>

የሀገራችን የፍትህ ስርአት ከእስር ወደ እስር!?!  (ለገሠ ወ/ሃና)

የሀገራችን የፍትህ ስርአት ከእስር ወደ እስር!?!
ገሠ ወ/ሃና
*  አዝመራው በቀለየተከሰሰበትን ጉዳይ እንኳ ሳያውቅ ሶስት አመት ከስድስት ወር ተፈርዶብሀል ተብሎ ያለ ሀጢአት በእስር እየማቀቀ ይገኛል!
በሀገራችን ኢትዮጵያ ሠማይና ምድር ላይ ለ27 ዓመታት ሰፍኖ የቆየውን ፋሽስታዊ አገዛዝ ከስሩ ገርስሶ ለመጣል በተደረገው ብርቱ ትግል ብዙ ታጋዮች ተፈጥረዋል ከነዚህ ብርቱ ታጋዮች መካከል አንዱ አዝመራው በቀለ ነው ጭቆናን ለ27 ዓመታት በቁርጠኝነት ታግሏል ከዚህ ቆራጥ የነፃነት ታጋይ ጋር የሞት ጥላ በሚያጠላበት ማዕከላዊ /ሳይቤሪያ /አንድ ክፍል ውስጥ ለወራት አብረን ታስረናል ብዙ ግፍ ተፈጽሞብናል በደከምኩ ጊዜ አፅናንቶኛል አፅናንቼዋለሁ አብረን ባሳለፍነው የመከራ ጊዜ በውስጡ ያለውን የነፃነት ጥማት ለትግል ያለውን ቁርጠኝነት አይቻለሁ ።
ማዕከላዊ የሚሰጠውን መከራ የመጀመሪያን ምዕራፍ ጨርሰን ሀሉተኛውን ምዕራፍ ለመጀመር በሽብር ወንጀል እየተከሰስን ወደ ቅሊንጦ ተወስደን በተለያየ ዞን ተበተን አዝመራው በቀለ ሌላ ዞን እኔም ሌላ ዞን ተጥለን ዳግም የምንገናኝበት እድል አላገኘንም ።
አዝመራው ቅሊንጦ ማጎሪያ ቤት ከአንድ አመት በላይ ታስሮ ሁላችንም በተፈታንበት የህዝብ ትግል ከእስር ተፈቶ ወደ ናፈቁት ቤተሰቦቹ ሔዶ ነበር ብዙዎቻችን የነፃነት አየር ስንተነፍስ አዝመራው በቀለ ዳግም ወደ እስር ቤት ተወርዉሯል ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ ያሳደገበት ቤንሻጉል ክልል የክልሉ መንግስት አመራሮች አዝመራው በቀለ ከእስር ቤት ተፈቶ ወደ ቀየው ሲሄድ የተቀበሉት እንኳን ደህና መጣህልን እያሉ እቅፍ አበባ ይዘው ሣይሆን እጁን የሚያስሩበት ካቴ ይዘው ነው ።
እስካሁን ድረስ አዝመራው በቀለ ለምን እንደታሰረ ትክክለኛ ምክንያቱ አይታወቅም አዝመራው ከሳሹን ባላወቀበት ፍርድ ቤት ቀርቦ ባልተከራከረበት ክስ 3 ዓመት ከ6 ወር ተፈርዶብሃል ተብሎ ዳግም ወደ እስር ቤት ተወርውሯል ።
Filed in: Amharic