>

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የሃያ ሺህ ብር ዋስ ተጠይቆበት ወደ ማረፍያ ክፍል መግባቱ ታወቀ

Elias Gebiru in prison

 

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበበት ክስ የፕሬስ ህጉን በሚፃረር መልኩ ለአራት ቀናት በማዕከላዊ ታስሮ የተለቀቀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ክሱ እንደ አዲስ እንዲቀሰቀስበት ከተደረገ በኋላ ዛሬ በተለምዶ ገዳም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ሁለተኛ የወንጀል ችሎት ከእንቁ መፅሔት አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን ጋር እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡
ችሎቱ በሰጠው ትዕዛዝም ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ እና የእንቁ አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን እያንዳንዳቸው የብር 20,000(የሃያ ሺህ ብር) ዋስ እንዲያቀርቡ እስከዛውም ወደ ማረፊያ እንዲሄዱ አዟል፡፡
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን በአሁኑ ሰዓት ችሎት መድኃኔዓለም አካባቢ በሚገኘው ወረዳ 8 ጣቢያ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡

ምንጭ:- የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ( ኣንድነት)

Filed in: Amharic