>

ማፈናቀል እንደገንዘብ[ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም]

profeser Mesfen Weldemariam Quateroከ1966 ዓ.ም. በፊት መሬት አገር ነበር፤ ከዚያ በኋላ እስከ1983 መሬት የጋራ ሀብት ሆነ፤ ከ183 ወዲህ መሬት ገንዘብ ሆነ፤ ጡንቻ ገንዘብ ሆነ፤ መሬት ጡንቻና ገንዘብ ሆነ፤ አገር የት ደረሰ?
በጡንቻ ሀብታም መሆን ይቻላል፤ በጡንቻ ገበያውን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ሻጩን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ገዢውን መቆጣጠር ይቻላል፤ ገበያውን፣ ገዢውንና ሻጩን መቆጣጠር ከተቻለ ዋጋውን መቆጣጠር ይቻላል፤ እዚህ ደረጃ ላይ ከተደረሰ ምሥጢሩ ግልጽ ይሆናል፤ ምሥጢሩ ምንድን ነው? ዋናው ነገር ጡንቻ ነው፤ ጡንቻ የሀብት ምንጭ ነው፡፡
ጤንቻ ካለ ተማሪ ቤት ወይም ሀኪም ቤት፣ ወይም አንድ መሥሪያ ቤት ለመሥራት በሚል ሰበብ አንድ መቶ ቤተሰቦችን ከኑሮአቸው ማፈናቀል ሕጋዊ ያሆናል፤ አንድ መቶ ቤተሰቦች ሰፍረውበት የነበረው በአማካይ በነፍስ ወከፍ 100 ሜ.ካ. መሬት ነው እንበል፤ አንድ መቶ ቤተሰቦችን በማፈናቀል የተገኘው መሬት 100×100=10,000 ሜ.ካ. ይሆናል፤ በሊዝ ገበያ ላይ 10,000 ሜ.ካ. መሬት እንደሚከተለው ካሬ ሜትሩ በ20,000 ብር ይቸበቸባል፤ 10,000×20,000=200,000,000 ብር! ሳይሠሩ፣ ሳይለፉ፣ ሰዎችን በጡንቻ ትእዛዝ በማፈናቀል ብቻ የሚገኝ የጡንቻ ትርፍ!
አንድ ሺህ ቤተሰቦችን ማፈናቀሉ የበለጠ ትርፍን ያስገኛል፤ — 1,000x100x20,000=2,000,000,000 ብር! ምን የመሰለ ዘመናዊ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻ ይሠራል! ገንዘብ ካነሰም ማፈናቀል ነው!

Filed in: Amharic