>
5:13 pm - Monday April 19, 6934

"...በፍጹም መሞትን አልፈራም፤ በመሞትህ ችግር አይፈጠርም ካላችሁኝ ግን ነገውኑ ወደ ወለጋ እሄዳለሁ... "  (ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ)

…በፍጹም መሞትን አልፈራም፤ በመሞትህ ችግር አይፈጠርም ካላችሁኝ ግን ነገውኑ ወደ ወለጋ እሄዳለሁ…
 ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ
ናትናኤል መኮንን
የትግራይ ነፃ አውጭ ድርጅት ዶክተር አቢይን በ ኦሮሞ ቅጥረኞች እጅ በማስገደል የኦሮሞን ሕዝብ እርስ በርሱ ደም ለማቃባት በዓብዮት አደባባይ ያደረገችው ሙከራ ከሽፎባታል። ሌሎች ቅጥረኞችን በሌላ አካባቢ አሰማርታ ለማስገደል ያላትን እቅድ ግን አላቆመችም። ዶክተር ዓቢይ አሕመድ ለምን ወደ ወለጋ ኣልሄዱም ተብለው ሲጠየቁ የሰጡት ምላሽ ይህን ያገናዘበ ይመስላል።
 “ጂማ ነው ተወልጄ ያደኩት። ከ17 ዓመቴ ጀምሮ በትግሉ ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ የቆየውት ወለጋ አካባቢ ነበር ።ታድያ ውሃ ስጠማኝ ወተት ነው የሚሰጠኝ የወለጋ ህዝብ ። የወለጋን ህዝብ ከልቤ እወደዋለሁ። እነሱም ከልባቸው ይወዱኛል ። ወለጋ የልሄኩበት ምክንያት የተደራጁ ነብሰ ገዳዮች እኔንና ለማን ለመግደል በሚገባ መዘጋጀተቸውን በበቂ መረጃና መስረጃ በማረጋገጡ ነው ። ይህ መረጃ እያለ ወለጋ በመሄድ ብሞት በመጀመርያ ደረጃ አላስፈላጊ መሰዋዕትነት ነው። ስቀጥል ወለጋ ሂጄ ብሞት ለኦሮሞ አንድነት ከበድ ችግር ይፈጥራል ። ወለጋና ጅማ መካከል፡ ወለጋና ባሌ መካከል ፡ ወለጋና ሸዋ መካከል በአንድነቱ ለይ ክፍፍልና ጥርጣሬ ይፈጥራል። ሌላ ክልል ላይ ብሞት የኦሮሞ አንድነት ላይ ምንም አይነት ችግር አይፈጠርም ፡ በአንድነት ትግሉን ይቀጥለሉ ። በፍጹም መሞትን አልፈራም ፡ የእኔን መሞት በኦሮሞ ህዝብ አንድነት ላይ ምንም አይነት ችግር አይፈጠርም ካላቹኝ ግን ነገውኑ እሄዳለሁ “
ራስ ስሁል ሚካኤሎች ‹‹ ቀታሊ ንጉሶች›› ዛሬም አሉ!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክረሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አቢይ አህመድ ‹‹ ወለጋን ለምን አትጎበኝም ? ›› ተብሎ ሲጠየቅ ተናገረዉ ተብሎ የተሰራጨዉን ዜና እንደ ቀላልና ቀልድ  መታየት ያለበት አይመስለኝም፡፡ የዓለምንና የአለም መሪዎችን ታሪክ መለስ ብሎ ማየት ትልቅ ትምህርት ይሆነናል፡፡  ጁሊየስ ሲዛር ፣ አብርሀም ሊንከን  ፣ ሀኒባል ፣ ጄንጂስ ካሃን፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁሉም ስለ ራሳቸዉ ህይወት አስጠንቅቀዉ ነበር፡፡ ፡ሁሉም  እንዳስጠነቀቁት አልቀረም ወድያዉኑ “ከሸክላነት ወደገልነት” ተሸጋገሩ፡፡  ሸክላ ማለቴ ያዉ የሰዉ ልጅን ፈጣሪ ከአፈር ስለሰራዉ ለመጠቆም ያክል ነዉ፡፡
..
በዚህ ዘመን ብዙ ራስ ስሁል ሚካኤሎች መኖራቸዉን መዘንጋት የለብንም ፡፡በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ከአደዋ ወደ ጎንደር የመጣ ራስ ሚካኤል ስሁል የሚባል ሰዉ ነበር ፡፡ ራስ ሚካኤል ስሁል ስፔሻላይዝ ያደረገዉ ንጉሶችን በመግደል ነበር ፡፡ ሚካኤል ስሁል ንጉስ ኢዮአስ በሻሽ አሳንቆ ሲገድለዉ ሌላዉን ንጉስ ደሞ በመርዝ አስገድሎታል፡፡ በዘመኑ የነበረዉ  የኢትዮጵያ ህዝብ የሰዉየዉን ተግባር በመመልከት ‹‹ ቀታሊ ንጉስ ›› የሚል ቅጽል ስም አወጣለት፡፡
..
 ዛሬም ራስ ሚካኤል ስሁሎች አሉ፡፡  በሰሜን በኩል ከተከዜ ማዶ በጥንቀቄ የሚያደባ ጌታቸዉ አሰፋ የሚመራዉ ኦሊጋርኪ ፕሮፌሽናል   ነፍሰ ገዳይ አለ፤፤ በምእራብ ኦሮሚያም ኦነግ የሚባል ነፍሰ ገዳይ አለ፡፡ ሁለቱም ግሩፖች  የጋራ አጀንዳና አላማ አላቸዉ፡፡ ዶ/ር አቢይንም ሆነ ለማ መገርስሳ ፣ ደመቀ መኮንንም ሆነ ገዱን  ቢያጋጥማቸዉ የሞት ዋራንቱን ከመቁረጥ አይመለሱም ፤፤ ስለዚህ በነገሩ ከመቀለድ በጽሞና በመመልከትና እርምጃ  በመዉሰድ በጊዜ መጠንቀቅ ደግ  ነው!!
Filed in: Amharic