>

የማለዳ ወግ… የመከራ ደወል በጋዛ ! ለፍልስጥኤም ጋዛ ጸልዩ …[ነብዩ ሲራክ]

gaza-sert-israelባሳለፍናቸው ሳምንታት የሶስት እስራኤል ታዳጊዎች መጥፋትና ከቀናት በኋላ ተገድሎ ተገኘ። ይህም እስራኤላውያንን አስቆጥቶ በአንድ ታዳጊ ፍልስጥኤማዊ ላይ የበቀል እርምጃ አስወሰደ ። ሟች እንጅ ገዳይ አይታወቅም ተባለ። ውጥረቱ ማየል መክረር ያዘ … የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ተፈጸመብን ያሉትን በደል ለመበቀል በአጸፋው በተወንጫፊ ሮኬት ሚሳኤል የእስራኤን መዲና ሳይቀር ማጥቃት ያዙ። የኢላማ ቴል አቢብን፣ እየሩሳሌምን ወደ የተለያዩ ከተሞችን ዘልቆ የደረሰው ጥቃት ድንጋጤን ፈጠረ። ጠቅላይ ሚነኒስትር ናታንያሁ ተበሳጩ ፣ ተሶረፉ! እስራኤል አጸፋ ትወስዳለች ብለው በተናገሩ ቀጽበት የማጥቃት እርምጃውን አዘዙ!ጥቂቶችን ለማጥቀሰት በጋዛ ፍልስጥኤማውያን ላይ መከራው ደወል ተደወለ!…
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ጋዛን መልሰው ለማጥቃት የክተት አዋጅ ጠሩ ። ሰኞ በአጸፋ የአየር ጥቃት እርምጃም ተጀመረ። ማክሰኞ ሮብ ቀጠለ …በርካታ የጋዛ ግፉአን ንጹሃን ዜጎች ህይወት መቀጠፍ ጀመረ ከስምንት አመት በፊት ጋዛን ካደቀቃትና በሽዊች የሚቆጠሩ ዜጎች የተቀጠፉበት ወረራ በኋላ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ የቀለ ጥቃት ከ500 በላይ በእስራኤል የተጠኑ የፍልስጥኤም ሚሊሽያ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ተነግሯል። ባሳለፍነው ሰኞ በተጀመረው የአየር ድብደባ አቅመ ደካማ ህጻናት ሴቶችና አዛውንትንቶችን ጨምሮ 75 ፍልጥኤማውያን በጥቃቱ መገደላቸውና 500 ያህል ንጹሃን በጸና መቁሰላች እየተሰማ ነው ።
ከጋዛ በፍልስጥኤም ሚሊሽያ ታጣቂዎች በኩል የተተኮሱት ከ200 የማያንሱ ተወንጫፊ ሚሳየሎች በሰው ህይወት ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት ባያደርሱም ነዋሪውን ስጋት ውስጥ ጥለውታል። ከተተኮሱት ሚሳየሎች መካከል 40 ያህሉ በእስራኤል ሚሳየል መከላከያ መክሸፋቸውም ተጠቁሟል።
የተቀሰቀሰውን ሁከት ተከትሎ የአለም መራሔ መንግስታት ከመግለጫ ያለፈ ስራ ሲሰሩ አልታየም። የንጹሃንና የግፉአን ፍልስጥም ተራ ዜጎች ደም ሲፈስ መፍትሔ ማምጣት ያልቻለው የተባበሩት መንግስታት ጸሃፊ ባንኪሙን ሁከቱን እና ድብደባውን ከኮነኑበት መግለጫና የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አልፈው የፈየዱትና የሚፈይዱት አለ አልልም ! የማያልቅበት ስብሰባ መፍትሄ ላይሆን ተጠርቷል። የውግዘት መግለጫ ብቻውን መፍትሄ ሆኖ ነፍስን አይታደግ ነገር ንጹሃን በጠራራ ጸሃይ ግፍ እየተፈጸመባቸው አለም ዝም ያለ ይመስላል !
ቀንደኛ የተባሉትን የሃማስ አላቅሳ ሚሊሽያ ታጣቂዎችን ለማጥቃት በሚል የጋዛ ፍልስጥኤም ንጹሃን በጥይት አረር እየተቃጠሉ ፣ እየቆሰሉና እየሞቱ ነው። በግፉአኑ ላይ ዛሬም አሳዛኝና ልብ ሰባሪ ግፍ እተፈጸመባቸው ነው ! ይህ ሁሉ እየሆነ አለም ዛሬም ይህን የለየለት የንጹሃን ደም መፈረሰስ ለማስቆም የተጋ አይመስልም።
ብቻ … ለጋዛ ጸልዩ
ነቢዩ ሲራክ

Filed in: Amharic