>

ወያኔ በህዝባችን ላይ ያወጀውን ጦርነት ተቋቁምን ድል ለማደረግ [ጁሃር ሙሃመድ]

NO MASTER PLAN!የሕ.ወ.ሓ.ት ኢህኣዴግ መንግስት በሕዝባችን ላይ ያወጀውን ጦርነት በድል መደምደም ብቸኛው ኣማራጭ ሆኖ በመገኘቱ ይህ ኣንገብጋቢና ወቅታዊ መግለጫ ተዘጋጅቷል።
እንደሚታወቀው ሕ.ወ.ሓ.ት መራሹ መንግሥት መጠነ ሰፊውን የመሬት ቅርምት ፖሊሲውን በሃይል ለማስቀጠል ወስኗል። የመሬት ቅርምት ፖሊሲውን በሰላማዊ መንገድ እየተቃወመ በሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ላይም ይፋዊ ጦርነት አውጇል፡፡ ከዚህም ኣልፎ ሥርዓቱ ሕዝባችንን ጭራቅ አድርጎ በመሳል «አጋንንትና ሰይጣን» እያለ እስከ መዝለፍም ደርሷል። ለዚህ አደገኛና እብሪተኛ የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ተገቢው ምላሽ ሊሰጠው ይገባል፡፡ በመሆኑም በሚከተሉት አምስት ፍሬ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
1. በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተተገበሩ ያሉት ህንፃዎችና የመንቀሳቀሻ ስፍራዎችን ዘግቶ የመቀመጥ ኣድማ (sit in)፣ የልቅሶና ሃዘን መግለጫ ሥነ- ሥርዓት፣ ስብሰባዎችን ረግጦ የመውጣትና የአደባባይ ተቃውሞዎች በተሻሉ የፈጠራ ጥበቦች እየታገዙ ሊቀጥሉና ሊስፋፉ ይገባል፡፡
2. ሕ.ወ.ሓ.ት ኢህኣዴግ ሕዝባችንን እየገደለ ያለው መሬቱን ያለማንም ከልካይ እየዘረፈና፣ የራሱን የንግድ ስራ ያለተቀናቃኝ ማካሄድ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በመሆኑም ሥርዓቱን ማንበርከክና አይቀጡ ቅጣት መቅጣት የሚቻለው በኦሮሚያ የሥርዓቱን የንግድ ኢምፓየሮች ሽባ ማድረግ ሲቻል ነው፡፡ ይህም ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ንብረትነታቸው የሕ.ወ.ሓ.ት መሆናቸው የተረጋገጡ ምርቶች ከቶ እንዳይገዙና እንዳይሸጡ ሙሉ በሙሉ ማእቀብ በመጣል፣ ምርትና ንብረቶቻቸውን ማውደም፣ እንዲሁም የፋብሪካዎቻቸው ሥራ ሙሉ በሙሉ እንዲስተጓጎል በማድረግ ነው፡፡ ይህ እርምጃ የሚወሰደው ማንኛውንም አዋጭ መንገድ በመጠቀምና የተሳታፊዎችን ለኣደጋ የመጋለጥ እንዲሁም ሥልታዊ አዋጭነቱንና ማእቀቡ በሥርዓቱ ላይ የሚፈጥረውን የኪሣራ መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል። ሕ.ወ.ሓ.ት በባለቤትነት የሚቆጣጠራቸውን ድርጅቶች፣ አጋሮቹንና የአመራሮቹን ስም ዝርዝር በማሰባሰብ ላይ ስንሆን ይህንንም በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን፡፡ በዚሁ ዙሪያ ተጨባጭ የሆነ መረጃ ያላችሁ ወገኖች የሕ.ወ.ሓ.ት የንግድ ድርጅቶችና የአጋሮቻቸውን ስምና የንግድ ምልክቶች ጭምር የሚገልፅ መልእክት በመላክ ለሕዝባችን ትግል ያላችሁን አጋርነት እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን፡፡
3. ሥርዓቱ ወታደሮቹን ከድንበር አካባቢዎች ወደተለያዩ የኣገሪቱ ክፍሎች ማንቀሳቀስ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም አሁን በበርካታ ከተሞች ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው መንገዶችን የመዝጋት ሥልት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ኣውራ ጎዳናዎችና ገባር መንገዶች በሙሉ መዘጋት አለባቸው፡፡ ይህ የሚፈጸመው በእያንዳደንዱ ከተማና መንደር መንገዶች ላይ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የሚገድቡ ኣንደ ቁዋጥኝ፣ ግንድ፣ ድንጋይና ሌሎችም ነገሮችን በመቆለል ሊሆን ይችላል፡፡ ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎችን የመዝጋት ስራ እንደአስፈላጊነቱ የሚታይ ሲሆን፤ ከየኣካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ኣንፃር ዝርዝር አፈጻጸሙ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡ መንገዶችን መዝጋት ወታደራዊ እንቅስቃሴውን ለመግታት ብቻ ሳይሆን በተራ ቁጥር 2 የተጠቀሰውን የሥርኣቱን የንግድ እንቅስቃሴ ሽባ ለማድረግም በጣም ወሳኝ ሥልት ነው፡፡ ሥርዓቱ ለዘረፋና ለግድያ ኣላማው እንደፈለገው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማስቆም ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ ኣንልም፡፡
4. ከአገር ውጪ የምንገኝም ወገኖች የተቃውሞና የጉትጎታ (ሎቢ) ስራችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን፡፡ በቅርብ ያሉ ወዳጆቻችንን በጉዳዩ ዙሪያ ከማሳመንና የውጪ መንግሥታት ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ ከማሳደር ጎን ለጎን ዋነኛ አላማችን ሊሆን የሚገባው በአውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራሊያ የሕ.ወ.ሓ.ት መንግስትን የዲፕሎማሲና የንግድ እንቅስቃሴ ማሽመድደመድ ነው፡፡ (የዚህ ሥልት ትግበራ ዝርዝር ሁኔታዎች ለየኮሚኒቲው ሁሉ በህቡእ ይገለጻሉ)
5. ዛሬ በዚህ ወቅት ወደኋላ ከማንመለስበት የትግል ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ የፖለቲካ አመራሮቻችንና የመረጃ ባለሞያዎቻችንን ኣቅም ለማሰባሰብ፣ የኣፈፃፀም ኣቅማችንን ለመገንባትና ለመጪው ዘመን ቀጣዩን መንገድ ለመቀየስ በፍጥነትና በቁርጠኝት ሊንንቀሳቀስ ይገባል፡፡ የሕ.ወ.ሓ.ት ‹‹ጥንካሬ›› ፍርሃታችን የፈጠረው እንደመሆኑ መጠን ትብብራችንም ይህን ‹‹ጥንካሬ››ውን ያከስመዋል፡፡ የፍርሃት ሥነ-ልቦና ካለፈው ወር ጀምሮ ከህዝባችን ላይ ሙሉ በሙሉ ተገፏል፡፡ አሁን ትብብራችንን በመንፈግና አቅማቸውን በማዳከም፤ በመሬታችን ላይ ወታደራዊና የንግድ እንቅስቃሴያቸውን ማካሄድ ከቶ ከማይችሉበት ደረጃ ማድረስ ይገባናል፡፡

ድል ለሰፊው ሕዝባችን!

Filed in: Amharic