>

የዛሬውን ችሎት አስመልክቶ ከዞን9 ጦማር የተሰጠ ማስታወሻ

ዛሬ ጥቅምት 5 2007 በዋለው ችሎት አንድ አመት ከ5 ወር እስር ቤት የቆዪት አራት የዞን9 ጦማርያን ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

zone 9- 15102015በውሳኔው መሰረት አንደኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ መከላከል ሳያስፈልጋት ከክሱ ነፃ
ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
አምስተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ መከላከል ሳያስፈልገው ከክሱ ነፃ
ስድስተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ መከላከል ሳያስፈልገው ከክስ ነፃ የተባሉ ሲሆን
ሁለተኛ ተከሳሽ ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ከሽብር ክስ ነፃ የተባለ ሲሆን መአከላዊ ምርመራ በሃይል እና በማሰቃየት የሰጠው ቃል ላይ አመፅ እንዳነሳሳ አምኗል በሚል በወንጀል ህጉ 257 መሰረት እንዲከላከል ግን ዋስትና መጠየቅ እንደሚችል ተገልፇል።

የጦማርያኑ ጠበቃ በፍቃዱ ይግባይ እንዲሰጠው የጠየቁ ሲሆን አቃቤ ህግ ተቃውሞ አሰምቶ ይግባኙ ላይ ለጥቅምት 10 ለማየት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ባለፉት 1 አመት ከ5 ወራት በማንኛውም በቻላችሁት አቅም ሁሉ ከጎናችን ለቆማችሁ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን በፍቃዱ ይፈታ የሚለው ጥያቄያችን እንደሚቀጥል ለማሳወቅ እንወዳለን።

የዞን 9 ጦማርያን ከማረሚያ ቤት ሲወጡም የምናሳውቅ ይሆናል።

እልፍ ምስጋና ለዞን9 ነዋርያንና ወዳጆች
ስለሚያገባን እንጦምራለን
ዞን9

Filed in: Amharic