>

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ችግሩ ሥር እንዳይሰድ፤ ይደምሩ አለያም ይተርትሩ (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)


ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ችግሩ ሥር እንዳይሰድ፤ ይደምሩ አለያም ይተርትሩ

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

 
             ለኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥት ምሥረታ ምርጫ ተቃርቦለታል፤በሌላ በኩል ደግሞ ለሃያ ሰባት ዓመታት የቀበሯቸውን የማሕበራዊ ቀውስ ፈንጂዎች ሕውሃት እንዲፈነዱ በማድረግ የየክልሉን ሕዝብ በረቱ ውስጥ እንደገባ ተኩላ በማመስ በጦርነት ማፈናቀሉን ተያይዞታል።ይሁንና አሁን ስለሕዝባዊ-ምርጫው ለማንሳት አይደለም፤እሱን በጊዜው ሲወሰን እንደርስበታለን።በአሁኑ ጊዜ ግን እራሱ የዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሕሊና ዳኝነት ምርጫ በመርጫቸው  ላይ በግልፅ አቋማቸው መታወቅ ይኖርበታል።ምክንያቱም ስለመንግሥት ምርጫ ከማሰባችን በፊት እርግጠኞች መሆን ያለብን አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተጨባጭ ሁኔታ በእርግጥም ሥልጣን በዶ/ር ዐቢይ አህመድ እጅ ስላለ ብቻ ነው።
         እሳቸውም ደግሞ በግልፅነት፣በትህትና፣በጨዋነት እና በአገር ፍቅር ወዳድነት ሰብዓዊነትን ተላብሰው የመደመር ቀመራቸውን በፍቅር ሚዛን ላይ አስቀምጠው የምሥራች እንደአሉን፤የኢትዮጵያ ሕዝብም በአንድ ድምፅ “ምሥር ይብሉ!”ብሎ እየመረቃቸው ይንገሡ ብለን አነገሥናቸው።እሳቸውም እንዲህም አሉን ፍቅርን እየሰበኩ”በመደመር ቀመር ሁላችንም ተሰብስበን በእኩልነት ርሃብን፣ ችግርንና መከራን ከአገራችን ለማስወገድ ይቅርታችንን እየሰጠን፣አንዱ ከሌላው ስህተት እየተማረ በትብብር ወደፊት እንራመዳለን፤ባለፉት አሰቃቂ ድርጊቶች ጨው ሆነን እንዳንቀርም ወደኋላ ሳንመለከት ወደፊት እንጓዝ”አሉን።እኛም እምቢ አላልንም፤ምክንያቱም ትናንት ያለአግባብ አይናችን እያየ የገደሏቸውን ዘመዶቻችንን፣ወገኖቻችንን፣ ልጆቻችንን እና አባትና እናቶቻችንን ለመርሳት”በፍቅር ካልሆነ፣እንዴት እንዲህ በቀላሉ ያውም ልብ ውስጥ ሆኖ ሕሊናን ማሸነፍ ይቻላል?”እያልንም፣ያ የደም ዕምባ ልባችን ውስጥ እያለ ጅማሮዋቸውን ልናየው፣በተስፋችን ውስጥ ተደመርንላቸው።
         ምክንያቱም የመደመር ቀመራቸውን በዝርዝር ባይነገረንም እንኳ፣እንደሰብዓዊነት አመለካከቴም እኔም ሆንኩ የማውቃቸው ጓደኞቼ በየግል ውሳኔአችን እንድንቀበላቸው የሚያስችሉ ዕውነታዎችን በማየታችን ወሰንን።ዳሩግን እኔ በሕሊና ዳኝነቴ አንድ የደረስኩበት ትልቅ መሰናክል ስለታየኝ በግዴታ የዶ/ር ዐቢይ አህመድን የግል ምርጫቸውን ምርጫ ማረጋገጥ ለእኔ የድጋፍ ልሳን ዕውነቱን ማወቅ አስፈለገኝ። ምን ምን ሠሩ ብዬ ሳይሆን እኔ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ምን መ-ጠ-የ-ቅ አለባቸው ወይም ምን ማድረግ ነበረባቸው ብዬ ያሳሰብኳቸውን፤በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎችም የተነሱ ጉዳዮች ነበሩ።ከነዚህም መካከል “እኔ አሻግራችኋለው”ብለው እንደቀልድ የነገሩን በ፳፻-፳፩፻ኛው ክፍለ ዘመን የተከሰተውን”ለሁለት ደቂቃ ብቻ ነው”እንደሚሉት ዓይነት መልሳቸው አሻሚ ሆኖብናል።አንዳንዶቹ እንደሚገምቱት ለውጥ ይሁን ወይም ሽግግር ገና የተረዳቸው ነገር የለም።እኛም የምንፈልጋቸውን ሁሉ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጠረጴዛችን ላይ ስላስቀመጡልን ባገኘናቸው ተስፋዎች መሠረት፣ከዚያ ሰው በላ የፋሺሽት-ወያኔ ባንዳ ቡድን ለመላቀቅ አማራጮችን አልፈለግንም።ስለዚህም ወደ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ቀመር፣ስሌት፣ትንተናና ቃሎች ተመልሼ የ”መ+ደ+መ+ር ቀመሩ”ን መረመርኩት፤አብረን እንመልከተው።
          በመጀመሪያ የመደምርን ሥሌት በሁለት ዘመናት ከፈልኩት የ፲፱፻-፳፻ ክፍለ ዘመንና የ፳፻-፳፩፻ ብዬ፤ለምን መደመር በ፲፱፻-፳፻ ክፍለ ዘመን በ፳፻-፳፩፻ ክፍለ ዘመን በመሠረታዊ ጉድዮች ላይ ሳይሆን በሥልጣኔ ዕውቀት የተገነቡበት የተለየዩ በመሆናቸው ነው።መደመር በሒሳብ ትምህርት ውስጥ  ከአራቱ መደቦች አንዱ እና ቀላሉ ሲሆን የትምህርት ደረጃ ጣሪያ እስከስምንተኛ ድረስ በነበረበት ዘመን በዕለት ተዕለት የምንኖረው ነው።በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ከዩኒቨርስቲም በላይ አልፎ የስብስብ(ሴትት ትሂዎሪ)ቀመር እስከተዘረጋበት ድረስ የመደመር ዋጋው ከማባዛትና ከማካፈል ባልተናነሰበት ስሌት እጅግ አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን ቢያንስ በትምህርት ገበታ ላይ የነበርን ሁሉ በደምብ እንገነዘባለን።ለዚሁም መገለጫው አብዛኛው ተማሪ ከሚጠላው  የትምህርት ዓይነት ሒሳብ የመጀመሪያው ነው፤በተለይም በአሁኑ ጊዜ በ፳፻-፳፩፻ኛው ክፍለ ዘመን ሁለት እና ሦስት አራት(2+3≠5)እንደሆነ በቀመር ተቀባይነት ባገኘበት ዘመን ትምህርቱን ውስብስብ ያደርገዋል።
            እናም ዶር ዐቢይ አህመድ ውስብስቡን አይሹትም ብል እንኳ የመደመር ቀመሩ በፖለቲካ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ውስብስብ ያደርገዋል እላለሁ።ምክንያቱም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስሌቱን የሚያገኙበት መመሪያ(ፎርሙላ)በትክክል መታወቅ አለበት፤የ፲፱፻-፳፻ኛው ክፍለ ዘመን መመሪያ (ፎርሙላ) የሒሳብ ስሌት ላይ ብቻ ተመርኩዤ መልስ እሰጣለሁ ብለው   ከተዘጋጁ አራት እና ሦስት ሲደመሩ ሰባት ይሆናል ብሎ ብቻ ያጠቃልላል።ይሄን የድምር ስሌት የሚያስቡ ካሉ የትኛው ዘመን ውስጥ እንዳሉ በትንተናዬ መሠረት መመደብ ይቻላል፤ከዚህ ስሌት ውጭ ወጥተው የሚያስቡ ግን፣ከሳጥኑ ውጭ ናቸውና በ፳፻-፳፩፻ ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ያሉ ስለሆነ የተሻለ ያስባሉ ብዬ አምናለሁ።እኔ የዶክተር ዐቢይ አህመድ የመደመርን ቀመር ያየሁበት መነፅር በዚህ አይነት ስሪት ነው፤ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተቀበሉትም አልተቀበሉትም፤እርግጠኛ ነኝ ይቀበሉታልም፣ምክንያቱም አሁን ያለንበት ፳፻-፳፩፻ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ በመሆናችን ነው።ይሁንና የመደመሩን ቀመር እኔ ስላልኩት ሳይሆን በዕውነትም ያለንበት ዘመናችን ፳፻-፳፩፻ኛው ክፍለ ዘመን ስለሆነ ነው።
            ስለዚህም በእርግጥም በስሌታቸው መሠረት ይህን የተገነዘብን ጥቂቶች እንሆናለን ብዬ አምናለ፤ለምን ተብዬ ብጠየቅ አብዛኛው ሰው እሳቸው የሚሄዱበት መንገድ ክህደቱ አያሌው እንደገለፀው ላስቀምጠውና “እንደዘንድሮው የኢትዮጵያን ፖለቲካ እጅና እግሩን ለመለየት ተቸግሬ አላውቅም፤”ለበት ስሌት ነው:-ምክንያቱም ሲፈልግ የነበረው ቀንዱን ነበር ።እንዴት ሊሆን ይችላል?ብላችሁ ብትጠይቁኝ መልሱ በጣም ቀላል ነው፤ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታትም ሆነ አርባ አራት ዓመታት ፖለቲከኞች ነን ብለውን በፖለቲካ ሥም ሲያታግሉን የነበሩት፣የሰው ሕወትና ደም እያስከሉን የነበረው ሠይጣንን እያማከሩ ስለነበረ ነው።ለዚህም መረጃዬ ክህደት፣ተንኮል፣ሸፍጥ፣ጭካኔ፣ልበ-ቢስነት፣  ፈሪነት፣አጭበርባሪነት  ትዕቢተኛነት፣ወዘተ በሙሉ ከዲያቢሎስ የተረከቡት በመሆናቸው ነው።በዶ/ር ዐቢይ አህመድ የአንድ ዓመት የፖለቲካ ጉዞ ውስጥስ  ምን ምን ነገሮች በእርሳቸው ትዕዛዝ ተፈፀመ?ይቅርታ፣ፍቅር፣አንድነት፣ተስፋ፣ተፈፀ ሲሆኑ፤ሌሎችም የተደረጉ በጎ ተግባሮች ሞልተዋል።
   በሌላ በኩል ግን በኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ እፈነዱ ያሉትና በነዚህም ምክንያት የሚፈናቀሉት፣የሚገደሉትና የሚጨፈጨት የዛሬ ሃያ ሰባት ዓመታት በፋሺሽት-ወያኔ ባንዳዎች የተቀበሩ የማህበራዊ ቅራኔ ፈንጂዎች ናቸው።እነዚያም የእነክህደቱ አያሌው የትግል ጓዶች:-በተንኮል የቋጠሯቸው ችግሮች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል፤ዳሩግን ሓቁን ደብቀው ምንም እንዳልተሰራና ወዴት እንደምንጓዝ የማያውቅ መሪ እንደሆነ:- ዶ/ር አቢይ አህመድን በየጊዜው በመተቸት አንዴ ትግራይ ውስጥ “ቁርበት አንጥፉልኝ” ሲል ሌላ ጊዜ “አዲስ አበባ መጠይቅ አድርጉልኝ” እያለ እንደሚጠይቅ ሰንሰማ:- ይገርቸው   ብሎ “ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋራ ይዋጣልን” ማለቱን ሰምተን ጉድ!!! አልን፤የሚያሳዝነው ደግሞ አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው የቅንጅት የማፍረስ ቁስል እየነካካ ያሳምመናል።የቅንጅትን ማንሳት ያስፈለገበት ምክንያት ዛሬም የተጀመረውን ሽግግር ለማደናቀፍ እንዴት ወደመቀሌ ሳይቀር እየሄደ እንደሚቅነዘነዝ ለማስገንዘብ ነው።
     እናም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እኔ በግሌ አምንዎታለሁ፤በይመስላል ልጠላዎት አልወድም።ዳሩግን አንዳንድ ዕውነት ያልሆኑና፤የነዚህም ውሸቶች ባለቤቶች እርስዎ ነዎት ብዬ ባላምንም  ዕውነትም የሚመስሉ ተግባሮች ግን ይታያሉ።ለውሸታቸው ማስተባበያ ደግሞ “እኛ ኢሃድጎች”የሚለው ምህፃረ-ቃል ከልሳንዎ አለመጥፋቱን በማስረጃነት ሲናገሩ ማስመሰል ሳይሆን ብርቱ አጠያያቂ አቋም እንዳለዎት ያሳያል።ስለዚህም ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምን መፈናቀልን፣መገዳደልን፣ማገዳደልን የሕውሃት ካድሬዎች ከቀበሌ ጀምሮ እንደሚያስፈፅሙት ሕሊናችን እያወቀ”የመ+ደ+መ+ር ሥልጠና ይግቡ”ስንልዎት ማስወሰን ከበደዎት?እኔ ከፋሺሽት-ወያኔ ጋር ልዩ ጥላቻ የለኝም፤ዳሩ ግን እያንዳንዷን የሠይጣናዊ ጥፋት ሳስታውስ እና የፈፀሟቸው ወንጀሎች ከዘረፉት ቢሊዮን ዶላር በላይ ሕሊናዬን ጎድቶታልና ነው።እርስዎም ለቀልባሾች መንገድ እንዳይሰጥ   ሕሊና  ምርጫዎ ውስጥ ሆነው ሥር እንዳይሰድ ችግሩ፤ௐይ፣ይ+ደ+ም+ሩ=አሊያም፣ይௐተௐርௐትௐሩ።
 
 
                               ኢትዮጵያ በነፃነቷ ለዘላለም ትኑር።  
Filed in: Amharic