>

የመንግሥቱ ኃ/ማ የመጨረሻዋ ጉብኝት!!! (ሻለቃ ላቀው መንግስቴ)

የመንግሥቱ ኃ/ማ የመጨረሻዋ ጉብኝት!!!
ሻለቃ ላቀው መንግስቴ
ወደ ዚምባብዌ ከማምራታቸው ጥቂት ቀን ቀደም ብሎ ግንቦት ወር 1983 ላይ ነበር፡፡ተሥፋ የጣሉበት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተለያየ ተንኮልና ሤራ ተልእኮውን እንዳይወጣ ተደርጎ የመጨረሻው ጠርዝ ላይ ለሚ ግንባር ላይ የተለያዩ የጦር ክፍሎች አዲሥ የተዋቀረው አየር ወለድ ብርጌድ፣ የልዩ ጥበቃ ብርጌድ ፣ የ605ኛ ኮር የተለያዩ ክፍሎች በለሚ ግንባር በሦሥተኛው አብዮታዊ ሠራዊት አዝማችነት በግንባሩ ላይ የሚሉንን ለመፈፀም በተጠንቀቅ ቆመናል፡፡
አየር ወለድ ብርጌዱ ቀደም ሢል ጦር የተደመሠሠበት ኮላትና አምባት ሸጥ ውሥጥ ትናንሽ የቀበሮ ጉርጓድ ውሥጥ ራሡን ቀብሮ ውሀና ቀለብ በአህያ እየቀረበለት ለሌላ ድምሠሣና ውጤት ለሌለው መሥዋእትነት ተዘጋጅቶ ለሊትም ቀንም ጎርጓዳው መሬት ውሥጥ ቀና ሢል ዳመናና ጠንከር ያለውን ፀሐይ ከአጥናፍ እሥከ አጥናፍ ብርሀኑዋን የረጨችውን ፀሀይ ሙቀትና ንዳድ የሚቀበሉ የሐገር ልጆች ፍሬ ባጣው ትግላቸው አየተቆጬ የእለቱን ትርኢት ይጠባበቃሉ፡፡ ከጠዋቱ 10.30 ላይ ቁጥር 1ወደ ግንባሩ እየመጡ መሆኑን ከሬዲዮ ክፍል ደርሦን ልንቀበል ወደከተማ ጠጋ ብለን በጀነራል ረጋሣ ጂማ መሪነት ተሠባሠብን፡፡ሊቀመንበሩ በተሽከርካሪ ይመጣሉ ብለን ሸብ ረብ ሥንል ከሠማይ አድማሥ የሂሊኮፕተር ድምፅ እያሥተጋባ እኛን አልፈውን የመጨረሻው ጠርዝ ላይ አርፈው ብቻቸውን ከጥቂት አጃቢዎች ጋር ይጠብቁን ገቡ፡፡የያዝናቸውን ተሽከርካሪዎች በፍጥነት እያሽከረከርን ጀነራል ረጋሣን ተከትለን አየር ወለድ ከታች ኮላሽና አምባትን የሞተ መሬት ውሥጥ የሠፈረውን ሀይል ሊያዩ የሚችሉበት ቦታ ቆመው ጠበቁን፡፡እንደደረሥን ጀነራል ረጋሣን ጌታዬ ጦሩን የት ነው ያሠፈሩት የሚል ጥያቄ በአክብሮት ጀነራል ረጋሣን ጠየቁ፡፡እሣቸውም የጦሩን አቀማመጥ ከገለፁ በሁዋላ በአክብሮት ለጀነራል ረጋሣ ጌታዬ እኔ ከርሦ በላይ የተለየ እውቀት የለኝም፡ወደ አየር ወለዱ ይዞታ እያመለከቱ አዚህ የሞተ መሬት ውሥጥ ጦር አሥቀምጣችሁ እርዳታ እንኳን እንዳይደርሥለት ሆኖ ተደምሥሧል፡፡እናንተ በምትፈጥሩት ወታደራዊ ሥህተት የበርካታ ድሀ ወላጆችን ልጆች በየሜዳው ያለአግባብ ህይወታቸው እንዲቀጠፍ ምክንያት ሆነናል፡፡እዚህ ገደል ውሥጥ የምናወጣው ነዳጅ አለ፡ወይሥ ማእድን፡፡ለማን ጦሩን በአህያ የውጊያ ቀለብ እያቀረብን ከምናሠቃየው ወደ እዚህ አውጥተንው ትኩሥ ምግብ እያቀረብንለት ወታደራዊ ልምምድ እያደረገ አያርፍም፡፡ጠላት በዚህ ገደላ ገደል ውሥጥ አልፎ ይሄንን አካባቢ ይቆጣጠራል ብለው የሚያሥቡ ከሆነ ሥህተት ነው ዛሬውኑ ይሄ ጦር ወደ ለሚ ይሣቡት ከሥህተታችን ያለመማራችን አሣዛኝ ነው ለማንኛውም ደብረብርሐን በሥፋት እንነጋገርበታለን ብለው ሁላችንን ሠላም ብለው በመጡበት አኳሁዋን ጀነራሉን ይዘው ወደ ደብረብርሀን አመሩ፡፡ትእዛዛቸውም ተግባራዊ ሆነ፡፡ሠውየው ሣይታሠብ በየጦር ግንባሩ ድንገታዊ ጉብኝት ማድረጋቸውና ወሣኝ ውሣኔ መሥጠታቸው የተለመደ ነበረ፡፡ከፍተኛ ጀነራሎችን አክብረው የሚያነጋግሩ ሢሆን አሣማኝ ሀሣቦችንም ይቀበላሉ ከዚች ቀን በሁዋላ ብላቴ ያለውን ከዩኒበቨርሥቲ የዘመቱትን ሠልጣኞች ለመጎብኘት እንደወጡ የቀሩበት ጉዞ ካልሆነ በቀር የለሚው የመጨረሻ ይመሥለኛል፡…..ጠብቁኝ፡፡
Filed in: Amharic