>
5:13 pm - Thursday April 18, 1630

በ አነ አስክንድር ነጋ ላይ የተሰራው ድራማ በዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ላይም ቀጠለ

የዞን ፱ ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች በዝግ ችሎት በተሰየመው የፍርድ ውሎ ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለት በቀነ-ቀጠሮ ወደ ነበሩበት ማእከላዊ እስር ቤት ተመልሰዋል።አስማማው፣ተስፋለም፣ኤዶም፣ዘላለም፣አጥናፍና ናትናኤል አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተገኙት አጆቻቸውን በካቴና ተጠፍረው ሲሆን፣በስፍራው የተገኙት የውጪ ዲፕሎማቶች፣ የውጪ አገር ጋዜጠኞች፣ቤተሰቦቻቸውና የሞያ አጋሮቻቸው በችሎቱ ላይ አንዳይገኙ ታግደዋል። ምክንያቱ ደግሞ ኢህኣዲግ ”ሰዎች በህግ ፊት በግልጽ አንደሚዳኙ ህገ -መንግስቱ ቢደነግግም” የውሸት ድራማ” በሚያዘጋጅበት ጊዜ ‘ዝግ ችሎት’ መጠቀሙ ግድ ነው።

የጦማሪዎቹና የጋዜጠኞቹ ጠበቃ አምሐ (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ) ደምበኞቻቸው ወደሚገኙበት ማዕከላዊ ለጥየቃ ሲመላለሱ ቢቆዩም፣ ፈቃድ በማጣታቸው ጋዜጠኞቹ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ዕለት አንደማንኛውም ሰው ነበር እስረኞቹን የተመለከቱዋቸው።ጦማሪዎቹና ጋዜጠኞቹ የተመሰረተባቸው ክስ የሽብር ክስ መሆኑም ጠበቃ ኣመሃ በኣጽንኦት ተችተዋል።ወያኔ ኢህ ኣዲግ ጋዜጠኞችንና ኣክትቪስቶችን በሽብርተኝነት ወህኒ ቤቶችና አስር ቤቶች መወርወሩ የለመደው በመሆኑ፣ ኣሁንም በ”ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል፣ ስለሚያገባንም አንጦምራለን” በማለት በማህበራዊ ድረ- ገጾች ላይ ኣመለካከታቸውን በህብረት በማስተጋባት ላይ በተሰማሩት ጦማሪዎች ላይ የ ኣስር ቀናት ለግንቦት ፲ ቀን 2006 (May 17) ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። በዛሬው ዕለት በዋለው ዝግ ችሎት ፖሊስ ” ጋዜጠኞቹና ጦማሪዎቹ በሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ነበራቸው እጠረጥራቸዋለሁ ገንዘብ በመቀበል፤ ላፕቶፕ፤ ኮምፒውተርና ሌሎች የጽሕፈት መገልገያዎችን ገዝተዋል፤ ሰልጥነዋል፤ ለማሰልጠን ተዘጋጅተዋል፤”በሚል መክሰሱም ተደምጦኣል።
ዓለም ኣቀፍ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎችና ትልልቅ የመገናናኛ ኣውታሮች ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች የ እስር ሁኔታቸው ማሳሰቡን በመጠየቅም በመዘገብም ሽፋን በመስጠት ላይ ሲሆኑ፣ስርዓቱና – የስርዓቱ ኣቃንቃኞች የተለመደውን ድራማቸውን በሽብር ሽፋን አነ አስክንድር ነጋ ላይ የስሩትን ድራማ መስራታቸውን ቀጥለውበታል።

 

Filed in: Amharic