>

የኦነግ ታጣቂዎች ነገር!!! (ከድር እንድርያስ)

የኦነግ ታጣቂዎች ነገር!!!
ከድር እንድርያስ
#ቤንሻንጉል – በግልፅ የሚታወቀው የካማሽ ዞን አመራሮችን መግደላቸውና እሱን ተከትሎ ወደ መቶ ሺህ የሚጠጋ ህዝብ መፈናቅል   ሞት እና ቀውስ መፍጠሩን ብቻ ነው። ነገር ግን ወለጋ እና ቤንሻንጉል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ትንኮሳ እና ግጭት መፍጠር ከጀመሩ ቆይተዋል። የካማሽ ዞን አመራሮችን ከገደሉም በሓላ ወደ ቤንሻንጉል የሚወስደውን መንገድ ዘግተው ብዙ አካባቢ የሚኖረውን ሰው የቁም እስረኛ ካደረጉት ሰነባብተዋል። የሰብዓዊ እርዳታ እንኳን ለማድረስ አይፈቅዱም። ማለፍ አይቻልም። ከምንም ውስጥ የሌሉበትን ዜጎች በምግብ አቅርቦት እጥረት፣ በህክምና ቁሳቁስ እና መሰል ግብዓቶች እጥረት እንዲሰቃይ እያደረጉት ነው።
#ሞያሌ – ሞያሌ ውስጥ ሶማሊና እና ኦሮሞ ይኖራሉ። ከተማዋ ለሁለት የሚከፍላት መንገድ ድንበር ነው ለሶማሊ እና ኦሮሚያ ክልል ( በወያኔ የተቀበረ አጥፍቶ መጥፊያ ቦንብ )። አንድ ከተማ የሁለት ክልሎች ናት ማለት ነው። ታዲያ ይሄው ኦነግ ነን የሚሉ ታጣቂዎች ትንኮሳ ከጀመሩ ቆይተዋል። የኦሮሚያ ክልል ወሰን እያለፉ የሶማሊ ክልል ወሰን ውስጥ እየዘለቁ የኦነግን ባንዲራ በመስቀል የኛ ግዛት ነው የሚል ትንኮሳ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ሰማኑን ደግሞ ከሀገር ድንበር አልፈው ኬንያ ውስጥ ከሚገኙ አጎራባች ጎሳዎች ጋር ትንኮሳ ላይ ነበሩ። እሱን ተከትሎ ግጭት ተፈጠር። በግጭቱም በጣም ዘግናኝ የሆኑ ለወሬም ለማየትም የሚቀፉ ነገሮችን ለማየት በቃን ። ሞያሌ ላይ ብቻ ሳይሆን በብዙ የኦሮሚያ እና ሶማሊያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ችግሮች አሉ። የኦነግ ነን ባዮች ሚና የጎላ ነው።
#ደቡብ_ብሄረሰቦች – ከኦሮሚያ ክልል አጎራባች ከሆኑት የደቡብ የተለያዩ ብሄረሰቦችም ጋር ተመሳሳይ ትንኮሳ ፈፅመዋል እነዚሁ የታጠቁ ኦነግ ነን የሚሉት። የተገደሉ እና የተፈናቀሉ ዜጎች ብዙ ናቸው። አሁንም ምክኒያቱ የኛ መሬት ነው በሚል ነው።
ደቡብ ክልል ውስጥ ትልቅ ቀውስ ለመፍጠር በሲዳማ በኩል መጥተዋል። ደቡብ ክልል ውስጥ ህዝቡ ወደፈለገው አይነት አስተዳደራዊ ወሰን የመቀየር የማስተካከል ሙሉ መብት አለው። ትልቁ ችግር እሱ አይደለም። የሲዳማ ብሄርተኞችን እየተሳሉ ያለበት መንገድ ግን እጅግ አስፈሪ ነው። በጣም ሲበዛ ጨካኝ፣ ስረዓት አልበኛ ፣ ሌሎቹን እንዱጠሉ እየተደረገ በጥላቻ እና ልዩነት ላይ ነው እየተገነባ ያለው። ልክ እንደ አዲስ አበባ ደቡብ ክልል ውስጥ #ሀዋሳ ከተማን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ ያለ እረፍት እየተሰራ ነው። ሀዋሳ ሰዎች በሰቀቀን በጭንቀት የሚኖርባት አሰቃቂ ከተማ ሁናለች #ኢጄቶ በሚባሉ ፅንፈኛ ቡድን።
#በክልሉ_ውስጥ_የሚኖሩ #አማራዎች
በደርግ ዘመን ከወሎ በሰፈራ የሄዱት ወገኖቻችን እየኖሩ ካሉበት ሁኔታ ሞት ይቀላል። በፈለጉበት ሰዓት ታጣቂዎች ሂደው የፈለጉትን ሰው ይገድላሉ፣ ይደበድባሉ፣ ይዘርፋሉ ፣ ያሸብራሉ። እዚህ ላይ የየአካባቢው የቀበሌ ሊቀመንበሮች እና ፀጥታ አስከባሪዎችም ተባባሪዎች ናቸው።
#የኦሮሞ_ፅንፈኞች – የኦሮሞ ፅንፈኛ ብሄርተኞች የጃዋር ቡድን ( Team OMN ) ፣ የዳውድ ኢብሳ ኦነግ ቡድን ክልሉ ውስጥም ፣ ከኦሮሚያ ክልል ውጭም በአጠቃላይ ሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን አልፈለጉም። አለመረጋጋቱን ይፈልጉታል። የተፈጠረው ሀገራዊ አንድነት ለመናድ በተቃራኒው ተናበው በጋራ እየሰሩ ነው። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ኦነግ ነኝ እያሉ ትጥቅ ይዘው ለሚያሸብሩት አካላት ከለላ እንደመስጠት እቆጥረዋለሁ። ላለፉት ወራቶች ልዩነቶችን ብቻ በማራገብ የለማ አስተዳደር እና የአብይ መንግስት ጥያቄህን አልመለሱም ተነስ እያሉ #ቄሮን ይወተውታሉ። ልዩ ትኩረት ሰጥተው ለግጭት እያዘጋጇቸው ያሉ ከተሞች ዋነኛዎቹ
#አዲስ_አበባ
#ድሬዳዋ
#ሀረር
ናቸው።
እነዚህ ከተሞች ትልቅ ቀውስ እንደሚያመጡ በማሰብ ነው ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው። እነዚህ ከተሞች ላይ ችግሮች ተፈጥረዋል። የከፋ ችግር እና ቀውስ ደግሞ አይቀሬ ነው ከወዲሁ መላ ካልተባለ።
አማራ ክልል ውስጥም ቀውስ ለመፍጠር ከህወሓት ጋር በአንድ ጎራ ተሰልፈው ህዝቡን ለመከፋፈል እየተሰራ ነው። በዚህም ለግዜው አንድ ቦታ ላይ ቀውስ ለማየት ችለዋል በመዕከላዊ ጎንደር አካባቢ።
ይሄን ሁሉ የሚያደርጉት ለምንድን ነው???
መንግስት ይሄ ሁሉ ሲሆን ዝምታን ብቻ መምረጡ እና መለማመጥን እንደ መፍትሄ መውሰዱ ምን ያህል ዋጋ ያስከፈላል????
የዚህ ሁሉ አላማው የለማ አስተዳደር እና የአብይ መንግስት ተረጋግቶ እንዳይሰራ እና ሀገራዊ አንድነቱን መናድ ነው። በጣም የሚያናድደው እነሱ ከወያኔ ጋር በአንድ ጎራ ተሰልፈው በሚፈጥሩት ቀውስ ተጠያቂ እያደረጉ ያሉት የለማን አስተዳደር እና የአብይን መንግስት ነው።  ሁለት አማራጭ ይዘዋል። በእንዲህ ቀውስ ውስጥ እየተሄደ መረጋጋት ሳይኖር የለማ አስተዳደር ድክመት አድርገው በማሳየት በተጭበረበረ ምርጫ ቶሎ ስልጣን መያዝ እና የመጨረሻ ግባቸውን ማሳካት ነው። ይህ ካልሆነ ለማ ማስተዳደር አልቻለም ብለው በጉልበትም ስልጣን መንጠቅ ነው። በእነሱ ቤት እኮ ሰላማዊ ትግል እያደረጉ ነው ኦሮሚያን ለመገንጠል።
የክልሉ መንግስት እና የፌደራል መንግስት ኮፍጠን ብሎ ምርር ብሎ በጣም ሳይዘገይ እርምጃ ካልወሰደ እና ይሄን የጅል ፓለቲካቸውን ካላስቆማቸው ከባድ ቀውስ ይመጣል እንደ ሀገር።
መፍጠን ያስፈልጋል
ውሳኔ ያስፈልጋል !!!
Filed in: Amharic