>
5:13 pm - Monday April 19, 8477

የግንቦት 7 ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በኖርዌ ኦስሎ በተሳካ ሁኔታ ተደረገ!!

በኣበበ ደመቀ

በግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በአለም አቅፍ ደረጃ በ26 ዋና ዋና ሃገሮችና ከተሞች በመካሄድ ላይያሉት ዝግጅቶች አካል የሆነውና እሁድ ኦገስት 31 በኖርዌይ ኦስሎ የተካሔደው ውይይትና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅትበተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ።

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ከሚደግፋቸው የፖለቲካ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የግንቦት 7 የፍትህ የዲሞክራሲ ንቅናቄ በአለም አቅፍ ደረጃ ያዘጋጀውን የውይይት መድረክ ተከትሎ ንቅናቄውን በገንዘብና በተለያዩ መንገዶች ማጠናከርለነፃነት የሚደረገውን ትግል ማፋጠን እንደሆነ አጥብቆ የሚያምነው የድጋፍ ድርጅቱ ፤ ተግባራዊ እንቅስቃሴውን የጀመረው ፯ የኮሚቴአባላትን ያቀፈ ግብረ ኃይል በማቋቋም ነበር ።

በግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ም/ሊቀመንበር አቶ አበበ ቦጋለ ከቦታው ሲደርሱ ሞቅ ያለ አቀባበል ከተደረገላቸውበኋላ የድጋፍ ድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አቢ አማረ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ለኢትዮጵያናለኢትዮጵያውን ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ እውን መሆን ክቡር ህይወታቸውን ላጡ እንዲሁም በሃገራቸው የንፁሃን ማጎሪያ ካምፖችበእስር ላይ ለሚገኙ የነፃነት አርበኞች የ 1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ የተከፈተው ይኸው ዝግጅት ምንም እንኳ ለጋራ ሀገራችንለነፃነታችን ለምናደርገው እንቅስቃሴ አመስጋኝና ተመስጋኝ ባይኖርም የአቅማቸውን ላበረከቱት ሁሉ የግብረ ኃይሉ ሰብሳቢ አቶ ደባሶመሰለ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ፤ በመቀጠልም የድጋፍ ድርጅቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ዓለሙ ለአቶ አበበ ቦጋለ በድጋፍድርጅቸው ስም የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ በውጭ ሀገር የምንገኜው ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ፤ የሻማማብራት ፤ የረሃብ አድማና የገንዛብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችና ለውጭ መንግስታት የተማጽኖ ደብዳቤ መፃፍና የመሳሰሉትን አካሂደናልበማካሄድም ላይ እንገኛለን ።

Ginbt 7 meeting in Oslo    ይሁን እንጂ የሃገራችን የኢትዮጵያና የህዝባችን የኢትዮጵያውያን መከራና ስቃይ እንዲሁም ከውያኔ እስር እንሰብር ዘንድ የተጠቀሱትክንውኖች የላቀ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ፤ የሚመሩት የድጋፍ ድርጅት ይህንኑ እንቅስቃሴውን አጠናክሮበመቀጠል በሁለገብ ትግል የህዝባዊ ድል ፤ እውን እንደሚሆን አስምረውበታል ።

በመቀጠልም የንቅናቄው ም/ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ፤ በጠላት እጅ መውደቅና ያስከተለው ሁኔታናየኢትዮጵያ ህዝብ ባሳየው የወገንተኝነትና የቁጭት ስሜት ልባቸው መነካቱን ገልፀው ፤ የአቶ አንዳርጋቸው ጅምር ስራዎችን አስመልክቶበንቅናቄያቸው መወሰድ የነበረባቸውን የማስተካከያ እርምጃዎችን መደረጋቸውን ያብራሩ ሲሆን በተጓዳኝ ፤ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌንየትግል ሂደቶች ከውልደት እስከ እድገት ፤ ከቤተሰብ እስከ አገር ፍቅር ፤ ከለንደን እስከ ኤርትራ በርሃ ፤ ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶችበመረጃ በተደገፈ ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ነበር ።

በአጠቃላይ አቶ አንዳርጋቸው መሆን ማለት ፤ እንደ እርሱ ትሁትና ቆራጥ መሆን ማለት እንደሆነ ፤ ለሃገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለትእንደሆነ ፤ ከዘረኝነት ፀድቶ መገኜት መሆን ማለት እንደሆነና ለዚህም በፅናት መታገል ማለት እንደሆነ አብራርተው ለዚህም ትግሉተግባራዊ ተሳትፎ ወደሚጠይቅ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቅሰው ፤ ንቅናቄያቸው በቅርቡ የፈፅመው የውህደት ስምምነት ቁልፍ ሚናእንዳለውና ከሌሎች ንቅናቄዎች ጋርም እንደሚቀጥል አብራርተዋል ።

በማጠቃለያቸውም ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ፤ ለሴት እህቶቻችን ፤ ለወጣቶች የምትመኟትን ኢትዮጵያ መገንባት የወጣቶች ኃላፊነትመሆኑን ጠቁመው ንቅናቄውን በመቀላቀል የፈጠራ ክህሎታችሁን በመጠቀም ንቅናቄውን አዘምኑት ፤ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባትግንባር ቀደም ሚና ተጫወቱ ፤ ተደራጁ ፤ አደራጁ ፤ ታገሉ ፤ አታግሉ ውባን ኢትዮጵያን ለመፍጠር በጋራ እንቁም ብለዋል ።

በዚህም ዝግጅት ላይ ፦ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲ ንቅናቄ ፧ ትሕዴን ታጋይ ሞላ በቴሌፎን

ከአርበኞች ግንባር ፦ አርበኛ መንግስቱ በቴሌፎን

ከሕዝባዊ ኃይሉ ፦ ታጋይ ዘመነ በስካይፒ ተካፋይ በመሆን የድርጅታቸውን ወቅታዊ አቋምና ውህደቱ የፈጠረላቸውን ጥንካሬአብራርተዋል ።Ginbot 7 in Oslo 3

በመጨረሻም አቶ ዳንኤል አበበ የድጋፍ ድርጅቱ መክትል ሊቀመንበር በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን እየደረሰ ያለውን ስቃይና መከራካብራሩ በኃላ ወያኔን ለማስወገድ በጋራ መቀም ወሳኝ መሆኑን አክለውበታል ።

በአጠቃላይ በዚህ ዝግጅት ለንቅናቄው ማጠናከሪያ 255 ሺ 519 ክሮነር ለማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን ፤ ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ የሕዝባዊ ኃይሉመዝሙር የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆናል ።

ይሁን እንጂ የሃገራችን የኢትዮጵያና የህዝባችን የኢትዮጵያውያን መከራና ስቃይ እንዲሁም ከውያኔ እስር እንሰብር ዘንድ የተጠቀሱትክንውኖች የላቀ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ፤ የሚመሩት የድጋፍ ድርጅት ይህንኑ እንቅስቃሴውን አጠናክሮበመቀጠል በሁለገብ ትግል የህዝባዊ ድል ፤ እውን እንደሚሆን አስምረውበታል ።

በመቀጠልም የንቅናቄው ም/ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ፤ በጠላት እጅ መውደቅና ያስከተለው ሁኔታናየኢትዮጵያ ህዝብ ባሳየው የወገንተኝነትና የቁጭት ስሜት ልባቸው መነካቱን ገልፀው ፤ የአቶ አንዳርጋቸው ጅምር ስራዎችን አስመልክቶበንቅናቄያቸው መወሰድ የነበረባቸውን የማስተካከያ እርምጃዎችን መደረጋቸውን ያብራሩ ሲሆን በተጓዳኝ ፤ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌንየትግል ሂደቶች ከውልደት እስከ እድገት ፤ ከቤተሰብ እስከ አገር ፍቅር ፤ ከለንደን እስከ ኤርትራ በርሃ ፤ ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶችበመረጃ በተደገፈ ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ነበር ።

በአጠቃላይ አቶ አንዳርጋቸው መሆን ማለት ፤ እንደ እርሱ ትሁትና ቆራጥ መሆን ማለት እንደሆነ ፤ ለሃገርና ለትውልድ ቤዛ መሆን ማለትእንደሆነ ፤ ከዘረኝነት ፀድቶ መገኜት መሆን ማለት እንደሆነና ለዚህም በፅናት መታገል ማለት እንደሆነ አብራርተው ለዚህም ትግሉተግባራዊ ተሳትፎ ወደሚጠይቅ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቅሰው ፤ ንቅናቄያቸው በቅርቡ የፈፅመው የውህደት ስምምነት ቁልፍ ሚናእንዳለውና ከሌሎች ንቅናቄዎች ጋርም እንደሚቀጥል አብራርተዋል ።

በማጠቃለያቸውም ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ፤ ለሴት እህቶቻችን ፤ ለወጣቶች የምትመኟትን ኢትዮጵያ መገንባት የወጣቶች ኃላፊነትመሆኑን ጠቁመው ንቅናቄውን በመቀላቀል የፈጠራ ክህሎታችሁን በመጠቀም ንቅናቄውን አዘምኑት ፤ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባትግንባር ቀደም ሚና ተጫወቱ ፤ ተደራጁ ፤ አደራጁ ፤ ታገሉ ፤ አታግሉ ውባን ኢትዮጵያን ለመፍጠር በጋራ እንቁም ብለዋል ።

በዚህም ዝግጅት ላይ ፦ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲ ንቅናቄ ፧ ትሕዴን ታጋይ ሞላ በቴሌፎን

ከአርበኞች ግንባር ፦ አርበኛ መንግስቱ በቴሌፎን

ከሕዝባዊ ኃይሉ ፦ ታጋይ ዘመነ በስካይፒ ተካፋይ በመሆን የድርጅታቸውን ወቅታዊ አቋምና ውህደቱ የፈጠረላቸውን ጥንካሬአብራርተዋል ።

በመጨረሻም አቶ ዳንኤል አበበ የድጋፍ ድርጅቱ መክትል ሊቀመንበር በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን እየደረሰ ያለውን ስቃይና መከራካብራሩ በኃላ ወያኔን ለማስወገድ በጋራ መቀም ወሳኝ መሆኑን አክለውበታል ።

በአጠቃላይ በዚህ ዝግጅት ለንቅናቄው ማጠናከሪያ 255 ሺ 519 ክሮነር ለማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን ፤ ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ የሕዝባዊ ኃይሉመዝሙር የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆናል ።

Filed in: Amharic