>

ኢሳት ወደ አየር ተመልሷል

ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ የተሰጠ መግለጫ
ታህሳሥ 25/2008
January 4/2016
ኢሳት ወደ አየር ተመልሷል
የኢሳት አስተዳደርየኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ራዲዮ /ኢሳት/ በኢትዮጵያ እና አካባቢዋ ሃገሮች በሁለት ሳተላይት ሲያስተላልፍ የነበረው ስርጭት ቅዳሜ ታህሳስ 9/2008 /December 19/2015/ እና በተከታይ ቀናት መቋረጡ ይታወቃል።ለሁለት ሳምንታት ያህል ከተቋረጠ በሁዋላ ኢሳት አሁን ወደ አየር ተመልሷል። ኢሳት በኢትዮጵያ ምድር እንዳይታይ ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ላለፉት አምስት ዓመታት ተኩል ያደረገውን ጥረት አሁንም በውጭ ባለሙያዎች እና አካላት ድጋፍ የቀጠለ ቢሆንም፣ኢሳት የትኛውንም ጫና በምቋቋም ነጻነቱን ተነፍጎ ለሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚያደርገወ ጥረት ይቀጥላል፡፡ኢሳት አሁን በአዲስ ሳተላይት ወደ አየር የተመለሰ ሲሆን፣በተጨማሪ ሳተላይቶች ስርጭቱን ለማስፋትም በኣንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።
አዲሱ ሳተላይት
SES 5 @ 5 East
Frequency 11919
Symbol Rate 27500 Horizontal
የኢሳት አስተዳደር

Filed in: Amharic