>

ጸረ ሙስሊሙ እና ጸረ ሰደተኛው እጩ አሜሪካዊው ፕ/ታዊ ተወዳዳሪን ለመግደል የዛተ ታሰረ [ታምሩ ገዳ]

በመጪው ሕዳር 2016 እኤአ አሜሪካ በወቅቱ ፕሬዘዳንቷ ባራክ ኦባማ ፋንታ አዲስ ፕ/ት ለማግኘት የሚያሰችላትን ምርጫ ታካሔዳለች ተብሎ ይጠበቃል። ታዲያ በዚህ መጠነ ሰፊ ገንዘብ እና ጉልበት በሚጠይቀው የምረጡኝ ዘመቻ የተጠመዱት በብዙዎች ዘንድ በአወዛጋቢነታቸው በሰፋት የሚታወቁት የሪፓብሊካኑ እጩ ፕሬዘንዳንታዊ ተወዳድሪው እና ብዙ ደጋፊዎችን እያማለሉ የሚገኙት ቱጃሩ ዶናል ትራምፕቱጃሩ ዶናል ትራምፕ By Tamiru Geda ከዚህ ቀደም “ እናንተ ምረጡኝ እንጂ የፕሬዘዳንታዊ መቀመጫውን ከጨበጥኩ ሕገወጥ የሜክሲኮ ሰደተኞችን አባርራለሁ ሌሎችም ወዲህ ( ወደ አሜሪካ ) ዝር እንዳይሉ ሰማይ ጠቀስ ግንብ አስገነባለሁ፣ ሙስሊሞችም ቢሆኑ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይመጡ ጠበቅ ያለ ህግ አወጣለሁ።” ማለታቸውን ተከተሎ በመላው አለም ማህበረሰብ ዘንድ በተለይ በአሜሪካ በሚኖሩ የላቲኖ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥርስ ውስጥ የገቡት ዶናል ትራምፕ ፖለቲካዊ አቋም ያሰቆጣው የ 20 አመቱ ሲያን ሞርኪ በወዳጆች መገናኛ ዘዴ ገጹ (ቲዊተር አካውንቱ) ላይ”የትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ ተገኝቶ በቦምብ የሚያናውጠው ሰው አለ? ወይስ አኔው ሄ ጄ ላከናው ነው?”የሚል መልእክት አስፍሮ ነበር።

ይህ በተላንትናው እለት በኮንኪቲኪዩት ግዛት የተካሄ ደውን የምረጡኝ ዘመቻን ለማደናቀፍ ሞክሯል የተባለው ወጣቱ ሲያን by Tamiru Gedaወጣቱ ሲያን ምንም እኳን መልክቱን ወዲያውኑ ከገጹ ላይ ቢደመሰሰውም (ዲሊት ቢያደርገውም) ከዚሁ ለጠቅ በማድረግ የሲያን ቤተሰቦቹ አደጋ እንዳይደርስባቸው ወተር ቡሪ ውስጥ በሚካኈደው በትራምፕ የመረጡኝ ዘመቻ ፕሮግራም ላይ እንዳይሳተፉ ማስጠንቀቂያ አዘል በቲዊተር እካውንቱ ላይ ይለጥፋል ።መረጃው ከአሜሪካ የደህንነት ስራተኞች የደረሳቸው የግዛቲቱ የፖሊስ ሃይላት እና የጸረ ሽብር ሃላት በመቀናጀት የሲያን የቲወተር አካውንትን ዱካ በመከታተል ተጠርጣሪው ግለሰብን ከቤቱ ድረስ ዘልቀው በመሄድ ግለሰቡን ወደ እስር ቤት በመውሰድ ከመረመሩት በሁዋላ “ግለሰቡ ለጊዜው በትራምፕ እና በምርጫ ቡድናቸው ላይ ምንም አይነት ቅጽበታው ጥቃት የመውሰድ እቅድ የለውም “ከሚል ግምት አኳያ ተጠርጣሪው ግለሰቡን እሰከ ሚቀጥለው የችሎት ውሎው ድረስ በ 25 ሺህ ዶላር ዋስትና ቢለቀቅም በ ሰው ይህወት እና በንብረት ለይ ጥቃት ለመፈጸም አሲሯል በሚል የመጀመሪያ ዲግሪ የወንጀል ክስ እና ሰላምን ለማወክ ሙከራ አደርጓል በሚል በሁለተኛ ደረጃ የወንጀል ክስ መከሰሱ ታውቋል።

በ ተለያዩ አወዛጋቢ አስተያየቶቻቸው ሳቢያ በርካት አሜሪካኖችን ያሰቆቱት እና የጥላቻ ግንብ የገነቡት ቱጃሩ ትራምፕ በአሁኑ ወቅት የሪፐብሊካኖቹን የምረጡኝ ዘመቻ ሩጫውን በሰፋት እና በሚያሰገርም ሁኔታ እየመሩ ሲሆን እንደው እድል ቀንቷቸው ወደ ሰልጣን ኮርቻው ላይ ጉብ ቢሉ ቃላቸውን የፈጸማሉ? ወይስ ወንዝ ሳይኖር ድልድይ እገነባላችሁዋለሁ እንደሚሉት ታዳጊ አገሮቹ መሪዎች( ጉዳዩ አንዳንድ የእኛንም አገር ፖለቲከኞችን የጨምራል) እንዲያው ለምርጫ ሲባል የህዝቡን ልብ ለማማለል የተጠቀሙት ዘዴ ይሆን? የሚሉ የውይይት ርእሶች በበርካት የምረጡኝ ዘመቻው አድናቂዎች እና የአሜሪካ ወስጣዊ እና ወጫዊ ፖለቲካን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ዘንድ ሰፊ የመወያያ ርእስ ከፍቷል።

Filed in: Amharic