>
5:13 pm - Friday April 19, 2847

የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሶስት ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

የፍኖተ ነጻነት ዋና ኣዘጋጅ ነብዩ ሃይሉ ከ፮ ቀን አስራት በኋዋላ ተፈታ
በዛሬው ዕለት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሶስት ጋዜጠኞች በኣራዳ ችሎት የሚቀርቡ ሲሆን፣ ከታሰሩበት ጊዜ ኣንስቶ ከቤተሰብም ሆነ ከጠበቃ (ከህግ ባለሙያ) ጋር ያለመገናኘታቸውንና ያለመጎብኘታቸውን በውጭ ያሉት የዞን ዘጠኝ ግብረ ሃይሎች በምሬት አየተናገሩ ነው።
አነዚሁ ጦማሪዎች በአስር ጊዜ ቆይታቸው የኢሜል ኣካውንታቸውንና፣ ፓስወርዳቸውን አንዲሰጡ በስርዓቱ ኣሳሪዎች የተገደዱ ሲሆን፣ በዚሁም የተነሳ የተለያየ ኣካላዊ ጉዳት አንደደረሰባቸው ተገልጾኣል።
በዛሬው ዕለት የዞን ዘጠኝ ስድስት ጦማሪዎችና ሶስት ጋዜጠኞች በኣራዳ ወረዳ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን፣ ህወሃት ኢህ ኣዲግ ቀደም ሲል በጋዜጠኛ አስክንድር ነጋና በሌሎችም ላይ አንደሚያዘጋጀው የሃሰት ወንጀል ታሳሪዎቹን በሽብርተኝነት ይከሳል፤ ኣለያም በቀጠሮ ያመላልሳል የሚለው የብዙዎች ግምት ሲሆን፣ በኣንጻሩም በፍርድ ቤት ውሎው ላይ ድጋፋቸውንና ትብብራቸውን ለማሳየት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ግብረ ሃይል በማህበራዊ ገጾች፣ በስልክና በመሳሰሉት ጥሪያቸውን ኣስተላልፈዋል። ብዙ የኣዲስ ኣበባ ወጣቶች ወደ ኣራዳ ፍርድ ቤት አየተመሙ ነው።

በተያያዘ ዜና የፍኖተ ነጻነት ዋና ኣዘጋጅ የሆነው ነብዩ ሃይሉ በትዊተር ገጹ ”ከ፮ ቀናት እስር በኋላ ትላንት አመሻሹ ላይ ከዘብጥያ ወጥቻለሁ፡፡ በህገወጥ እስር ተይዤ በነበርኩባቸው ቀናት በተለያዩ መንገዶች ላበረታታችሁኝ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡” በማለት መታሰሩን ሲወተውቱ ለነበሩ፣ የመናገርና የመጻፍን ነጻነት ለሚያደንቁ ወዳጆቹ ኣስተላልፎኣል።

Filed in: Amharic