>

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የመጨረሻ መጽሃፍ – መጽሃፍ ቅዱሱን ተነጠቀ!!

(ዳዊት ከበደ ወየሳ እንደዘገበው)

Eskindir nega 1ሃሳቡን በጽሁፍ ስላቀረበአሸባሪተብሎ 18 አመት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ በእስር ቤት ውስጥ በከፍተኛ ጫና እየደረሰበት መሆኑ ተገለጸ።ምንም ነገር ማንበብም ሆነ መጻፍ ተከልክሏል። በአንድ ለሊት እስከሶስት ግዜ ክፍሉ እየመጡ፤ ከእንቅልፉ በመቀስቀስ ፍተሻ ያደርጉበታል። ይህ ሁሉየሚደረገው ደግሞ ከህግ እና ህገ መንግስቱ ተጻራሪ በሆነ መንገድ ነው። 

ለምሳሌበህገ መንግስቱ አንቀጽ 21 ላይ፤የህግ እስረኛ መብት ሊጠበቅ ይገባል።ይላል። አንድ ታሳሪ ሰብአዊ ክብሩም መጠበቅ እንዳለበትይዘረዝራል። ይህ ብቻ አይደለም። በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 2 ላይማንኛውም እስረኛ ከሚቀርበው ሰው ጋር መገናኘት ይችላልይልና መብቱን በዝርዝርሲገለጽከትዳር ጓደኛው፣ ከቅርብ ዘመዶች፣ ጓደኞች ከሃይማኖት አማካሪው፣ ከሃኪሙ እና ከህግ አማካሪው ጋር የመገናኘት መብት እንዳለው ብቻሳይሆን፤ ስለጾም እና ጸሎት ለመማከር ቢፈልግ የሃይማኖት አባት ማነጋገር እንደሚችል ተደንግጓል።
 
በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ግን ራሳቸውን ከህገ መንግስቱ በላይ ያደረጉ የወህኒ ቤቱ አዛዦች ሰብአዊ መብቱን የሚጋፉ ድርጊቶች በተደጋጋሚሲፈጽሙበት ቆይተዋል። ይህም በጨለማ ቤት ውስጥ ከማሰር ጀምሮ ቤተሰብ እና ጓደኞቹ እንዳይጠይቁት እስከማድረግ ድረስ ይዘልቃል። በተለይምከቅርብ ግዜ ወዲህ ገብረወልድ የተባለ ደህንነት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ተመድቦበት፤ በቁም እንዲሰቃይ እያደረገው ነው። በቀን እና በለሊትበማንኛውም ግዜ ጋዜጠኛ እስክንድር ወደታሰረበት ክፍል በመግባት ያዋክበዋል፤ የሚጠቀምበትንም ቁሳቁስ ይወስድበታል።
 
 ለምሳሌእስረኞች እዚያው ከሚሰሩትና ገዝተው ከሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች መካከል እዚያው ግቢ ውስጥ የሚሰራው መቀመጫ አንዱ ነው። ይህንመቀመጫ ከጋዜጠኛ እስክንድር ክፍል ውስጥ ወስደውበታል። እንዲህ ያለ ተራ ተግባር ነው እየተፈጸመ ያለው። ከእስር ቤት አካባቢ የደረሰን መረጃእንደሚያስረዳው፤ መቀመጫ ወንበሩን ከጋዜጠኛው ላይ ከወሰዱበት በኋላ፤ በእስር ክፍሉ ውስጥ የሚገኘውን ባልዲ ገልብጦ፤ እንደወንበርይጠቀምበታል።ይህን ዘገባ ሲመለከቱ ደግሞ፤ ይህቺኑ ባልዲ ሊወስዱበት ይችላሉብለውናል ዘገባውን ያደረሱልን ግለሰቦች።
 
ይህን እንደምሳሌ ገለጽን እንጂ፤ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ከዚህ በላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሲደርስበት ነበር፤ አሁንም እየደረሰበት ነው። በአሁኑወቅት ምንም አይነት መጽሃፍ ወይም ወረቀት እንዲኖረው አይፈቀድለትም። ባለፈው ሳምንት ክፍሉን የበረበረው ገብረወልድ ሲያስጠነቅቀው፤እስክሪብቶ እንኳን ይዘህ እንዳይህ አልፈልግም።ሲል ነበር የዛተበት። ሌላው ቀርቶ እስክንድር ያነበው የነበረውን የመጨረሻ መጽሃፍመጽሃፍቅዱሱን ጭር ወስደውበታል። ይህን መጽሃፍ ቅዱስ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል የሰጠችው ነበር። ከምንም ነገር በላይ ግንከአምላኩ ጋር የሚገናኝበት፤ በጸሎት ግዜ የማይለየውን መጽሃፍ ቅዱስ የወሰዱበት የጋዜጠኛውን ቅስም ጭምር ለመስበር ቢሆንም፤ ጋዜጠኛ እስክንድርነጋ ግን አሁንም በመንፈሰ ጠንካራነት ከሚታወቁት እስረኞች መካከል አንዱ ነው።
 
ኢትዮጵያ በህገ መንግስቷ ላይ እንደተገለጸው ከሆነ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን ትቀበላለች። ሆኖም በጋዜጠኛ እስክንድር ላይ የሚደርሰው ግፍ ግን የሰው ልጅ ሊሸከመው የሚከብድ ነው። ትላንት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን መብት መከበር ይቆረቆር እና ይጽፍ የነበረው ጋዜጠኛ ህክምና ጭምር ተከልክሎ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ተጠይቆ ፈቃደኛ ባለመሆኑጥርስ ተነክሶበታል። እንደኢትዮጵያ አለም አቀፉን የሰብአዊ መብት አያያዝ የፈረሙ አገሮች የእስረኞችን ሰብአዊ ክብር ይጠብቃሉ። እስረኞች እንደየሃይማኖታቸው መጽሃፍ ቅዱስም ሆነ ቅዱስ ቁርአን እንዳያነቡም ሆነ እንዳይኖራቸው አይከለከሉም፤ በኢትዮጵያ ግን እየሆነ ያለው ከዚህ በተቃራኒ ነው። (በዚህ አጋጣሚ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች – የጋዜጠኛው መጽሃፍ ቅዱስ እንዲመለስለት ጠቅላይ ሚንስትሩን እንዲጠይቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን)
 
በአሁኑ ወቅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በታሰረበት ክፍል ውስጥ፤ እሱን ጨምሮ አምስት እስረኞች አሉ። ከነሱም ውስጥመንግስትን በሃይል ወይምበመፈንቅለ መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ አድርጋችኋልተብለው ሞት የተፈረደባቸው ጌታቸው ብርሌ እና መላኩ ተፈራ፤ ከመኢዴፓ ክንፈሚካኤልደበበ (አበበ ቀስቶ) እና በከፍተኛ ሙስና የታሰረው የጉምሩኩ ገብረዋህድ አብረው ነው የታሰሩት።
 
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከታሰረ በኋላ፤ ሃብት እና ንብረቱንገንዘብ እና ቤቱን ሳይቀር መንግስት አግዶበታል። የወላጆቹን ንብረት እንዳይሰበብ ሆኗል።በሚሊዮን ይቆጠር የነበረውን እና እናቱ በባንክ አካውንታቸው ያስቀመጡት ገንዘብ ከፍርድ ቤት እግድ ውጪ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል። እናቱ በህይወትበነበሩበት ወቅት፤ ክሊንካቸውን እንዲዘጉ ከተደረጉ በኋላ ንብረታቸውን አዘርፍታል። አራት ኪሎ የሚገኘው ቤታቸው ተወስዶባቸው ሆቴል ውስጥ ነበር የሚኖሩት። በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ፤ የእስር ብቻ ሳይሆን የግል መኖሪያ ቤቱ እና ንብረቱ ጭምር እግድ ወጥቶበታል። ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን ከሁለትአመት በፊት፤ የመጨረሻ ውሳኔ ሲሰጠው፤እኛ ሁላችን እናልፋለን። ልጄ ናፍቆት እክንድር አድጎ፤ አንድ ቀን ንብረታችንን ያስመልሰዋል።የሚል ምላሽለፍርድ ቤቱ መስጠቱ ይታወሳል።
 
ከዚህ በታች ያወጣነው ለፍርድ ቤቱ የተጠየቀው የእግድ ደብዳቤ ነው። 
eskinder2-300x213በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው፤ 1ኛ ንፋስ ስልክ ላፍቶ የሚገኘው G+2 መኖሪያ ቤት፤ ከእናቱ በውርስ ያገኘው የካ ወረዳ የሚገኘው ትልቅ ቪላ ቤት እንዲሁም ልጁን ናፍቆት እስክንድርን ትምህርት ቤት ያመላልሱበት የነበረው አቶዝ መኪና በባለቤቱ በወ/ሮ ሰርካለም ተመዝግቦ እንደሚገኝ ደብዳቤው ገልጾ፤ በመንግስት እንዲወረስ ጥያቄ ቀርቧል።
Filed in: Amharic