች ሆይ! ሁሉንም ዜጎች ከሥራ አውጡና በትግሬ ተኩ፤ ጀምራችሁ እያጠናቀቃችሁት እንደምትገኙት ከዳር እዳር ሁሉንም ሙያዎችና የጥቅም ቦታዎች እናንተው ያዙ – ግን እባካችሁን ሰዎቻችሁ በቂ ሥልጠናና የማኅበራዊ ተግባቦት ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጉ – የምትቃዡባትን የትግራይ “ሪፐብሊክ”ን መሥርታችሁ እስክንገላገላችሁ ድረስ፤ ያው እናንተም እንደኛው ኢትዮጵያውያን መባላችሁ አይልቀረምና ስለናንተ ፀያፍ የዘረኝነት ተግባር እኛም እያፈርንባችሁ ነው – ከሚደርስብን ቁሣዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ባልተናነሰ በእናንተ ምክንያት ሃፍረቱም አሸማቀቀን – እውነቴን ነው – ከናንተ ጋር የአንዲት ሀገር ዜጋ መባሉ ራሱ በበኩሌ ቃላት ከሚገልጹት በላይ እያሣፈረኝ ነው – 27 ሆስተስ ከትግራይ ብቻ? ይህ ተግባር ብቻውን አይደለም ኢትዮጵያውያንን በእንስሳዊነት የጋራ ተፈጥሮ ምክንያት ዓሣማና ጅቦችንም በሃፍረት አንገት ሊያስደፋ የሚችል አጸያፊ ወያኔያዊ ድርጊት ነው (እናንተን ስፖንሰር ያደረጉ ምዕራባውያን ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ይህን ተግባራችሁን አያውቁም አልልም፤ ከነሱም ሆነ ከናንተ ከዚህ የሚብስ ግፍ እንጂ መልካም ነገርን አልጠብቅም – ተፈጥሯችሁን ለአፍታም አትዘነጉምና)። በዋናነት ታዲያ ዐውሬ ትግሬዎችን ከጫካና እልም ካለ ገጠር እያመጣችሁ በአንጻራዊነት ሻል ባለ የሥልጣኔና የንቃተ ኅሊና ደረጃ በሚገኝ ህዝብ ላይ እንደውሻ ጃዝ አትበሉ። ህዝቡን እያስመረሩና እያስለቀሱ፣ የሀገሪቱንም ምስል እያበላሹ ነውና በጣም እየተዋረድን ነው። እርግጥ ነው – ኢትዮጵያን ማዋረድና ከምድረ ገጽ ማጥፋት ትልቁ አጀንዳችሁ መሆኑን እናውቃለን – ግን በቅጡ አጥፉን እባካችሁን። ፕሮፌሽናል በሆነ ሥልጡን መንገድ አጥፉን እንጂ ይህን ያህል የለዬላችሁ ‹ፋራ› አትሁኑ።

ወያኔዎች ፈጣሪንም አግተው እንደያዙ አሁን አሁን መጠራጠር ጀምሬያለሁ፤ እንዲያ ባይሆን ይህን ሁሉ ግፍ እየሠሩ ሃይ የሚላቸው ባልጠፋ ነበር እላለሁ። … በርግጥም ለኢትዮጵያ አሁን ያልታዘነ መቼም አይታዘንላትም። 27 ሰው ከአንድ ቀየ? የመንግሥት ተቋማትን ሁሉ በአንድ ክልል ሰዎች ማስያዝ? ማን ናቸው … እኚያ ስመጥር ፕሮፌሠር አሁን የት ነው ያሉት? የለም፣ የለም … እርግጥ ነው … ትግሬ ሣይሆኑ የሆኖሉሉ ዜጎች ናቸው በወያኔ እየተጠቀሙ ያሉት። ትግሬዎች ምን በወጣቸው? 27 … ወይ መድኃኔዓለም … ምኑን አመጣህብን፤ ምን ጉድ ነው እያሳየኸን ያለኸው … ለማንኛውም እግዜሩን እግዜር ይይለት።

“ሰውነት ቢያብጥ በምላጭ ይበጣል – ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጣል? …” አዎ፣ አሁንም እውነት ነው – “እህል ቢያንቅ በውኃ ይዋጣል፤ ውኃ ቢያንቅስ በምን ይዋጣል?” ፍርዱን ለራሱ ለፈጣሪ ሰጥቻለሁ።

Filed in: Amharic