>
5:13 pm - Thursday April 19, 1483

ኢትዮጵያ፡ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ያልፈቀደ በኃይል ለውጥን እንዲቀበል ይገዳዳል![ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም]

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 

.. ታህሳስ 2015 በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ ታላቅ ስፍራን በመያዝ እየተብላላ ያለ አንድ ጥያቄ ብቻ አለ፡፡ 

TTPLF-Victims.jpg Almariamየወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ህወሀት) የኢትዮጵያን ህዝቦች በዘፈቀደ በመግደል፣ እልቂትን በመፈጸም፣በማረድ፣ ሰላማዊ ህዝቦችን በጅምላ በመፍጀት እና እልቂትን እና አካለ ጎደሎ የማድረግ ዘመቻውን አጠናክሮ በመቀጠልላይ ያለው በስልጣን ኮርቻ ላይ ዘላለም እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመኖር ስለሚፈልግ ነውን? 

አሳዛኝ በሆነ መልኩ የዚህ ጥያቄ ምልሽ አዎንታዊ ነው፡፡ አዎ እንደ መዥገር በስልጣን እርካብ ላይ ተጣብቆ ህዝቦችንእያተራመሰ ሲገዛ ለመኖር ነው! 

ላለፉት 24 ዓመታት ህወሀት በሀገሪቱ ውስጥ ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ መልካም አጋጣሚን አግኝቶ ነበር፡፡ 

ህወሀት በእያንዳንዷ የሰላም እና እርቀሰላም የድርድር መድረክ፣ በእያንዳንዷ የፖለቲካ ተሳትፎ እና መስተጋብር፣በእያንዳንዷ የዴሞክራሲያዊ ሂደቱን የማጠማዘዝ እና ምርጫውን በሸፍጥ በታጀበ ድል አድራጊነት አሸነፍኩ እያለበማወጅ በህዝብ ላይ ሸፍቶ እልቂትን እየደገሰ ህዝቦችን በመግደል መኖርን በመምረጡ ምክንያት እንጅ ሰላማዊ የሽግግርለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉትን መልካም አጋጣሚዎች ሁሉ ያጣበት አጋጣሚ አልነበረም፡፡ 

ላለፉት 24 ዓመታት ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ እንዳይመጣ አሻፈረኝ በማለት ህዝቦችንእንደ ቄራ በሬ እያረደ ሞገደኛነቱን አጠናክሮ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህወሀት ህዝባዊ እምቢተኝነትን በኃይል ለመቀበል የሚገደድበት እና የቱንም ያህል ሰላማዊ ህዝቦችንቢገድል፣ ቢፈጅ እና እንደ አበደ ውሻ ከወዲያ ወዲህ ቢቅበዘበዝ ከለውጡ አይቀሬነት እና ከህዝቡ የትግል መንፈስአይበገሬነት ሊያመልጥ እንደማይችል በዓይኑ በብረቱ እየተመለከተ ነው፡፡ ህዝባዊ ማዕበል ዓይኑን አፍጥጦ እየመጣበትነው! እራሱ ሰላማዊ ዜጎችን በህዝብ ገንዘብ በተገዛ ጥይት በግንባራቸው እና በደረታቸው ላይ እያነጣጠረ እየገደለ እናእልቂትን እየፈጸመ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሀል እንዲሉ በዚሁ በተለመደው አደንቋሪ ቅጥፈቱ ለህዝቦች ህልፈትምክንያት የሆኑት ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ኃይሎች ስለሆኑ ህዝቡ እነርሱን አሳልፎ እንዲሰጥ በማለት ህዝቡን እያስገደደበካድሬዎቹ እና በእበላ ባይ ምሁራን ተብየዎች እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ጥቅም በተገዙ እበላባይ የደናቁርት ስብስብአንደበት አማካይነት እንደበቀቀን እያስጮኸ የስብሰባ መድረኮችን በየከተማው እና በየቀበሌው እያዘጋጀ በህዝብ ግብርየሚተዳደሩትን የመገናኛ ብዙሀን አጨናንቆ ይገኛል፡፡ የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ እና የቂል ለቅሶ መልሶ መላልሶእንደሚባለው ህወሀት የህዝቡን ነባራዊ የትግል ወኔ እና አይበገሬነት ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል አሁንም ደግሞ እናደጋግሞ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ኃይሎች የቆቀሰቆሱት አመጽ ነው በማለት ህዝቡን ለማደናገርእና ከተቀጣጠለው የአመጽ ማዕበል ለማዘናጋት የቅጥፍና ድርጊቱን በማራመድ ላይ ይገኛል፡፡ 

.. ታህሳስ 2015 የኢትዮጵያ ህዝቦች በሰላማዊ የለውጥ ሽግግር እና በአመጽ ኃይል መካከል ያለውን መስመርተራምደውት አልፈዋል፡፡ 

.. ታህሳስ 2015 የኢትዮጵያ ህዝብ የለውጥ ማዕበሉ ሊቀለበስ የማይችልበትን መስመር ተሻግሮ ለወሳኙ ድልበመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የለውጥ ሂደቱ ሊቀለበስ የማይችልበትን መስመር ተሻግሮ የመሄዱን እውነታ በግልጽ የሚያመላክተው ህዝቡማንንም ሳይሆን የእራሱን በሙስና የተዘፈቁ ነቀዞች እና ገዳይ መሪዎቹን፣ የጥፋት ግብረ አበሮቹን እና ታዛዥ ሎሌዎቹንብቻ በሚወክለው ህወሀት በሚባለው ወንጀለኛ ድርጅት ላይ ያለውን ጥላቻ በግልጽ እና በአደባባይ በማሳየት ላይየመገኘቱ ሁኔታ ነው፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የለውጥ ሂደቱ ሊቀለበስ የማይችልበትን መስመር ተሻግሮ የመሄዱን እውነታ በግልጽ የሚያመላክተውየኢትዮጵያ ህዝብ ህወሀትን የሚፈራበት ሁኔታ ጭራሽ የማይታይ የመሆኑ ሁኔታ ነው፡፡ 

ህወሀት የሚባለው ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ወሮበላ ስብስብ በዓለም አቀፍ ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ጉያ ውስጥ ተወሽቆያለ እና እስከ አፍንጫው በኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት የተገዛ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የሚገኝ እና በአንበሳዎቹ መካከልእያሽካኩ እንደሚገኙ የጅብ መንጋዎች ዓይነት መሆኑን የአንበሳ ልብን የተጎናጸፈው የኢትዮጵያ ህዝብ አሳምሮ ያውቃል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ደፍሮ በአደባባይ በመውጣት በዘህወሀት ላይ ያለውን እምቢተኝነትበግልጽ እና በማያሻማ መልኩ በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ 

ህዝቡ በሀገሪቱ ውስጥ በግልጽ ፍጹም የሆነ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲደረግ በመጠየቅ ላይ ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ ህወሀት የሚባለው በህዝቦች ደም የተጨማለቀ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ወሮበላ የወንጀለኛ ድርጅትበህዝቦች ጫንቃ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ከሚገኝበት ስልጣኑ በአስቸኳይ እንዲወገድ በመቀስቀስ እና ከፍተኛ የሆነእንቅስቃሴ በማድረግ በግልጽ በመጠየቅ ላይ ይገኛል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የለውጡ ሂደት ሊቀለበስ ከማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክተው እውነታ ህዝቡ ህወሀትየተባለው ወንጀለኛ ድርጅት በማንኛውም መንገድ በየትኛውም የትግል አማራጭ ከሚያመልከው ስልጣኑ ከኢትዮጵያህዝብ ጫንቃ ላይ መወገድ አለበት ብሎ የተነሳ መሆኑን በግልጽ መመልከት በመቻሉ ነው፡፡ 

ህወሀት የተቀመጠበት በሰዓት የተሞላ ፈንጅ ባሩድ/ደማሚት በርሜል ላይ ፊዩዝ (ምላጭ) አሳት አየተቀጣጠለመፈንዳት ብርሀን በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ በጣም አጭር የሆነች የማፈንጃ ፊዩዝ ናት፡፡ ጥያቄ ሆኖ የሚነሳው ይህችየመተኮሻ ፊዩዝ በባሩድ የተሞላውን የፈንጅ ሳጥን እሳት የምትለኩስበት ሰዓት መቸ ነው የሚለው ብቻ ነው፡፡ 

ህወሀት 25 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ህዝቦች ልብ ውስጥ የሚነድ እሳትን ሲለኩስ እና ሲያቀጣጥል ቆይቷል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ህወሀት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙትን ህጻናትን እና ወጣቶችን እንዲሁም ሴቶችን እናአዛውንቶችን በመጨፍጨፍ፣ በመግደል እና በማሰቃየት እንደ ቋያ እሳት በመቀጣጠል ላይ ያለውን አመጽ ለመጨፍለቅየሚችል መስሎ ይታየዋል፡፡ 

ህወሀት በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ እንደ ቋያ እሳት ከዳር እስከ ዳር የተቀጣጠለውን የአመጽ እንቅስቃሴ በፍጥነት እናአሁኑኑ በማጥፋት፣ ነገ፣ በሚቀጥለው ሳምንት እና በቀጣዩ ዓመት የሚነሳውን ህዝባዊ አመጽ በሙሉ የሚያጠፋው መስሎይሰማዋል፡፡ 

ባለፈው ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዲህ የሚል ዘገባአውጥቷል፡ 

ፖሊስ እና ወታደራዊ ኃይሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይቶችን በመተኮስ ቢያንስ 75 ሰላማዊ ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ሌሎችበርካታዎችን ደግሞ ቁስለኛ እንዲሆኑ አድርገዋልኦሮሞዎች ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ የመንግስት ምላሽ በዜጎች ላይ በመተኮስእልቂትን መፈጸም ሆኗል፡፡ መንግስት ሰላማዊ የሆነውን ሰልፍአሸባሪዎችየጠነሰሱት የሚል ፍረጃ በመስጠት ከፍተኛ የሆነወታደራዊ ኃይል በማሰማራት እያጸመው ያለው ግድያ እና የኃይል እንቅስቃሴ ይህንን በቋፍ ላይ ያለን ሁኔታ ወዳልተጠበቀ እናከፍተኛ ወደሆነ አደገኛ ሁኔታ ሊወስደው ይችላል፡፡

እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፡ 

40 ሰዎች እልቂት ምክንያት ለሆነው እና ሰላማዊ አመጸኞችን በመጨቆን መሬትን በኃይል ለመያዝ መንግስት እያደረገ ያለውንድርጊት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣኖች አሸባሪዎች ተብለው ተፈርጀዋል፡፡

በሀገር ውስጥ እየታተመ የሚወጣው አዲስ ፎርቹን እየተባለ የሚጠራው ሳምንታዊ ጋዜጣ በበኩሉ እንዲህ የሚልማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡

በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በሚያሰሙ የዩኒቨርስቲ ወይም ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጠብመንጃተኩሶ መግደል መፍትሄ ሊሆን አይችልም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በቋፍ ላይ ያለውን ሁኔታ የበለጠ ያባብሰዋል፣ እናም በሀገሪቱ ውስጥባለው የጸጥታ ሁኔታ ላይ አሉታዊ እንደምታ ሊያሳርፍ ይችላል፡፡ ህይወታቸውን ላጡት ሰላማዊ ዜጎች ከህዝቡ ጋር በመቀራረብለመነጋገር እና ሁኔታውን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት የማይደግ ከሆነ የአሁኑ ብቻ ሳይሆን ከዓመት በፊት በተመሳሳይመልኩ ወገኖቻቸው የተገደሉባቸውን ዜጎች ስሜት እንደገና በመቀስቀስ ሌላ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለውን እና እንዲህ የሚለውን መግለጫ አውጥቷል፡ 

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙበት ጊዜ ለበርካታ ዜጎች ህይወትመጥፋት ምክንያት የሆነው ጉዳይ እጅግ ያሳስባታል፡፡ በተደረገው ግድያ እጅግ በጣም እናዝናለን፡፡ እንዲሁም በዚህ ድርጊትህይወታቸውን ላጡት ዜጎች ቤተሰቦች የተሰማንን ሀዘን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ተቃውሞንእንዲፈቅድ እና ሕጋዊ ጥያቄውን በመቀበል ተቀራርቦ በመወያየት ቅሬታዎችን እንዲፈታ እንጠይቃለን 

የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሀፊ የነበሩት እና .. 1991 በለንደን ተደርጎ በነበረው የድርድር ኮንፈረንስላይ ህወሀት አዲስ አበባ በመግባት ስርዓት እንዲያስከብር በማለት አሁን የሙጥኝ ብሎት ለሚገኘው ስልጣን ያበቁትኸርማን ኮሆን በአሁኑ ጊዜ ህወሀት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ኢትዮጵያውን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው እልቂትእንቆቅልሽ እንደሆነባቸው እንዲህ በማለት ግልጽ አድርገዋል፡ 

የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ አመራሮች በእነርሱ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ወደ አደባባይ መንገዶች በሚወጡ ሰላማዊ ዜጎችላይ ግድያ የመፈጸም ፖሊሲን ያራምዳሉ፡፡ ሌሎች መግለጫ በመስጠት ተቃውሞ የሚያሰሙትን እና ሆኖም ግን ሰላማዊ ሰልፍየማያደርጉትን ዜጎች ደግሞ ለብዙ ጊዚያት ለሚቆይ እስራት ወደ ዘብጥያ ይወረውሯቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አገዛዝበእራሱ ዜጎች ላይ እጅግ በጣም ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ማደርግን እና በየጊዜው እንደዚህ ያለ ግድያ ለምን እንደሚፈጽም ሊገባኝአልቻለም፡፡ መንግስት በመሰረተ ልማት እና በግብርናው ዘርፍ ላይ እያደረገ ባለው የመውዕለ ንዋይ ፍሰት የዓለም አቀፉማህበረሰብ በአዎንታዊነት መልኩ ይመለከተዋል፡፡ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ዘና ቢያደርገው እና እንዲላላየሚያደርግ ቢሆን ኖሮ በህዝቦች ዘንድ ታዋቂነትን ያተርፍ ነበር፡፡ ከምንም ጥርጣሬ በላይ በቀረቡት እውነታዎች ላይ ፊት ለፊትእንጋፈጥ!

በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ በወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ምላጭን በመሳብ እልቂት እናግድያን መፈጸም የዘህወሀት የሁልጊዜ መገለጫው ነው፡፡ 

ህወሀት .. 2005 ተደርጎ ነበረበረው የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ወደ 1000 የሚጠጉ ወገኖቻችንንበአደባባይ ገድሏል አቅሱሏል ፡፡

ህወሀት .. 2004 በጋምቤላ ክልል የሚገኙ የአኙዋክ ብሄረሰብ አባላት የሆኑትን 400 ወገኖቻችንን በጥይትእየቆላ በጊሬደር በተቆፈረ በአንድ ጉድጓድ ውስጥ እንዲቀበሩ አድርጓል፡፡ 

ህወሀት .. 2007/08 በሶማሊ ክልል በኦጋዴን አካባቢ በአስርት የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንንበጥይት እየረፈረፈ እልቂት ፈጽሞባቸዋል፡፡ 

ህወሀት .. 2006-2009 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ የሰውን ሀገር ሉዓላዊ ድንበር ጥሶ በመግባት 10ሺዎች የሚቆጠሩ ሶማሌያውያን ዜጎች ላይ ግድያ ፈጽሟል፡፡ ይህ የእብሪት ወረራ እና ግድያ ለመጭው የኢትዮጵያትውልድ የማይድን ጥቁር አሻራ ጥሎ ከማለፉም በላይ የአረቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ ቂም በመቋጠር በየዘመኑ ጥቃቱንሲሰነዝር እንዲኖር የሚያደርግ ዕኩይ የሰይጣን ድርጊት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ 

ህወሀት .. 1991 ስልጣንን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚኖሩ 10ሺህ በላይ በሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይ የግድያ እልቂትን ፈጽሟል፡፡ 

ውልደቱ እና ተፈጥሯዊ ባህሪው ስለሆነ የዘህወሀት የግድያ አባዜ ለማንም ሰው ቢሆን የሚያስገርም ነገር አይሆንም፡፡ 

በአሁኑጊዜ የዘህወሀት መሪዎች ወታደራዊ ዩኒፎርሞቻቸውን በመልበስ ሌሎችንም የማስመሰያ ድርጊቶችን ሁሉበማድረግ በሰለጠነው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ተሰግስገው ይገኛሉ፡፡ ወገኖች እባካችሁ ይህንን ማስመሰያቸውን እናየኒፎርሞቻቸውን በሙሉ አስወልቋቸው! ሸክስፒር በግልጽ እንዳስቀመጡት እነዚህ የዕኩይ ምግባር ባለቤቶች እዚህቆመው ያሉት የህዝቦችን ጉሮሮ ለማነቅ ነው፡፡ 

ህወሀት በህዝቦች ደም ጨቅይቶ የተጸነሰ ደም መጣጭ አጋንንት ድርጅት ነው፡፡ 

ህወሀት በእልቂት የተፈጠረ ቀንዳም የሆነ ሰይጣናዊ ደም አፍሻሽ ድርጅት ነው፡፡ 

ህወሀት የህዝብ እልቂትን ደም በማፍሰስ በመፈጸም የሚኖር እና የሚጥር ዕኩይ ድርጅት ነው፡፡ 

ብቸኛ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው ጥያቄ ግን ህወሀት እርሱም እራሱ በደም እልቂት ይጠፋል ወይስ አይጠፋም የሚለውነው፡፡ 

የዘህወሀት መሪዎች፣ ግብረ አበሮች እና ከስር ያሉ መጋቢ ሞተ ለሆዱ ሙሰኛ አለቅላቂ ምሁራን ተብዬዎች በአሁኑ ጊዜእየተደረገ ባለው ህዝባዊ አመጽ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ፈርተው እና ተሸማቅቀው ወኔ ከድቷቸው ይገኛሉ፡፡እነዚህ የህዝብ ጠላቶች ለመጨረሻ ጊዜ በአስከፊ የፍርሀት ቆፈን ውስጥ ተወሽቀው የተገኙበት ጊዜ ቢኖር የአለቆች ሁሉአለቃ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ .. 2012 እንደ ጧት ጤዛ ከጎናቸው ብን ብሎ የጠፋ ጊዜ ነበር፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ላለው ህዝባዊ አመጽ ዋና መነሻ ሆኖ የቀረበው ከሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ዳርቻ በሁሉምአቅጣጫዎች የሚገኘውን የኦሮሚያ መሬት በመውረር እና በመቀራመት በሚሊዮኖች ብር እየቸበቸቡ ለማይሞውኪሳቸው ለመዝረፍ በማሰብ የተዘጋጀው የዘህወሀት እርባና ቢስ የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተባለው ስልትነው፡፡ (በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን እና የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን እየተባለ የሚጠራውን የሸፍጥ ሰነድ እዚህ በመጫን ማንበብ ይችላሉ፡፡) 

የመወሰን አቅም የለሹ የዘህወሀት የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለዚህ ተቃውሞ ዋና አንቀሳቃሹድብቅ አጀንዳ ያላቸው የውጭ ኃይሎች ናቸው በማለት እንዲህ የሚል አደንቋሪ ዋይታውን አሰምቷል፡ 

ይህንን አመጽ ከፊት እና ከኋላ በመሆን በማደራጀት በርካታ የሆነ የመንግስት እና የሕዝብ ሀብት እንዲቃጠል ያደረጉት ከውጭየሚገኙት ጸረ ልማት ኃይሎች ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች እንደተገደሉ እና በጸጥታ ኃይሎች እናበህዝቡ ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው አይተናል፡፡ እንደዚህ ያለው ሁኔታ በምንም ዓይነት መልኩ ሊቀጥል አይችልም፡፡ እኛ ከህዝቡጋር በመተባበር በአካባቢዎች ላይ መረጋጋት እንዳይፈጠር በሚንቀሳቀሱት ጸረ ሰላም ኃይሎች ላይ ምንም ዓይነት ምህረትየማይደረግለት ሕጋዊ እርምጃ እንደምንወስድ መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ በማለት ዝቷል፡፡ 

ድንቄምምህረት የማይደረግለት ሕጋዊ እርምጃ!” 

መቸም ወያኔ እና ሎሌዎቹ የሚነግሩን ሁሉ የተገላቢጦሽ ነውና ይልቁንም ኃይለማርያምምህረት የማይደረግለት ግድያእንፈጽማለን ማለቱ ነውን? ለመሆኑ ይህን ያህል ሰላማዊ ዜጋ (የትምህርት ቤት እምቦቀቅላዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እናአዛውንቶች) በጥይት እየተቆሉ በመገደል ላይ ያሉት በየትኛው የሕገ መንግስት ሰነድ እና የሕግ አንቀጽ እንደሆነ የዘህወሀት የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ያውቀው እና ይጠቅስልን ይሆን? 

ለስሙ የፕሮቴስታንት ኃይማኖት እምነት ተከታዩ ኃይለማርያም ቅዱሱ መጽሐፍ ሰው አትግደል፣ ጠላትህን እንደራስህአድርገህ ውደድ የሚለውን አምላካዊ ቃል ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ስትገባ በካራቴ መትተህ ስለጣልከው ነውይህንን የእብሪት ቃል የምትናገረው፡፡ የዘህወሀት የይስሙላው ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም የኃይማኖቱን ጉዳይስተወው አንዴ ስልጣንን ስትወድ እና የዘህወሀት ታማኝ አገልጋይ ሎሌ ሆነህ ስትሰየም ቀንዳሙ ሰይጣንተፈናጥጦብሀልና፡፡ 

እንዲያው ለመሆኑ የይስሙላ ሕጋችሁን እንኳ ለይስሙላ እንኳ ለመናገር ድፍረቱ ቢኖርህ በሰላማዊ መንገድ ቅሬታቸውንወደ አደባባይ በመውጣት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ለማሰማት ሰላማዊ ሰልፍየወጡትን ዜጎች በጠራራ ጸሐይ ከግንባራቸው እና ከደረታቸው ላይ በማነጣጠር እልቂትን በፈጸሙ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮችላይ ነው ሕጋዊ እርምጃ መወሰድ ያለበት ወይስ ደግሞ መብቴ ይከበር፣ ይህንን ድርጊት እቃወማለሁ ባለ ዜጋ ላይ ነው?የኃማኖቱን ነገር ተወው እና በዓለማዊው ሕግም ቢሆን እንኳን መብቴ ይከበር ብሎ የጠየቅን ሰላማዊ ህዝብ ይቅርና ህዝብበስሜት ተነሳስቶ ግድያ ቢፈጽምም እንኳ ለሕግ ይቀርባል እንጅ ግደል የሚል ሕግ የለም፡፡ ግን በሕገ መንግስት ሰነዱ ላይእንጅ በዘህወት ላይ ይኸ ነገር አይሰራም እንደምትለን ጥርጥር የለውም፡፡ 

ኃይለማርያም እና የእርሱ ህወሀት ጌቶቹ ፍጹም በሆነ መልኩ ምህረት የለሽ እርምጃ የመውሰድ ብቃቱ አላቸው፡፡ሆኖም ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ብቃቱ የላቸውም፣ ምክንያቱምከሕግ የበላይነትጋርበፍጹም አይተዋወቁምና ነው፡፡ 

ኃይለማርያም እና የዘህወሀት ጌቶቹበህግ የበላይነትእናበወሮበሎች የሕግ የበላይነትመካከል ያለው ልዩነትተምታቶባቸዋል! 

ኃይለማርያም በዘህወሀት ጌቶቹ እንዲህ የሚለውን ነገር እንዲናገር ተነግሮታል፡ህወሀት በስልጣኑ ላይ ለመቆየትየትኛውንም ዓይነት እርምጃ በመውሰድ ተቃዋሚዎቹን እና ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹን ያለምንም ምህረት ይገድላል፡፡ 

ህወሀት በተቃዋሚዎቻቸው ላይ ምህረት የለሽ ዲያብሎሳዊ እርምጃ እንደሚወስዱ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡የሸክስፒርን አባባል በመዋስገሀነም ባዶውን ቀርቷል ምክንያቱም ሁሉም ሰይጣኖች ከዘህወሀት ጋር ተቀላቅለዋልና!” 

ሌላው የዘህወሀት ተቀጣሪ አወናባጅ የሆነው እና ለንደን የሚኖረው በስም አብይ ብርሀኔ በሚል የሚጠራው እንደኃይለማርያም ሁሉ ተመሳሳይ የገደል ማሚቶውን እንዲህ በማለት አሰምቷል፣በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎችየተቀሰቀሰው አመጽ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሕገ መንግስታዊ ስርዓት በኃይል ለመናድ መሰረታቸውን በውጭ ያደረጉተቃዋሚ ቡድኖች ያደረጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ 

ሌላው በሞራል ስብዕና የዘቀጠው እና የዘህወሀት የአሻሻጭነት ሰራተኛ ስብዕናን ተላብሶ እንደ በቀቀን እና ዛርእንደያዘው በሽተኛ እየተንተባተበ የሚለፈልፈው በስም ጌታቸው ረዳ የተባለው ሎሌ ካድሬ እንዲህ የሚል ዲስኩርአሰምቷል፣የችግሮቹ ዋና ምክንያት በከተማዋ መስፋፋት ጉዳይ ላይ ከህዝብ ጋር ምክክር ለማድረግ ጥረት እያደረገያለውን ህወሀትን በመቃወም ላይ ያሉ የታጠቁ ወሮበላ ኃይሎች ናቸው፡፡ የወሮበላ ቡድኑን ዓላማ ለማምከን እና በክልሉውስጥ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን በማስፈራራት ላይ ያለውን ቡድን የጸጥታ ኃይሎች ኃላፊነት የተመላበት እናተጨባጭነት ያላቸውን እርምጃዎች ይወስዳሉ፡፡በእርሱ ትርጉም እና አረዳድ ኃላፊነት በተመላበት መልኩ ማለትመግደል ማለት ነው፡፡ 

እስከ አፍንጫው የታጠቀ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን አገዛዝ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ተማሪዎችን እና ወጣትተቃዋሚዎችን የጦር መሳሪያ የታጠቁ ወሮበሎች በማለት የሚጠራው እንዴት ዓይነት ስብዕና እና አመክንዮ ቢኖረውነው? 

የዘህወሀት መሪዎች፣ አስመሳዮች እና ከታች ያሉት ጫማ ላሽ መጋቢዎች የተቃዋሚዎችን ስም በማጥፋት፣ በመወንጀል፣በማዋረድ፣ ስሚታዊነትን በማሳየት፣ ትችት በማቅረብ እና የኃይል እርምጃዎችን በመውሰድ ጊዚያቸውን አያጠፉም፡፡  

ህወሀት የማይቀረውን ህዝባዊ አመጽ እንዴት እንደሚያፋጥነው፣ 

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ ቀንዲል የሆነችው ርዕዮት ዓለሙ በዘህወሀት ላይ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂደውግንቦት 7 ለተባለው የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆና መቀላቀሏን ይፋ አድርጋለች፡፡ 

.. 2012 ህወሀት ሸፍጥን በተላበሰ መልኩ ርዕዮትን በአሸባሪነት በመክሰስ 14 ዓመታት እስራትን በይኖባትነበር፡፡ ባለፈው ሀምሌ ወር ከእስር ከተፈታች በኋላ ካለፉት ጥቂት ሳምንታት በፊት ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ ገብታለች፡፡ 

ርዕዮት ህወሀትን በትጥቅ ትግል ከስልጣኑ ለማባረር እንቅስቃሴ እያደረገ ካለው ድርጅት ጋር ለምን እንደተቀላቀለችእንዲህ በማለት ግልጽ አድርጋለች፡ 

በሀገር ውስጥ ምን ማድረግ እንደምችል ሳስብ ቆይቻለሁ፡፡ የምጽፍ ከሆነ እታሰራለሁ፡፡ ወደ እስር ቤት ዘብጥያ እወርዳለሁ፡፡የመጨረሻው የሚሆነው ይህ ነው፡፡ ይህንን አገዛዝ ለመቃወም እና ስርዓቱን ለመለወጥ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝአውቃለሁ፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ ልዩ የሆነ የእራሴን ድርሻ ማበርከት አለብኝ፡፡ የእኔ መስዋዕትነት ሰይጣናዊ ድርጊቱንከማስወገድ አንጻር ሊመጥኑ የሚችሉ መሆን መቻል አለባቸው፡፡ አንድ ነገር በመጻፌ ብቻ ታስሬ ከምንም እንቅስቃሴ ተገድቤመቀመጡን አልፈቅድም፡፡ ይኸ ለምከፍለው መስዋዕትነት ተመጣጣኙ አይደለም የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ በሀገሬ ላይ ለውጥለማምጣት አንድ ነገር ለማድረግ በማስብበት ጊዜ የተሻለ ነገር ለማድረግ እንደምችል አስቤበታለሁ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እነሱበሚፈልጉበት ጊዜ ሊዘጓቸው ይችላሉ፣ በማንኛውም በሚፈልጉበት ጊዜ የጋዜጦችን ህትመት ማገድ ይችላሉ፡፡ የተቃዋሚ የፖለቲካፓርቲ አባላትን ወይም ደግሞ መሪዎችን ማሰር መቻላቸው ቢያንስ የተሻለ ነገር ነው፣ ምክንያቱም ፓርቲው ከእንቅስቃሴውሳይታቀብ መጓዝ ይችላልና፡፡ ፓርቲዎችን እና ጋዜጦችን በመዝጋት ጋዜጠኞችን ማሰር ለእነርሱ ቀላል ነገር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜትንሹ ነገር ለምሳሌ ያህልም በፌስ ቡክ ሀሳብን መግለጽ ሊያሳስር የሚችል ነገር ነው፡፡ እንዲያውም አስቂኝ ተውኔቶችን የሚሰሩኮማኪዎች በአገዛዙ ላይ ቀልድ መስራት አይችሉም፡፡ ስለሆነም ምን ማድረግ አለብኝ? ብዙም አይደል፡፡ በእስር ቤት ሆኘ ምንምነገር መስራት እንደማልችል ግንዛቤ በመውሰድ ከድምዳሜ ላይ ደረስኩ፡፡ ከእስር ቤት ከተፈታሁ በኋላ በኢትዮሜዲያ የሚወጣጽሁፍ በመጻፍ እና ቃለ መጠይቅም በመስጠት አቋሜ ምን እንደሆነ ግልጽ አደረግሁ፡፡ የፍርሀት ድባባችንን በማስወገድበተጨባጭ ሊታዩ እና ሊዳሰሱ የሚችሉ ተግባራትን በማከናወን ገንቢ የሆኑ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለብን አምናለሁ፡፡ተጨባጭንት ያለው ድርጊት ዝም ብሎ መልካም ነገርን በማሰብ ብቻ የሚመጣ ነገር አይደለም፡፡ ይህንን ሁሉ እናገራለሁምክንያቱም ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ዕቅዱ የለኝምና፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር ቤት ብመለስ ቃሊት እየተባለ በሚጠራው [የመለስዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት] እንደምገባ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ከውጭ ሆኘ ለትግሉ መጎምራት የትግል ድርሻዬን በማበርከትአስተዋጽኦ ባደርግ የተሻለ ነገር ነው፡፡ ገና በእስር ቤት ሳለሁ የግንቦት 7 ንቅናቄን መቀላቀል እንዳለብኝ ወስኛለሁ፡፡ ለሰላማዊትግል ምንም ዓይነት ዕድል የለም፡፡ እንዲያውም ትንሽም ቢሆን አለ ከተባለ እኔ በእስር ቤት ታስሬ በነበርኩበት ጊዜ የነበረውዕድል በአሁኑ ጊዜ ጭራሹን የለም፡፡ ምንም ዓይነት የቀረ ምርጫ የለም፡፡ ምንም የቀረ ነገር የለም፣ የቀረው ምርጫ ቢኖር የትጥቅትግል ማካሄድ ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው ግንቦት 7 የተቀላቀልኩት፡፡ 

በኢትዮጵያ ውስጥ የቀረየሰላማዊ ትግል ዕድልየለምን? 

ርዕዮት በኢትዮጵያ ውስጥ የቀረ ምንም ዓይነት የሰላማዊ ትግል ዕድል የለም በማለት የሰጠችው መግለጫ በእያንዳንዱኢትዮጵያዊ ዘንድ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ጥያቄ ሆኖ ቀርቧል፡፡ የዚህ ጥያቄ ምላሽ የወደፊቷን ኢትዮጵያ መጻዒ ዕድልሊመልስ በማይችል መልኩ ሊወሰን የሚችል ጉዳይ ነው፡፡ (የዘህወሀት የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስቀድሞ ተወስኗል፡፡ምንም ዓይነት አዎንታዊ የሆነ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በፍጹም የለውም!) 

እኔ 10 ዓመታት ያህል በዘህወሀት ወንጀለኞች ላይ ያለምንም ማቋረጥ ጣቴን በመቀሰር ትችት ሳቀርብ ከቆየሁትየትግል መንፈስ እና አሳቤ ጋር ሳነጻጽረው የርዕዮት መግለጫዎች ጥልቅ መሰረት ያላቸውን ጥያቄዎች የሚያስነሳ ጉዳይነው፡፡ 

በመጀመሪያ ደረጃ ለርዕዮት ከፍተኛ የሆነ ክብር አለኝ፡፡ ለከፈለችው እና አሁንም ውድ ሀገሯን በመተው በሰው ሀገር ላይሆና እየከፈለችው ላለው መስዋዕትነት ከፍተኛ የሆነ ምስጋና ላቀርብ እፈልጋለሁ፡፡ ለዘህወሀት አይበገሬ እምቢተኛነቷንያሳየች ጀግኒት በመሆኗ ከፍ ያለ አድናቆት አለኝ፡፡ 

ርዕዮት ይቅርታ በመጠየቅ ምህረት እንዲደረግላት እና ከማጎሪያው እስር ቤት እንድትለቀቅ በዘህወሀት ትንንሽ አምላኮችፊት በመቅረብ ለመስገድ የቀረበላትን ጥሪ በጽኑ ተቃውማለች፣ ሞቴን እመርጣለሁ እንጅ ይህ በፍጹም አይደረግምበማለት አይበገሬነቷን በተግባር አሳይታለች፡፡ 

ከመሰረታዊ ዓላማዋ ንቅንቅ ሳትል በእስር ቤት ውስጥ ሆና በዘህወሀት ሲደርስባት ከነበረው ማስፈራራት፣ ማዋረድ እናስብዕናን የማጥፋት ዕኩይ ምግባር ሳትንበረከክ በድል አድራጊነት የወጣች አይበገሬዋ ጀግኒት ናት፡፡ 

ርዕዮትበኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ዕድል የለምስትል በመብረቅ የተመታሁ ያህል ክውብዬ ነው የቀረሁት፡፡ 

ርዕዮት የእራሷን አመለካከት ግልጽ አደረገች ብዬ የማምን ቢሆንም እንኳ የእርሷን መግለጫዎች የግል የእምነቷመገለጫዎች ናቸው የሚል እምነት ይኖረኝ ነበር፡፡ 

ሆኖም ግን ርዕዮት እኔ ለማውቀው ለምንም ሳይሆን 70 በመቶ ለሚሆነው ለወጣት ኢትዮጵያውያን ትውልዷ ወክላ  ነውእየተናገረች ያለችው፡፡ 

ርዕዮት ጨለምተኝነት፣ ተስፋቢስነት፣ ፍጹም የሆነ ፍርሀት፣ ከፍተኛ ስቃይ እና ለእርሷ ትውልድ መጻዒ ዕድል ስትልድምጿን ከፍ በማድረግ በመጮህ እንደገደል ማሚቶ በማስተጋባት ላይ ትገኛለች፡፡ 

ርዕዮት በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት የቀረ የሰላማዊ ትግል ዕድል የለም የሚል መልዕክት ስታስተላልፍ ለእኔ እርሷየጨዋታው ሕግ አጧዥ ኃይል ሆና መቅረቧን በውል እንድገነዘብ ያደርገኛል፡፡ 

የርዕዮትን መግለጫዎች በውል በማጤንበት ጊዜ ለሰላማዊ ትግል ሌላ አማራጭ ምን መሆን እንዳለበት እራሴንእጠይቃለሁ፡፡ የትጥቅ ትግል ሊሆን ይችላልን? 

ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በአንድ ላይ ተሰባስቦ ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች እናበተቃዋሚው ስብስብ ላይ የእሩምታ ተኩስ በመክፈት፣ በአምልኮት ቦታዎች በምዕመናን መካከል የእጅ ቦምቦችንበማፈንዳት፣ ተቃዋሚዎችን በማሰር እና በማሰቃየት፣ የህዝቡን የምርጫ ድምጽ በመዝረፍ መቶ በመቶ አሸንፊያለሁ ብሎበማወጅ እና በአደባባይ ምህረት የለሽ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት ማወጅ እና መዛት ምርጫው በሰላማዊ እና በትጠቅትግል መካከል ያለመሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡ 

አይደለም! አይደለም! ምርጫው በሰላማዊ እና በትጥቅ ትግል መካከል ያለመሆኑን፣ ይልቁንም ምርጫው በቦቅቧቃፈሪዎች እና በደፋር ኃይለኞች መካከል መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያመላክታል፡፡ 

ርዕዮት ጋንዲየጎራዴው መርህበሚል ርዕስ ካዘጋጁት እንዲህ ከሚለው መንፈሳዊ ድምጽ የመጨረሻ ጠርዝ ላይደርሳለች ብዬ አምናለሁ፡ 

በፍርሀት እና በድፍረት/ኃይል መካከል ምርጫ ሲቀርብ ኃይልን መምረጥ የተሻለ እንደሆነ ምክር መምከር እንዳለብኝአምናለሁህንድ በፍርሀት አዘቅት ውስጥ ሰጥማ እረዳትየለሽ ሆና ለእራሷ ውርደት ምስክር ሆና ከምትዳክር ይልቅየእራሷን ክብር ለመጠበቅ ስትል መሳሪያ አንስታ ብትዋጋ የምመርጥ ይሆናል፡፡ 

እንደዚሁም ሁሉ ርዕዮት ኢትዮጵያውያን በዘህወሀት ተዋርደው እና ክብራቸውን እና ሀገራቸውን አጥተው ለዘላለምበውርደት አንገታቸውን በመድፋት እየተገደሉ እና እየተሰቃዩ መኖር ወይም ደግሞ በአንድነት በህብረት በአንድነትበመነሳት የዘህወሀትን አፋኝ ስርዓት በትጠቅ ትግል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጫንቃ ላይማስወገድ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ የደረሰች መሆኗን አምናለሁ፡፡

እስከ አፍንጫው ድረስ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን ኃይለኛ ወታደራዊ ኃይል፣ እንዲሁም የገንዘብ አቅምውስንነት ባለበት እና ህወሀት ሁሉንም ነገር ሙሉ በሙሉ ጨምድዶ በእራሱ ቁጥጥር ስር ይዞ በሚገኝበት ሁኔታየተጨቆነው እና የተገፋው ህዝብ እንዴት አድርጎ ለድል ይበቃል ለሚለው ጥያቄ ርዕዮት እንዲህ የሚለውን የጋንዲንአዋጅ ደግማ አውጃለች፣ኃይል ከአካላዊ እና ከቁሳዊ ብቃት የሚመጣ አይደለም፡፡ ኃይል የሚመጣው ከማይበገረውየዓላማ ጽናት ነውብላለች፡፡ 

ርዕዮት ከሰላማዊው የትግል መንገድ እንድትወጣ ያስቻላት የእምነቷ ድፍረት እና ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን እምቢኝአሻፈረኝ ለጨቋኙ እና ለበከተው ስርዓት ለዘህወሀት አልገዛም ብላ ፍርሀትን በመቃወሟ እና በቀጣይነትም የዘህወሀትን ውርደት በመሸከም እና ክብርን በማጣት እንደ እንስሳ ሆኘ አልኖርም ከሚል የማይበገረው የዓላማ ጽናቷበመነሳት ነው፡፡ 

ርዕዮትበቃ በቃ ነው!“ ከሚለው ጠርዝ ላይ ደርሳለች፡፡ 

እንደዚሁም ሁሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያንበቃ በቃ ነው!“ ከሚለው ጠርዝ ላይ ደርሰዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ 

እኔ 10 ዓመታት በላይ ሰላማዊውን የትግል መንገድ በመከተል ለድል መብቃት ይቻላል የሚል እምነት በመያዝ የግልአመለካከቴን በማራመድ በዘህወሀት እና በዓለም አቀፍ ደጋፊዎቹ ላይ ጣቴን ስቀስር በቆየሁበት ጉዳይ ላይ ጥያቄእንዳነሳ በማድረግ ሰላማዊ የትግል ጥያቄ ያበቃለት እና የተቀበረ መሆኑን በማስረገጥ የሰላማዊ የትግል መንገዱን እርግፍአድርጎ መተው እና በፍርሀት እና በድፍረት መካከል ያለውን ምርጫ በውል አጢኖ ፍርሀትን ከላያችን ላይ ጠራርጎበመጣል አምባገነኑን አገዛዝ በኃይል እና በሁለገብ የትግል ስልት አሽቀንጥሮ ለመጣል በጽናት የተያዘው የርዕዮት ውሳኔለሌሎቹ በእርሷ የትውልድ ዘመን የሚገኙትን የበርካታዎቹን ወጣቶች አመለካከት፣ ስሜት እና ፍላጎት የሚያንጸባርቅእንደሆነ አምናለሁ፡፡ 

ረዣዥሞቹን ትችቶቼን ለበርካታ ጊዘያት ስታነቡ ለቆያችሁ አንባቢዎቼ .. 2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላየቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የዘህወሀት መሪ በእብሪተኝነትእና በማን አለብኝነት የግፍ ስሜት ተነሳስቶ ለአፋኝ እና ለቅጥር ነፍሰ ገዳይ ሎሌዎቹ የእልቂት ትዕዛዝ በማስተላለፍበጠራራ ጸሐይ በአደባባይ የተዘረፈውን የኢትዮጵያን ህዝብ ድምጽ ለመቃወም እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እናለኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳወቅ ወደ አደባባይ በወጡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን እልቂት ከተመለከትኩ በኋላ በቁጭትበወገኖቼ ላይ የተፈጸመውን ግፍ እና ወንጀል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችበማሳወቅ የስርዓቱ አዛዥ ቁንጮዎች እና ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ለፍትህ አካል ለፍርድ እንዲቀርቡ በማሰብ ወደ ትግሎ ዘውብዬ እንደገባሁ የምታስታውሱት ጉዳይ ነው፡፡ 

በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ትግል በጀመርኩበት ጊዜ በሚከተሉት ሶስት ነገርች ላይ ሙሉ እምነትነበረኝ፡፡ እነርሱም፡ 

1) በኢትዮጵያ ሰላማዊ የለውጥ ሽግግር ለማድረግ መቻሉ ብቻ ሳይሆን የማይቀር ግዴታም ነው የሚል ሙሉእምነት ነበረኝ፡፡ 

2) አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እና ህወሀት በኢትዮጵያ ላይ እሳት ለኩሰዋል፡፡ እንደ እኔ ያሉት እሳት አጥፊዎችደግሞ የጎሳ ጥላቻ፣ የዘር እና የብሄር ክፍፍል፣ የበላይነት እና ተጻራሪነት እንዲሁም የእኩልነት እጦት እናየኢፍትሀዊነት እሳት እንዲጠፋ እንድንታገል አስፈላጊዎች ነን የሚል እምነት ነበረኝ፡፡ 

3) የኃይል አመጽ (የጭካኔ ሕግ) ማህበራዊ ለውጥን እንደሚያስገኝ መሳሪያ አድርጎ መውሰድ ኢሞራላዊ፣ያልሰለጠነ ኋላቀር እና ኢሰብአዊነት ነው የሚል እምነት ነበረኝ ፡፡ 

ጋንዲሰላማዊነት የሰው ዘር ሕግ ነው፡፡ አላግባብ ኃይለኛነት ግን የጨካኞች ሕግ ነውበማለት አስተምረውናል፡፡በጨካኞች ላይ የመፍጀት የሕግ መንፈስ ነው ያለው፡፡ የሰው ልጅ ክብር የመንፈስ ከፍተኛ ጥንካሬ ለሆነው ሰላማዊ መንፈስ ታዛዥ መሆን ይጠይቃል፡፡ 

የሰው ልጆች ዘር ሕግ ሰላማዊ እንደሆነ አድርጌ አምን ነበር፣ አሁንም አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን ከዚህም በተጨማሪ በሰውልጆች ዘር ላይ ምህረት የለሽ እርምጃ የሚወሰድ ከሆነ ሌላው ወገን ደግሞ ባጻፋው ምህረት የለሽ ምላሽ እንደሚሰጥእገነዘባለሁ፡፡ 

.. ነሐሴ 2006 HR 5680 ጋር በተያያዘ መልኩኢትዮጵያ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶችመጠናከር 2006 ድንጋጌ/Ethiopia Freedom, Democracy and Human Rights Advancement Act 2006“ በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ አስፈላጊነቱን በእራሴ ፍልስፍናበማወጅ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ የህዝቡን ልብ እና አዕምሮ በማሸነፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንችላለንበማለት እንዲህ ብዬ ነበር፡ 

የእኛን ትክክለኛነት የምናረጋግጠው በጦር ሜዳ ውስጥ በመግባት በደም በመዘፈቅ እና የሬሳ ክምርን በመከመርአይደለም፣ ሆኖም ግን የእኛን ትክክለኛነት የምናረጋግጠው ለመልካም እና ለጥሩ ነገር በወንዶች እና በሴቶች አእምሮ እናልብ ውስጥ በምናስቀምጠው ደግ ነገር እንደሆነ አምናለሁየአእምሮ እና የልብ ውስጣዊ ትግል በማድረግ እራሳችንንከጎሳ ጥላቻ መርዝ ማጽዳት አለብን ብየ አምናለሁ፡፡ 

.. 2016 የአዲስ ዓመት ደወል ከመደወሉ ጥቂት ቀናት ቀደም ሲል ህወሀት 24 ዓመታት ከሕግ አግባብበላይ ስልጣኑን በመጠቀም የኢትዮያን ህዝብ ልብ ሊጠገን በማይችል መልኩ እንዲሰበር አድርጓል፣ 24 ዓመታትበዘለቀው ኢፍትሀዊ አገዛዙ የኢትዮጵያን ህዝብ ልብ አቃጥሏል፣ 24 ዓመታት ክብር በማሳጣት እና በማዋረድ የህዝቡንልብ አጥቁሯል፣ 24 ዓመታት በመበዝበዝ የህዝቡን ልብ እንዲያመር አድርጓል፣ 24 ዓመታት በሙስና ባህር ውስጥበመዘፈቅ የህዝቡን ልብ እንዲታመም አድርጓል፣ እንደዚሁም ሁሉ 24 ዓመታት በዘለቀው አምባገነናዊ የጭቆና እናየጭካኔ አገዛዙ የህዝቡን ልብ እንዲደነድን አድርጓል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝቦች የልብ ትርታ በግድ ወደ መሳሪያ የትጥቅ ትግል ወደማድረግ እና  የጦርነት ከበሮ ወደመምታት ተሸጋግሯል፡፡ 

ባለፉት አስር ዓመታት ጊዜ ውስጥ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ መጠቀምን፣ ስለአምባገነንነት እና ጨቋኝነት፣ ስለሰብአዊመብት ድፍጠጣ እና ስለዴሞክራሲ፣ በኢትዮጵያ ስለፍትህ እና ስለሰብአዊ መብት ጥበቃ ያደረግሁትን እልህ አስጨራሽትግል ወደ ኋላ መለስ ብየ ስመለከተው ለሰላማዊ ለውጥ ሳደርጋቸው የቆየኋቸው እነዚያ ሁሉ ጥረቶች የመከኑ ባዶእንደሆኑ ያህል ሆኖ ይሰማኛል፡፡ ምንም ነገር ያልተደረገ እርባና ቢስ አድርጌ ግን አልቆጥረውም፡፡ 

አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ እና ትክክለኛውን አካሄድ እንዲከተሉ ለዘህወሀት እና ለመሪዎቹ የሰጠኋቸው ምክሮች እናማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ተደማጭነትን እና ትኩረትን ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ 

ጭቆናውን እንዲያቆም፣ የበለጠ ሰብአዊነት እንዲሰማው እና ትክክለኛውን መንገድ እንዲከተል እንደዚሁም ደግሞህዝቦቸን ማዳመጥ እንዲችል ያቀረብኳቸው ልመናዎች ሁሉ ምንም ሰሚ ሳያገኙ ህወሀት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏቸውቀርቷል፡፡ 

በኢትዮጵያ ተለኩሶ የነበረው እና ለማጥፋት ጥረት ሳደርግ የቆየሁት እሳት በአሁኑ ጊዜ በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች ውስጥተቀጣጥሎ ይገኛል፡፡ 

.. 2007 “ትንሿ ወፍ እና የጫካው እሳትበሚል ርዕስ አቅርቤው የነበረውን ተመሳስሎ በርካታዎቹ የረዥምጊዜ አንባቢዎቼ ታስታውሱታላችሁ፡፡ 

በዚያ ባቀረብኩት ትችት ላይ ራቅ ካለ ወንዝ በመመላለስ በኩምቢዋ ውኃ እያመጣች እሳቱን ለማጥፋት ጥረት ስታደርግበነበረችዋ ትንሿ እሳት አጥፊ ወፍ እራሴን በመመሰል አቅርቤ ነበር፡፡ 

አመናችሁም አላመናችሁም ሀገራችን በእሳት ተቀጣጥላ ትገኛለች፡፡ በእሳት ለማቃጠል ምንም ኃላፊነት የማይሰማው አውዳሚኃይል ከጎን ተቀምጧልሆኖም ግን ጢሱ እንዲህ የሚል መልዕክት ያስተላልፋል፡በሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን እናእህቶቻችን በእሳቱ ውስጥ በመቃጠል ላይ ናቸው፣ በአስር ሺዎች እና ከዚያም በላይ የሚሆኑት ወገኖቻችን ደግሞ በአሁኑ ጊዜበመቃጠል ላይ ይገኛሉ፣ እንደዚሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ዜጎች በጥይት እየተደበደቡ በመሞት ላይ ይገኛሉ፣ 77 ሚሊዮንየሚሆኑት ዜጎች በጥይት የተኩስ መስመር ጠርዝ ላይ ተሰልፈው ይገኛሉ! 

ቤትህ በእሳት ተቀጣጥሎ ሳለ በአካባቢው ዝም ብለህ ቆመህ መልካም ንግግር እየተናገርክ አትመለከትም፡፡ የተቀጣጠለውን እሳትለማጥፋት እንደ ትንሿ እሳት አጥፊ ወፍ ሁሉ ከወንዝ እየተመላለስክ የውኃ ጠብታዎችን እያመጣህ እሳቱን ለማጥፋት ጥረትማድረግ ይኖርብሀል፡፡ 

ሆኖም ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣት ወገኖቻችን በየዕለቱ በእሳት ነበልባል መስመር ላይ ተጥደው ይገኛሉ፡፡ በሰላማዊመንገድ ለመቃወም እንቅስቃሴ ካሳዩ እንደ አበደ ውሻ በጥይት ይገደላሉ፡፡ አእምሯቸው የሚያምንበትን ነገር አውጥተው ከተናገሩአሸባሪ በመባል ተፈርጀው ወደ ሞጎሪያው እስር ቤት ዘብጥያ ይወርዳሉ፡፡ ለአገዛዙ ታማኝ አይደሉም የሚል ጥርጣሬ ካለየማስፈራራት ድርጊት ይፈጸምባቸዋል፡፡ ግፈኛውን አገዛዝ በኃይል ያስወግዳሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ከሆነ ታፍነው የደረሱበትደብዛው እንዲጠፋ ይደረጋሉ፡፡  

እነዚህ የዲያስፖራ እሳት አጥፊዎች እሳትን በእሳት አይዋጉም፣ በፍጹም፣ እሳትን የሚዋጉት በውኃ ነው፡፡ ውኃ በእሳት ላይእንደሚያደርገው ድርጊት ሁሉ እነዚህ እሳት አጥፊ ተዋጊዎች ጨለምተኝነትን በተላበሰው እና ምንም ዓይነት የተስፋ ጭላንጭልእና ብሩህ ነገር በማይታያቸው ላይ ላሉት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የተስፋ እና የብሩህ ልምላሜ ስሜትን  በመፈንጠቅ፣የጭቆናን እና የጭካኔ አምባገነናዊ ቆሻሻን በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብት መጥረጊያ ጠርጎ እና ጠራርጎ ወደ ቆሻሻማጠራቀሚያ ቅርጫት በመጣል፣ በፖለቲካ ሸፍጠኝነት፣ በሙስና፣ በኋላቀር ድርጊት እና በሕግ አልበኝነት ምድረበዳ በሆነውመሬታችን ላይ የነጻነት እና የፍትህ ዘርን በመዝራት ወደ ልምላሜ ይመልሳሉ፡፡ 

እነዚህ እሳት አጥፊዎች እንዲህ የሚል አንድ ብቸኛ ተልዕኮ አላቸው፡በብሄራዊ ራዕይ የሚመራ የኢትዮጵያን ህዝብበማይከፋፍል አንድነት ላይ መሰረት ያደረገ በኢትዮጵያ ውስጥ እርስ በእርሳቸው የሚወዳደሩ እና በጥልቅ ቅራኔ፣ በቋንቋ፣ እናበአካባቢያዊ የልዩነት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቀው ያሉ ተዛማጅነት የሌላቸው ስብስቦች ናቸው የሚለውን የመከነ ሀሳብ አሽቀንጥሮበመጣል በፍቅር የተሳሰረ አዲስ የህብረተሰብ እንዲገነባ ማገዝ ነው፡፡ 

እንግዲህ እንዲህ በማለት ደመደምኩት፡ 

ወጣቶቻችን ተቀጣጥሎ የሚገኘውን እሳት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሆኖም ግን በማይበገር ወኔ እና ጽናት ለማጥፋት እንዲችሉእናስተምራቸው፣ እናሰልጥናቸው፣ እናበረታታቸው፣ እንደግፋቸው፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን የእሳት ሰለባዎች እና የወደፊትዕጣፈንታቸውን ለማዳን ሲባል በእሳት ነበልባል ተቀጣጥለው በተስፋየለሽነት የሚገኙትን ወገኖቻችንን እንቀፋቸው፡፡በመጨረሻም በማቅለጫ ምድጃው/ፈርነሱ ውስጥ ቀልጦ እንደሚወጣው የአረብ ብረት የሚያንጸባርቁ እና ምድረበዳ ለሆነው እናለጠፋው ደን ፈውስ የሆነችውን ብርቅየዋን ጸሐን እንደሚያመጡ እርግጠኛ እናድርጋቸው፡፡ 

የእኛ ወጣት እሳት አጥፊዎች ለዘመናት በፖለቲካ ጭቆና እና በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ የደቀቀ ማህበረሰብ እንዳላቸው የሚገነዘቡቢሆንም እንኳ በአንድ ወቅት በተራራው ጫፍ ባለች ከተማ ላይ ፍትህ የሰፈነባት፣ ሰብአዊነት የሚከበርባት እና ክብርን እና ሞገስንየተላበሰ ህዝብ የሚኖርባት፣ ማንም ወንድ መንግስትን የማይፈራበት ወይም ማንም ሴት መንግስትን የማትፈራበት፣ መንግስትየእራሱን ዜጎች የሰብአዊ መብት እና ነጻነት የማክበር ግዴታ ያለበት፣ ማንም ሰው ያለምንም ፍርሀት እና መሸማቀቅ ቀጥ ብሎየመሄድ፣ አዕምሮው የፈቀደውን ነገር በነጻ የመግለጽ፣ ማንም ወንድ፣ ሴት ወይም ልጅ ህይወቱን የማያጣበት፣ ከሕግ አግባብ ውጭማንም ሰው ንብረቱ የማይወረስበትን ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደሚችሉ ምንም ዓይነት ጥርጥር የለውም፡፡ 

በኢትዮጵያ አሁንም ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ማምጣት ይቻላልን? 

ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የሽግግር ለውጥ ማምጣት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ በእርግጠኝነትየማውቀው ነገር የለኝም፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር በተራራ ጫፍ ላይ የኢትዮጵያን ከተማ ለመገንባት ሳስበው የነበረውህልሜ ከመቅጽበት እንደጉም በኖ ጠፍቷል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት ወጣቶቻችንንለማስተማር እና ለማሰልጠን ሳደርገው የነበረው ጥረት ሁሉ መክኖ እና ወደሌላ መንገድ ተሻግሮ በማይበገር መልኩ የጎሳክፍፍል እሳትን፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ እሳትን እና ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ በመጠቀም አየተካሄደ ያለውንአምባገነናዊ የጭቆና አገዛዝ እሳት በአንዴ እና ከመቅጽበት ተለውጦ እሳትን በእሳት ወደማጥፋት የአካሄድ መንገድተቀይሯል፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ህዝብ በፈረጠመ ህዝባዊ ጡንቻው ህወሀትን እንደመዥገር ተጣብቆ ካለበት ስልጣኑ ላይ በኃይል ለማስወገድ በጽኑ የወሰነ መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም ህወሀትለምክንያታዊነት ተገቢውን ምላሽ የማይሰጥ ግትር ወንጀለኛ ነው፣ የውይይት መድረክ ለመክፈት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎየተቀመጠ እብሪተኛ እና ሞገደኛ ድርጅት ነው፣ በውይይት እና በክርክር የማያምን እና ሀገሪቱን በእርስ በእርስ የጦርነትእሳት ውስጥ ለመማገድ ሌት ቀን አበርትቶ እየሰራ ያለ ኃላፊነት የማይሰማው ወንጀለኛ የዘራፊ ወሮበላ ስብስብ ነው፡፡ 

ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉ እንደዚህ ያሉ ክስተቶች ቢኖሩም በሰላማዊ መንገድ ለውጥማምጣት የሚለው ህልሜ አሁንም ድረስ እኔን ብቸኛ አድርጎኛል፣ ኃይልን በመጠቀም በመሳሪያ ኃይል በአመጽ ለውጥንከማምጣት በሰላማዊ መንገድ ለውጥ የማምጣት ተስፋ ላይ የመቸከል እምነት የእኔ ብቻ ተስፋ እንዲሆን አድርጎኛል፣እንደዚሁም ሁሉ ለባዶ ለማይሆን ነገር ሰላማዊ መንገድን ብቻ መከተል የሚለው የእኔ ሰበካ የእኔ ብቻ አመለካከትእንዲሆን አድርጎኛል፡፡ 

ኢትዮጵያ ሰላሟን አስጠብቃ እራሷ ሰላም ሆነ ከጎረቤቶቿም ጋር በሰላም እንዲትኖር አሁንም ብቸኛው ህልም አላሚ ሆኘየቀጠልኩ ይመስለኛል፡፡ 

.. ሀምሌ 2012 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ የዘህወሀት መሪ ከዚህ ዓለም በሞት በተለየበት ጊዜበሰላምየምትኖር ኢትዮጵያ ህልም/Dreams of an Ethiopia in Peace” በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ 

በዚያ ትችቴ ላይ በስልጣን ላይ ባሉ አዳራሾች ብቻ ሳይሆን፣ በቢሮክራሲው እና በወታደራዊ ኃይሉ የመሰብሰቢያአዳራሾች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በጣም ሩቅ በሆኑ መንደሮች፣ ቤተክርስቲያኞች፣ መስጊዶች የመሰብሰቢያ አዳራሾችእንዲሁም በትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆች፣ በጎረቤታም ማህበራት እና በምግብ ቤት አዳራሾች፣ በመንገዶች እና በገበያዎችእንዲሁም በሌሎች ሁለት ወይም ከሁለት በላይ ሰው ሊሰበሰብባቸው በሚችሉ በየትኞችም ቦታዎች  ላይ ጭምር ውይይት በማድረግ ብሄራዊ እርቅ የማውረድ ጥረት እንዲጀመር ሀገራዊ ጥራ አቅርቤ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት አማራጭየለንም ሆኖም ግን በመልካም ፈቃደኝነት እና እምነት ላይ በተመሰረተ መልኩ እርስ በእርሳችን መነጋገር ብቻ ነው ብየነበር፡፡ 

ሰላሟ የተጠበቀ ኢትዮጵያን እመኛለሁ ምክንያቱም ጥቂት ሰዎች ነገሮችን ከብዙ አቅጣጫ በመመልከትለምን’? ይላሉ፡፡ 

ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም ሆነው የማያውቁትን ነገሮችለምን መሆን አይችሉም’? የሚል ምኞት በማቅረብ እናገራለሁ፡፡ 

ሁላችንም ኔልሰን ማንዴላ በተጓዙበት መንገድ መጓዝ እንችላለን በማለት በድፍረት በመናገር ያለኝን እምነት አገልጻለሁ፡፡ 

ትምኔታዊዋን ኢትዮጵያ ለማየት በድፍረት አልማለሁ! ለምን አይሆንም? እላለሁ፡፡ 

በህልም ትችቴ ላይ ለመውደድ ጊዜ አለው፣ ለመጥላትም ጊዜ አለው፣ ለጦርነትም ጊዜ አለው እናም ለሰላምም ጊዜ አለውበማለት የክርክር ጭብጥ በማቅረብ የመንፈሳዊ ጥቅስ አቅርቤ ነበር፡፡ 

ከሁለት አስርት ዓመታት የዘህወሀት የጭቆና አገዛዝ በኋላአሁን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር መሰረት ስንት ሰዓትነው?” የሚል ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ 

አሁን ጊዜው የሰላም ነውስለ ሰላም የምናልምበት ከፍተኛ ጊዜ፡፡ መራራውን የጥላቻ መንፈስ በእርቀ ሰላም የምንተካበት፣ህብረተሰቡን የሚያቆስለውን ጥላቻን በፍቅር የምንተካበት፣ በቀልን በይቅርታ የምንለውጥበት፣ ተስፋቢስነትን በተስፋየምንተካበት፣ ቁስልን በፈውስ የምንሽርበት፣ ፍርሀትን በድፍረት የምንቀይርበት፣ ክፍፍልን በአንድነት የምንተካበት፣ ጥርጣሬንበመተማመን መንፈስ የምንቀይርበት፣ ውርደትን በክብር የምንተካበት፣ ማጭበርበርን በቀጥተኛነት እና በታማኝነት የምንተካበት፣ግንፍልተኝነትን በአምክንዮአዊ አቀራረብ የምንተካበት፣ ጭካኔን በሩህሩህነት የምንቀይርበት፣ ጥላቻን በጓዳዊነት የፍቅር ስሜትየምንተካበት፣ አታላይ ነገር ሰሪነትን በግልጸኝነት የምንቀይርበት፣ ቃልን በተግባራዊ ድርጊት የምንተካበት፣ ልዩነትን በፍቅርየምንገልጽበት፣ ያልሰለጠነ ኋላቀር አስተሳሰብን በጨዋና በሰለጠነ አስተሳሰብ የምንተካበት፣ ጥርጣሬን በመተማመንየምንቀይርበት፣ ስግብግብነትን በለጋስነት የምንተካበት፣ ታማኝየለሽነትን በታማኝነት የምንቀይርበት፣ ምቾትን እና ድሎትንበክብር እና ሞገስ የምንተካበት፣ ተራ የማጭበርበር ኢሞራላዊ ስብዕናን በሞራላዊ ስብዕና መቀየርን፣ ድንቁርናን በእውቀትመተካትን፣ ጠባብ አስተሳሰብን በአርቆ አሳቢነት መተካትን፣ ብልግናን በሰለጠነ አካሄድ መቀየርን፣ ምኞትን በስኬት መተካትን፣የጭቃ ጅራፍን እና ስህተት ፈላጊነትን ብሄራዊ ውይይት በማድረግ መተካትን ጊዜው መቼም ሳይሆን አሁኑኑ ነው፡፡ 

ለመነጋገር እና ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ብያለሁ! ለሰላማዊ ለውጥ እውንነት ጊዜው አሁን ነው! 

ሆኖም ግን የዘረዘርኳቸው ቃሎቼ ምንም ሰሚ ጆሮ ሳያገኙ እንዲያው በአየር ላይ ተበትነው የቀሩ ይመስላሉ፡፡ 

.. 2015 እየተጠናቀቀ ባለበት በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የታላቁን የአሜሪካ አብዮተኛ የፓትሪክ ሄንሪን ቃላትበመጠቀም ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እና የበለጠ ግልጽነትን በተላበሰ መልኩ ከእኔ ቃላት በበለጠ ሁኔታ እንዲህ እያሉለሰላማዊ ሽግግር ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡ 

ለሰው ልጅ በተስፋ ውስጥ መኖር ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ለሚያም እውነታ ዓይኖቻችንን ድርግም አድርገን እንዘጋለን፣ እናም የዚያሙዚቃ አባዜ ወደ አውሬነት እስከሚቀይረን ድረስ ዝም ብለን በትዕግስት እናዳምጠዋለን፡፡ ይህ ድርጊት ለነጻነት ሲባል በታላቅእና በአስቸጋሪ ትግል ውስጥ የሚገኝ ብልህ ሰው ሊፈጸመው የሚችል አካል ነውን? እኛ ሁላችንም ዓይኖች እያሉን የማናይ፣ጆሮዎች እያሉን መስማት የማንችል ዝም ብለን ምንም ዓይነት ስሜት ሳይሰማን፣ ለምንም የማንፈይድ ዜጎችን ከአደጋ ለመጠበቅየማንችል ፍጡራን ሆነን ቀጥለናልን? በእኔ በኩል የፈለገውን ያህል ጭራቃዊ መንፈስን የተላበሰ ድርጊት ይሁን ሁሉንም እውነታለማወቅ፣ እንዲሁም መጥፎውን ነገር በመጥፎነቱ አሳምሬ ለማወቅ እና ለዚህም መፍትሄ ለመስጠታ ጥንቃቄ በማድረግእሰራለሁ፡፡

ሰዎች ሰላም፣ ሰላም በማለት ይጮሃሉ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት ሰላም የለም፡፡ ጦርነቱ በእርግጠኝነት ተጀምሯል፡፡ በቀጣይነትከስተሰሜን አቅጣጫ የሚነፍሰው ሞገድ ግልጽ የሆነ የመሳሪያ ግጭን ለጆሯችን የሚያደርስ ነው! ወንድሞቻችን በአሁኑ ጊዜቀጥታ በጦር ሜዳ ውስጥ ናቸው! እኛ እዚህ ስራፈት ሆነን የተቀመጥነው ከቶ ለምንድን ነው? ህይወት እንደዚህ ውድ ነው ነገርነው ወይስ ደግሞ ሰላም በሎሌነት እና በአሽከርነት ዋጋ የሚገዛ እንደዚህ ያለ ጣፋጭ ነገር ነው? 

ኃያሉ አምላክ እባክህ ቸርነትህ አይለየኝ! ሌሎች ምን መንገድ መከተል እንዳለባቸው የማውቀው ነገር የለኝም፡፡ ለእኔ ግን ነጻነቴንወይም ደግሞ ሞቴን ስጠኝ! 

አመናችሁም አላመናችሁም አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ይመጣል ብዬ የማምነው በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትነባራዊ እውነታዎች ይደግፋሉ በሚል ምክንያት አይደለም፣ ወይም ደግሞ የእኔ እምነቶች በኢትዮጵያ ህዝቦች ሀሳቦችምየተደገፉ ናቸው በሚል ምክንያትም አይደለም፣ እንደዚሁም ደግሞ ህወሀት 11ኛው ሰዓት ላይ ከውድቀቱ ትምህርትበመውሰድ ለውጡን ያፋጥነዋል የሚል እምነት ይኖረኛል በሚል ምክንያትም አይደለም፣ ወይም ደግሞ ህወሀትየሚፈጥረው ግጭት እና የሚከተለው የህዝቦች እልቂት እና የደም ጎርፍ አሳስቦት በምሁርነት ደረጃ እና በሰለጠነአስተሳሰብ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ህዝብን ከእልቂት ይታደጋል ከሚል ምክንያትም አይደለም፣ ኃያልና ሀገራትበጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት በዘህወሀት ላይ ጫና በማሳደር ወደ ህሊናው እንዲመለስ ያስገድዱታል በሚል ምክንያትምአይደለም፣ እንደዚሁም ደግሞበመሆኑ ምክንያት አይደለም 

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ቢሆን ሰላማዊ የሽግግር ለውጥ ሊደረግ ይችላል የሚል እምነት አለኝ ምክንያቱም ሀሳባዊተቆርቋሪ ኢትዮጵዊ ነኝና፡፡ 

ይቀጥላል 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!        

ታህሳስ 12 ቀን 2008 .

Filed in: Amharic