>

በጠቅላይ ምኒስትሩ መግለጫ ላይ የምለው አለኝ!! (ደረጀ ደስታ)

በጠቅላይ ምኒስትሩ መግለጫ ላይ የምለው አለኝ!!

 

ደረጀ ደስታ

 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል። ከጥቂት ቀናትም በፊት ህገመንግሥቱ ይከበር እሚል ሰልፍም አይተናል። የተከበረውን ህገመንግስት ለማሳየት ሰሞኑን የተለቀቀው አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዶክዩመንተሪም እየታየ ነው፡፡ “ያው እኛኑ ነው” ያሉት ሰዎች ለፖለቲካ ፍጆታ የዋለ በማለት እየተቃወሙት ነው። መቸም እንዲህ ያለ አሰቃቂ በደል ተፈጽሞ ከሆነ ከዚህ በላይ ለፖለቲካ ፍጆታ ሊውል እሚገባው ነገር ምን ይኖራል በሚል የጠቅላይ ሚኒስትሩን መግለጫና የሰሞኑን ሁኔታ እሚቃኝ የግሌን አስተያየት ለማቅረብ ሞክሬያለሁ። ከአብይ መግለጫ “ለአንድ ገጽ ብለን መጽሐፍ የምንቀድ ሞኞች አይደለንም” እምትለዋን ወድጃታለሁ። አገር እዚያም እዚህም እንደ መጽሀፍ ገጾች እየተቀደደች እንዳታልቅ እሚያሰጉ ነገሮች መኖራቸውም እንደ ዜጋ ያሳስበኛል። አገሪቷን ለአንዲት ገጽ ብለን ብቻ ሳይሆን “ስለጥቂት ገጾችም” ብለን ባንሰጋ ደግሞ ሁኔታዎችን እንደ አንገት አዟዙሮ ለማየት ይጠቅመናል። የኢትዮጵያ ችግር አቅጣጫው አንድ ብቻ አይደለም። ቢሆንም ቢሆንም እኛ ኢትዮጵያውያንን ጥቂቶች ቀደው እማይጨርሱን ባለ ብዙ ገጽ መጽሀፍ መሆናችችን ደግሞ ተስፋ ይሰጠናል። አስተያየቱን በሉ አድምጡልኝ!

Filed in: Amharic