>
5:13 pm - Monday April 19, 3306

ህወሀቶቹ መረጥነው ያሉትን መሪ ተቀባይነት ለማሳጣት እያሴሩ ነው!!!  (ሂሩት ሀይሉ)

ህወሀቶቹ መረጥነው ያሉትን መሪ ተቀባይነት ለማሳጣት እያሴሩ ነው!!! 
ሂሩት ሀይሉ
 
* ህወሐት እንዴት እና መቼ ስልጣን ከእጁ እንደወጣ ሳያውቀው ስልጣንን ድንገት የለውጥ ሀይሎች እጅ ውስጥ ሆና አያት!  ስሥልጣን ማለት ለእነርሱ መዝረፍ፣ መግደል፣ ማሰርና ማሳደድ ነበር፤ ያ  የለመዱት ዝርፊያና ግድያ ሲቀርባቸው ያክለፈልፋቸው ጀመር  በሀገር ውስጥም በውጭም ማመሡን ማተረማመሱን ስራዬ ብለው ተያያዙት በዚህም አላበቁ በዲፕሎማሲ ጭምብል ማሴሩን ተያይዘውታል አልተሳካም እንጂ…!
ማፊያው ወያኔ እስካሁን የዘረፈውና ያሸሸው ሃብት ሳያንስ.. በዲፕሎማሲ ጭምብል የሃገር ሉአላዊነትና ክብር መዳፈር ጀምሯል
የህወሀቱ ተጠሪ ስዩም መስፍን በዲፕሎማት ጭንብል የቻይና ባለስልጣንን እንዲህ ማለቱ ተነግሯል፡ “….ኢትዮጵያ ባሁኑ ግዜ እየፈረሰች ትገኛለች ፤ ሁከት ፣ ብጥብጥና የእርስ በርስ ግጪት ዉስጥ በመግባቷ አገሪቷ ያላችሁትን ብድር ችላ አትመልስላቹም። ዶ/ር አብይ አገር መምራት ስለማይችል ኢንቨስትመንታችሁ ይዘረፋል ፣ ብድራችሁ አይከፈልም ከኛ ጋር ስሩ….” የሚል አሳፋሪ ተማጽኖ ያቀረበ ሲሆን..
የቻይና መንግስት ደግሞ በበኩሉ:-
“….የኢትዮጵያ መንግስት አሁን በአፍሪካ ካሉት መንግስታት ቀዳሚ እዉቅና ያገኘ መሆኑን እናዉቃለን ፣ የአለም መንግስታትም ለኢትዮጵያ እዉቅና ከመስጠትም ባሻገር የጀመረችዉን አዲስ የፖለቲካ ሥነምህዳር ዘላቂ እንድታደርግ የበኩላቸዉን እየተወጡ ባሉበት ወቅት ቻይና ለብቻ ከናንተ ጋር ግንኙነት አትፈጥርም!” በማለት የቅሌት ካባ አልብሳዋለች። ይሄንኑ መረጃ የቻይና መንግስት ሳይ ውል ሳይ ድር ለዶ/ር አብይ እንዳቀበሉ ከቅርብ ሰዎች መረጃውን ማግኘት ተችሏል።
መቼም የእናንተ ቅሌት ማብቂያ የለው ለመሆኑ “እኛው መርጥነው” ብሎ የመሰናክል ድንጋይ ማስቀመጡ ለምን ይሆን?
ባለፈው የኢሀዴግ ምርጫ ላይ ዶ/ር ደብረ ወ*ብ መሸነፉን ካረጋገጠ በኋላ ምንድን ነበር ያለን? “እኔ እራሴ አትምረጡኝ ብዬ ቅስቀሳ አድርጌ ነው!”   በአለም ላይ የመጀመሪያው  ብቸኛው ተወዳዳሪ ሰው ፣ ለውድድር ቀርቦ አትመርጡኝ የሚል :። ካልፈለክ ለምን ውድድር ውስጥ ገባህ መጀመሪያውኑ?! በራሱ ፍላጎት ዶ/ር አብይ እንዲመረጥ እንዳደረገ ነገረን፣ ታዲያ እራሳችሁ በፍላጎት እንዲመረጥ ያደረጋችሁትን ጠ/ሚ ስራውን እንዳይሰራ ጠልፋችሁ ለመጣል የምትሯሯጡት ለምንድ ነው? በአለም አቀፍ ደረጃ መምራት አይችልም እያላችሁ ድጋፍ ለማሳጣት ጉድጓድ የምትቆፍሩት ለምንድ ነው?!
አወ! እውነታው ሁልግዜ እያጭበረበራችሁና እያስፈራራችሁ ምንም ምርጫና ተወዳዳሪ በሌለበት አሸነፍን ብላችሁ ብቅ ስትሉ ነበር፣ ዘንድሮ ግን አልተሳካም! በኦሮሞና በአማራ መካከል የጠላትነት ግንብ ገንብታችሁ፣ በኦህዴድና በብአዴን መሀከል አለመተማመንን ፈጥራችሁ እድሜ ልክ ከናንተ አልፎ እስከነ ልጅ ልጆቻችሁ ድረስ እየቀጠቀጣችና እየዘረፋችሁ ልትገዙን ፣ልጆቻችሁ ሁሉ “ገና ሞቶ አመት እንገዛችኋለን!” እያሉ ሲፎክሩብን ፣ ቅኝ ገዢነታቸውን በኩራት ሲነግሩን ነበር! ነገር ግን ባልታሰበና ባልተጠበቀ ሁኔታ ታሪክ ተቀየረ!
ከኦህዴድ ውስጥ እና ከብአዴን ውስጥ መናበብ ተጀመረ፣ መተማመን ተጀመረ፣ ለብቻቸው መነጋርና መመካር ጀመሩ፣ የህወሐት ተንኮል ከገባቸው ቆይቷል፣ በተለይ በኦሮሞ ህዝብና በአማራ ህዝብ መሀከል ለማቀራረብ ስራ መስራት ጀመሩ፣ በኦህዴድ በኩል “ጣና ኬኛ” በሚል መርህ 200 የሚሆኑ የኦሮሚያ ወጣቶች የጣናን እምቦጭ ለመንቀል ወደ ባህርዳር አቀኑ! ከእምቦጩም በላይ ትልቅ መልክት ነበረው! በመቀጠል በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራ የልኡካን ቡድን ከታዋቂ የኦሮምኛ ዘፋኝ አርቲስቶች ጋር ወደ ባህርዳር ተጓዘ! ጥሩ ሞቅ ደመቅ ያለ አቀባበል ተደረገላቸው! በህወሐት እሳትና ጭድ የተባሉት ህዝቦች እሳትና ጭድ ሳይሆኑ ክርና መርፌ፣ እንደገመድ የተሳሰሩ መሆናቸውን እና በምንም አይነት መንገድ የማይለያዩ ህዝቦች መሆናቸው ኦቦ ለማ አስረግጠው ተናገሩ! ከህዝቡ ጋር ስለአንድነት ተወያዩ፣ ተመካከሩ!
በህወሐት ቤት ግን አልተወደደም ነበር፣ ሀዘን ላይ ተቀምጠው ነበር! መቼ በዚህ አበቃ?  🙂
በሁለቱ መሀከል የተጀመረው መናበብ እና መተማመን አንደር ግራውንድ ስራውን ሲሰራ ቆይቶ በምርጫው ወቅት ህወሐትን ከጨዋታ ውጭ አደረጉት! ህወሐት እንዴት እና መቼ ስልጣን ከጁ እንደወጣ ሳያውቀው ስልጣን ወደ የለውጥ ሀይሎች እጅ ገባ! መዝረፍና መግደል የለመደው ህወሐት እየቆዬ ባሰበው ቁጥር ያቀዠው ጀመር፣ እውነቱን መቀበል አልፈለገም፣ አሁንም የተለመደውን የአሸባሪነት ባህሪውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፣ አገር እያተራመሰ ነው፣ ህዝብ እርስ በእርስ እያጫረሰ ነው!
በግልፅ አማረኛ ሊያውቁት የሚገባው ጉዳይ ዳግም ወደ ስልጣን መምጣት እንደማይችሉ ነው! ህዝቡ ዘረኛውን፣ ዘራፊውን፣ ግብረ ሰዶማዊውን፣ ወንጀለኛውን እና ፀረ ኢትዮጵያዊውን ህወሐትን ዳግም ማየት አይፈልግም! ለዚህ ደግሞ የሚከፈለው ሁሉ ይከፈላል!
ኖ ሞር!!!
Filed in: Amharic