>
2:36 am - Sunday October 21, 2018

የዲሲ ሽኩቻ[ አርአያ ተስፋማሪያም]

Moneyበዲሲ በሚገኘው ቅ/ማርያም ቤ/ክ ሽኩቻና ፍጥጫው ቀጥሏል። ትላንት ምሽት 5 ሰዓት የፈጀ የስልክ ኮንፍረንስ ነበር። በአብዛኛው ወሬው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነበር። የገረመኝ የዳይቆንና ቄሶች ስም እየተጠቀሰ «በአመት 40 ሺህ ዶላር እያገኙ..አነሰን ብለው እንዲጨመርላቸው ጠየቁ»፣ በመቀጠል ደግሞ « እከሌ የተባለው ዳይቆን ሁለት እጃችሁን ወደላይ ከፍ አድርጉ፣ አሁን እጃችሁን ኪሳችሁ ውስጥ ክተቱ፤ በኪሳችሁ ያለውን ገንዘብ በሙሉ አውጡና ቅርጫት ውስጥ ከተቱ…ካለ በኋላ ጠራርጐ ይዞት ይሄዳል» ተባለ። አንዱ የኰሚቴ አባል «ያለን ተቀማጭ ሂሳብ 3.5 ሚሊዮን ነው» ሲል ሌላው ደግሞ 4 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ተናግሯል። በተጨማሪ « ፍርድ ቤት ይለየናል፤ ለእነሱ ከተፈረደ ማርያም ሳር ይበቅልባታል፤ ትዘጋለች» እያሉ ያስፈራሩም ነበሩ። ባጠቃላይ ስለቅ/ማርያም ወይም ስለእምነቱ ሳይሆን ገንዘብን ኢላማ ያደረገ «ፍልሚያ» ነው የሚታየው። እንዳውም «ነገ ይለይልናል» እያሉ የሚዝቱ ነበሩ። አገሩ አሜሪካ መሆኑን የዘነጉ ይመስላል።.. በአሁኑ ወቅት 7 ሚሊየን ወገናችን ተርቧል። 4 ሚሊዮን ዶላሩ ለነዚህ ወገኖች ስንዴ ተገዝቶ ይላክበት እላለሁ። በዚያውም ያሰፈሰፉት ዝም- ጭጭ ይላሉ። ጐበዝ ስንት አመት ለመኖር ይሆን!? ስንት እንጀራ ለመብላት?…ፈጣሪን መፍራት ቀረ ማለት ነው!?..እደግመዋለሁ ገንዘቡ ለተራቡ ወገኖቻችን ይዋል!?..በነገራችን ላይ ፓስተር የተባሉ «ደ/ዘይት ህፃናት እንረዳለን»በሚል በአመት 5ሚሊዮን ዶላር ከሃይማኖት ተከታዩ ሰብስበው ኪሳቸው ይከታሉ።

Filed in: Amharic