>

የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት የነገው የአደባባይ ተቃውሞ ሰልፍ እንደማይታጠፍ ውሳኔ ማስተላለፉ ታወቀ

ፍኖተ ነጻነት

Andinet poster on demo.የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት በምርጫው ለመወዳደር መወሰኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ኢህአዴግ እያደረጉት ያለውን ስውር ደባ እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቢቆይም መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመገኘቱ ምክንያት ‹‹መብታችንን ለማስከበር አንለምንም›› በማለት በነገው እለት ማለትም ጥር 17/2007 ዓ.ም በ5 ከተሞች የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በመንግስትና በተለያዩ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አካላት ፓርቲው የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ቀን እንዲቀይርና ከመንግስት አካላት ጋር ድርድር እንዳያደርግ ጥረት ቢደረግም የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባደረገው ልዩ አስቸኳይ የምክር ቤት ስብሰባ ሰልፉ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች እንደሚደረግና ለዚህም የሚያስፈልገውን ክፍያ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን በማረጋገጥ ስብሰባውን ማጠናቀቃቸውንና ከአዲስ አበባ በተጫማሪ ሌሎች ከተሞች እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲልም መመሪያ የሰጠ ሲሆን በአሁን ሰዓት የአንድነት አዲስ አበባ ምክር ቤት ስለነገው ሰላማዊ ሰልፍ የስራ መመሪያዎችንና የድርጊት መርሀግብሮች ላይ እየተወያየ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡

Filed in: Amharic