>

የአርበኛው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል በኖርዌይ ይከበራል

Happy 60 birthday to Andargachew Tsige - posterየነጻነትና የፍትህ ታጋዩ አርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ትውልድ ገዳይና ሰው በላ መዳፍ እጅ ከወደቀበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በእልህ፣ በቁጭትና በቁርጠኝነት ከበፊቱ በበለጠ ትግላችንን አጠናክረን እንድንቀጥል አድርጎናል።ዘረኛውና አረመኔው ወያኔ አንዳርጋቸውን በመያዝና በማሰር የነጻነት ትግሉ ወደ ኋላ ይገታል ብሎ የቅዠት ህልም ቢያልምም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ግን ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች በመሆን የቆመለትን ዓላማ  ከግብ ለማድረስ ተግተን ተነስተናል።
ይህንንም ለማረጋገጥ ለኢትዮጵያ አገራችን ነጻነትና ፍትህ ለማስፈን የህይወት መስዋትነትን እስከ መክፈል ድረስ እየታገለ የሚገኘውን የነጻነት ተምሳሌት የጀግናው አንዳርጋቸው ጽጌ  ፷ኛ ዓመት የልደት በዓልን በዓለም አቀፍ ደረጃ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን። 

ስለዚህ ዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት በኖርዌይ ለምትኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ  በልደት በዓሉ ላይ ተገኝታችሁ ለአንዳርጋቸው የአላችሁን አክብሮት ትገልጹ ዘንድ ተጋብዛችኋል።
 
በዝግጅቱም ላይ 
  • የአርበኛው አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ ነጻነት ያደረገው አስትዋጾ በዝርዝር
  • የትግል ዓላማውና ለኢትዮጵያ ያለው ራእይ 
  • ሥነጽሁፎችና ስሜት ቀስቃሽ አገራዊ የኪነ ጥበብ ዜማዎች እና ሌሎችም ይቀርባሉ
ቀን፡ ፌብሯሪ 14/2015 ከ16፡00_ 22፡00 ስዓት
የዝግጅት ቦታ: Antirasistisk Center, Storgaten 25 
የአንዳርጋቸውን ራእይ እውን እናደርጋለን!
ወያኔን ከህዝባችን ጫንቃ ላይ እናወርዳለን!
የኢትዮጵያን የክብር ትንሳኤ እናያለን! 
 
ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ዲሴሶን ወጣቶች ክፍል
Filed in: Amharic