>

ጋዜጠኞችን ማዋከቡ ቀጥሏል፤ የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ማዕከላዊ እንዲቀርብ ታዘዘ

በየ15 ቀኑ ለንባብ በምትቀርበው ዕንቁ መጽሔት በዋና አዘጋጅነት ይሰራ የነበረው ጋዜጠኛና ደራሲ ኤልያስ ገብሩ በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ እንዲቀርብ መታዘዙን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ኤልያስ ገብሩ በማዕከላዊ ቃሉን እንዲሰጥ የታዘዘው ከመጽሔቱ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ቢታወቅም በየትኛው ወር ወይም አመት በቀረበ የዕንቁ ህትመት እንደሆነ አልታወቀም፡፡ጋዜጠኛው ከመጽሔት ዋና አዘጋጅነት በተጨማሪ የ”ሳይኮሎጂና ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት የተሰኙ መጻህፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወቃል፡፡

ምንጭ: freedom4ethiopian

 

Filed in: Amharic