>
5:13 pm - Saturday April 18, 3891

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን Citizen journalists of the year አሸናፊ ሆኑ

ዞን ዘጠኝ 

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን Reporters sans frontières / Reporters Without Borders / RSFበየአመቱ በሚያዘጋጀው የሽልማት ውድድር የዞን ዘጠኝ ጦማርያን Citizen journalists of the year አሸናፊ ሆኑ

Reporters-without-borders logoበትላንትናው ዕለት በፈረንሳይ ስትራስበርግ በተካሄደው ሥነ-ስርዓት የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ በማለት የሶሪያዋን ዜይና ኤርሃምን የሸለመ ሲሆን በዜጋ ጋዜጠኝነት ደግሞ የዞን ዘጠኝ ጦማርያንን ሸልሟል እንዲሁም የዓመቱ ሚድየም በሚል የቱርኩCumhuriyet Gazetesi አሸናፊ ሆኗል፡፡
ጦመርያኑ ጋር ከኩባ ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ኢራን፣ ሲንጋፖር፣ ቻይና እና ቬትናም ከሚገኙት ጋር ተወዳድረው ነው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት፡፡
የዞን ዘጠኝ ጦማርያንን በመወከል ዘላለም ክብረት በቦታው ለመገኘት ያደረገው ጥረት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመንግስት እንዳይወጣ በመደረጉ ምክንያት ሳይሳተፍ ቀርቷል፡፡
ዘላለም በፍትሕ ሚኒስቴር በሐምሌ መጀመሪያ ክሳቸው ተቋርጦ በነጻ ከእስር ከተለቀቁት ጦማርያን አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Filed in: Amharic