>

ቀይ መስቀል በቀይ ስህተት!!! (የሺሀሳብ አበራ)

ቀይ መስቀል በቀይ ስህተት!!!
የሺሀሳብ አበራ
ሰኔ 30 ቀን 1983 ዓም በታምራት ላይኔ የሚመራ የአማራ የሽማግሌ ቡድን አስመራ ሂዶ በአማራ ህዝብ ስም ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ደርግ የአማራ መንግስት ነው ብሎ ተቀበለ፡፡
በ1990 ዓም ክልሎች ዘመናዊ ሆስፒታል ያስፈልጋቸዋል ተብሎ በከፍተኛ በጀት አይደር እና ሀዋሳ ሆስፒታሎች አቅማቸው ተሻሻለ፡፡ ባህርዳር ፈለገህይዎት ሆስፒታል እንዲሻሻል በጀት
ተመድቦ፣ ኢንጅነሩ ሁሉ መጥቶ ወዲያው አቶ አዲሱ ለገሰ ሆስፒታል አያስፈልግም፡፡ በጀቱ ለኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ይዋል አለ፡፡ ለኢትዮጲያ ሲል ሞኝ የሆኑ ሽማግሌዎችም ” ሆስፒታል አንፈልግም፡፡ሀገራችን ለማዳን ለኢትዮጵያ ይሰጥ አሉ” ::
የወቅቱ የጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አሰፋ ይባሉ ነበር፡፡”ለምን እኛ ብቻ በጀታችን እንሰጣለን?” ብለው ሲከራከሩ ጊዜ “መድሃኒት ሽጠሃል” ተብለው ታሰሩ፡፡
ፈለገ ህይዎት ሆስፒታልም ቀዳማዊ ንጉስ
ሃይለስላሴ ከሩሲያ እና ከጀርመን መንግስታት ጋር በ1950 ዎቹ እንዳሰሩት ቁሞ ቀረ፡፡
….
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ብዙው ወታደር አማራ ነበር፡፡ ግን አማራ የሆኑት እነ መቶ አለቃ ቀሬ ደጉ አይነቶች ምሽግ እንደሰበሩ ታሰሩ፡፡ ሻዕቢያም ትህነግም እኩል አጠፏቸው፡፡
አማራ በትክክል የፖለቲካውን ሂደት በሚረዱ ሰዎች
ስላልተወከለ እስካሁን ሶስት ሪፈራል ሆስፒታሎች ብቻ አሉት (ደሴ፣ጎንደር፣ባህርዳር)
አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ከፍተኛ ለ 3 ሚሊየን ህዝብ
ያገለግላል፡፡ የአማራ ህዝብ ቁጥር አዴፓ በተቀበለው በ 1999 ቆጠራ መሰረት 21 ሚሊየን ነው፡፡ (2.4 ሚሊየኑ የአማራ ህዝብ ጠፋ ተብሎ በ2001 እንደገና ታክሏል፡፡)
….
እና በዝቅተኛው እና ፉፁም ተቀባይነት በሌለው የአማራ ህዝብ 21 ሚሊየን ነው ብንል እንኳ 11 ሚሊየኑ ህዝብ ሪፈራል ሆስፒታል የለውም፡፡
147 ቀበሌዎች የነፍስ አድን የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሉትም፡፡22 ወረዳ የጤና ኤክቴሽን ሰራተኛ የለውም እንደማለት ነው፡፡
856 ጤና ጣቢያ ክልሉ ቢኖረውም አንዱም ጤና ጣቢያ ደረጃውን አያሟላም፡፡ በክልሉ አንደኛ ሆኖ የተሸለመው የደምበጫ ጤና ጣቢያ 39 አይነት ምርመራዎችን ማድረግ ሲገባው 21 ብቻ ያደርጋል፡፡ሌሎቹ 39 አይነት የምርመራ አይነቶች እንዲያደርጉ ቢጠበቅም፣ሁሉም ከ21 በታች ናቸው፡፡
….
አምቡላስም ሌሎች ክልሎች በ 30 እስከ 50 ደቂቃ ሆስፒታል እየደረሱ የአማራ ከሁለት ሰዓት በላይ ነው፡፡ ሆስፒታልም፣አምቡላ ንስም፣ መንገድም የለም፡፡፡
….
ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ክልሉን የሚመራው አዴፓ ነው፡፡ የጤና ቢሮ መሪዎች ጤና ፖለቲካ አይደለም፡፡ማህበራዊ ጉዳይ ነው በማለት የፌደራል መንግስቱ ራርቶ እና ቸር ሆኖ እንዲሰጣቸው ይጠብቃሉ፡፡
….
አይጠይቁም፡፡አይከራከሩም፡፡ ጤና የሰባዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ የጤና ሰባዊ መብትን እንኳ የሚያስከብር መሪ ያጣ ህዝብ ነው፡፡
በ 1990 ” ሆስፒታል ይገንባ!” ያለው አቶ አሰፋ ትምክህተኛ ተብሎ ታስሯል፡፡ትምክህተኛ ያልሆኑ መሪዎች በፌዴራል መንግስት ሃብት እንዲህ ሲከፋፈል ጨዋ ለመባል ዝም ብለዋል፡፡
….
በዚህ የአምቡላንስ ክፍፍል ኦዴፓ አይታማም፡፡ ጀግኗል፡፡ የአዴፓ መዛል ብቻ ነው ስህተቱ፡፡ የባለፈው 27 ዓመትም ትህነግ የተለየ ጀግና ሆኖ ሳይሆን ብአዴን የተለየ ሰነፍ መሆኑ ነው
ችግሩን ያባባሰው፡፡
ቀይ መስቀል አምናም ሆነ ዘንድሮ አሰጣጡ ተመሳሳይ ነው፡፡ ቢሆንም ግን፣የቀይመስቀል ስህተት አይደለም፡፡
ብቸኛ ስህተቱ በጤናው ዘርፉ የተወከሉ የአዴፓ ሰዎች ነው፡፡
ፍትሃዊነት በአሸናፊነት የሚመጣ የድፍረት ፍሬ ነው፡፡ዓለምም የአሸናፊዎች መኖሪያ ናት፡፡ የማባባል እና የመልመጥመጥ
ፖለቲካ በየትኛውም ዓለም አያሸንፍም፡፡
Filed in: Amharic