ጌታቸው ይሰራበት ከነበረው መስሪያ ቤት ሲባረር ተመልሶ ወደ መንግስታዊ መስሪያ ቤት ቅጥር ማመልከትን አልመረጠም፡፡ ይልቁንስ አብዝቶ ወደሚወደው የሚዲያ ስራ አጋደለ እንጂ! በዚህም በቀድሞዎቹ መሰናዘሪያ ጋዜጣ እና ላይፍ መጽሄት (በኋላ ስሟ ተቀይሮ ‹ፍቱን› ተብላለች) በአምደኝነት ሰርቷል፡፡ ከዚያም የዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ ለ26 እትሞች ያህል ከሄደች በኋላ በጫና ከህትመት መውጣቷን ተከትሎም ጋዜጣዋን በማህበራዊ ድህረ ገጽ እንድትቀጥል ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ዛሬ ጠዋት ለእስር እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በጋዜጠኝነት ስራው ላይ ደፋ ቀና ከማለት አልቦዘነም፡፡ በተያዘበት ወቅት እንኳ የፍርድ ቤት ውሎ ለመዘገብ ወደ ስራ እያመራ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ጌታቸው በማህበራዊ ሚዲያም ንቁ ተሳታፊ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ጌች ማዕከላዊ በእስር የሚገኝ ሲሆን የታሰረበትን ምክንያት ግን እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም፡፡
ጥቂት ስለ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው[በላይ ማናየ]
Filed in: Amharic