>
5:13 pm - Monday April 19, 9515

ሕገ መንግሥት የሚባለው  የግድያና የቅሚያ ደንብ  መሻሻል ሳይሆን ተቀዶ መጣል ይኖርበታል!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ሕገ መንግሥት የሚባለው  የግድያና የቅሚያ ደንብ  መሻሻል ሳይሆን ተቀዶ መጣል ይኖርበታል! 
አቻምየለህ ታምሩ
ሕገ መንግሥት ተብዮው የግድያ ፣ የቅሚያና የአፓርታይድ ደንብ  መሻሻል ሳይሆን ተቀዶ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ መጣል አለበት። የዛሬዋ ኢትዮጵያ የተዋቀረችበት የአፓርታይድ ስርዓት [ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ  የፌዴራል ስርዓት ነው  ይሉታል] የተዘረጋው ይህን  የግድያ፣ የቅሚያና የንጥቂያ ደንብ መሰረት በማድረግ  ነው። በመሰረቱ የፌዴራል ስርዓት የድርድር ስርዓት ነው። ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ  ግን በኢትዮጵያ ያቆሙትን  የአፓርታይድ ስርዓት የዘረጉት  አማራና አብዛኛውን  ኢትዮጵያዊ  እንዲገለል አድርገው ነው። ይህም በመሆኑ  ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የቆመው  ስርዓት የሁለቱ ጸረ ሰብ  ድርጅቶች አሐዳዊ የአፓርታይድ አገዛዝ እንጂ   የተቀረው ኢትዮጵያዊውም የሚሳተፍበት ያልተማከለ ወይንም የፌዴራል አስተዳደር አይደለም።
ኢትዮጵያ ልትተዳደርበት ይገባ የነበረው በአባቶቻችን ዘመን  ከጥንት ጀምሮ ትተዳደርበት  በነበረው አይነት ሁሉን አካታች  በሆነ ያልተማከለ አስተዳደር  ወይንም በፈረንጆቹ  አገላለጽ multicultural fedralism በሚሉት  አይነት ስርዓት ነበር።  አባቶቻችን የዘረጉት ያልተማከለ አስተዳደር  ከዘመኑ ጋር አብሮ የማይሄድ እንስከን  ቢገኝበት  እንኳ ዘመኑን እንዲዋጅ  ተደርጎ  መታደስ  ነበረበት እንጂ  ለብዙ ዘመናት ተረጋግቶ የኖረው ያልተማከለ አስተዳደር ተደምስሶ ፍጹም  አሐዳዊ በሆነው የፋሽስት ወያኔና የናዚ ኦነግ የአፓርታድ ስርዓት ተተክቶ ወደ አረመኔያዊ አገዛዝ መውረድ አልነበረበትም።
ሆኖም ግን በመንግሥትነት የተሰየሙት ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ የታገሉት  ኢትዮጵያን ወግተው ኦሮምያና ታላቋ ትግራይ የሚባሉ በጎሳ አጥር ተከልለው የሚተራመሱ  የአካባቢ አገሮች ለመፍጠር  በመሆኑ የተስፋ ምድራቸውን እውን እስኪያደርጉ ድረስ   ድረስ ቀን ጥሏቸው ያገኙትን የመንበረ መንግሥት ስልጣን ተጠቅመው ሌላውን ሀብትና መሬት  እየዘረፉ  ለመመስረት የሚታገሉትን አገር ለማበልጸግ  የሚያስችላቸውን የአፓርታይድ ስርዓት ዘረጉ። ሕገ መንግሥት የሚሉትን የቅሚያና የግድያ ደንብ  የተፈጠረው ይህንን የጋራ የአፓርታይድ ዓለም ሕጋዊ  ለማድረግ ነው።
ወደ ትክክለኛ ሕዝባዊ አስተዳደር የምታመራ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸውና የሚገባቸው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ክፍሎች  ያልተደራደሩበትን ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ  ብቻ የፌድራል ስርዓት የሚል የዳቦ ስም ሰጥተው ያዋቀሩትን   የአፓርታይድ አደረጃጀት  አፍርሳ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለ ገደብ ተደራድሮበት የሚመሰረት ያልተማከለ አስተዳደር ወይንም የፌድራል መዘርጋት ይኖርባታል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ኢትዮጵያን በአፓርታይድ ለመመተር ጥቅም ላይ የዋለው  የፋሽስት ወያኔና የናዚ ኦነግ  የግድያና፣ የቅሚያና የአፓርታይድ ደንብ መሻሻል ሳይሆን  ተቀዶ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ መጣል ይኖርበታል። በመሳሪያ ኃይል ሥልጣን የያዙት ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ በመንግሥትነት ተሰይመው ፍላጎታቸውን ያለ ገደብ ለማስፈጸም  ያዘጋጁትን  የአፓርታይድ ደንብ በማሻሻል ሁሉም ተደራድሮበት የሚመሰረት ያልተማከለ አስተዳደር ወይንም  የፌድራል ስርዓት መዘርጋት አይቻልም።
Filed in: Amharic